Get Mystery Box with random crypto!

የአልበርት ካሙ ወርቃማ አባባሎች አልበርት ካሙ(ከ1913-1960) በሥነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት የ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የአልበርት ካሙ ወርቃማ አባባሎች

አልበርት ካሙ(ከ1913-1960) በሥነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት የተበረከተለት ትውልደ አልጀሪያዊ ፈረንሳዊ ደራሲና ፀሐፌ ተውኔት ነው። እንደ የልቦለድ ደራሲ፥ ወግ ፀሐፊ፥ ጋዜጠኛና ፀሐፌ-ተዉኔት ስሙ የገነነ ነዉ። አልበርት ካሙ በሥራዎቹ የሕይወትን ወለፈንድ(the absurdity of life) በስፋት ዳሷል።

ምድር ላይ ብዙም ያልሰነበተው ካሙ ከሆነ ስፍራ በባቡር ለመሳፈር ሲጣደፍ ጓደኛዉ በመኪና ካላደረስኩህ ብሎት እያሽከረከር ሲጓዝ በሌላ መኪና ይገጫሉ። ጓደኛዉ ሲተርፍ፥ ካሙ ግን በአደጋው ይሞታል። ልክ እንደ ፅሁፎቹ አሟሟቱም ፍልስፍናዉን -የሕይወት ወለፈንድን- ያደምቃል ይላሉ ብዙዎች ከአባባሎቹ ለዛሬ እንቀንጭብ:-

1.በዚህ ሁሉ መኃል መረዳት የቻልኩት በተሸፈነ ድቅድቅ ክረምት ውስጥም የተሸሸገ በጋ በውስጤ ተዳፍኖ መኖሩንና ማግኘቴን ነው::

2.እስከ ዕንባህ የመጨረሻ ጠብታ ጥረስ ኑር፤

3. ደስተኛ ለመሆን ስለሌሎች ከልክ በላይ መጨነቅ የለብንም።

4.በሁሉም ውብ ልብ ውስጥ አንዳንዴ ኢ-ሰብአዊ የመሆን ነገር አለ።

5.ሰዎች ያለቅሳሉ ምክንያቱም ይች ዓለም ፍትሐዊ አይደለችምና

6.እኔ ያለሁት ስላመጽኩ ነው።

7.ነጻነት የተሻለ የመሆን ዕድል እንጂ ሌላ አይደለም።

8. ልቦ-ለድ በምስል የተገለጸ ፍልስፍና እንጂ ሌላ ዐይደለም

9. በዓለም ላይ ያለው ክፋት ሁል ጊዜ ከድንቁርና የሚመጣ ነው፣ መልካም ህሳቤም ከሌለው የመጥፎ ስሜት ያህል ይጎዳል።

10. የሕይወት ትርጉም ምን መሰለህ(ለሽ) 'ራስህን ከማጥፋት የሚከለክልህ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እሱ የሕይወት ትርጉም ነው።

11. በየቀኑ የምትወስነው በጣም አስፈላጊው ውሳኔ 'ራስህን ላለመግደል መወሰን ነው።

12. ሕይወት የሁሉም ምርጫዎችዎ ድምር ውጤት ነው፣ ታዲያ ዛሬ ምን እያደረክ ነው?

13. ደስታና ወለፈን ሁለት የተለያዩ የአንድ ምድር ልጆች ናቸው፣ አይነጣጠሉም።

14. ራሴን ላጠፋ ወይንስ ቡና ልጠጣ? በመጨረሻ አንድ ሰው 'ራሱን ከማጥፋት ከሚያስፈልገው ድፍረት ይልቅ ለመኖር የበለጠ ድፍረት ያስፈልገዋል።

15. ተስፋ 'ኮ የለም እንፈጥረዋለን 'ጂ

16. የወለፈንድ(absurd) ጽንሰ-ሐሳብ አስፈላጊና የመጀመሪያው እውነት ነው።

17. እኔ የምወደው ሥዕሎችህን ሳይሆን ሥዕልህን ነው።


ሳሙኤል በለጠ ባማ ( በኔ የተመረጡ እና የተተረጎሙ )

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology