Get Mystery Box with random crypto!

ምዕራባውያን በነፃነት የመጠየቅ ጠንካራ ባህል አላቸው። የሰዎችን ንግግር እንድያው በድፍን ቅል ይ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ምዕራባውያን በነፃነት የመጠየቅ ጠንካራ ባህል አላቸው።
የሰዎችን ንግግር እንድያው በድፍን ቅል ይሆናል በሚል አይተረጒሙም። የተባለው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ ማብራሪያ ይጠይቃሉ ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዝህ መጠን የመጠየቅ ባህሉ ያለን አይመስልም። እንዲያውም በአብዛኛው ለንግግሮቹ አሉታዊ ትርጓሜ በመስጠት ጉዳዩን በጥሬው (በራሳችን ግምት) የምንወስደው ይመስላል። አንድ ወዳጄ ይህ ችግር አትመርምር አትጠይቅ ከሚለው ጨቋኝ ባህላችን እንደሚነሳ ይናገራል፡፡ እንዲያውም አሁን የምናየው የአገሪቱ ዝርክርክ ፖለቲካ ከዝህ ፈላጭ ቁራጭ አኗኗር እንደሚመነጭ ያስረዳል፡፡

ምዕራባውያኑ ግን ጥያቄንና ምርምርን የእውነት ማንሸራሸሪያ ሠረገላ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ ብንጠይቅ ብንመራመር ሰዎች ይቀየሙናል የሚል አስተሳሰብ የላቸውም። ለምን ተጠየቅሁ ለምን ተመረመርሁ በሚል አምባጓሮ የሚያነሳ ጦር የሚሰብቅ ፍልሚያ የሚገጥም ሰው ፈፅሞ አይገኝም። እኛ ግን ጥያቄ ያበዛብንን ሰው እንደጠረጠረ ምናልባትም ክብረ ነክ በሆነ መንገድ እንደሰደበን እናስባለን። በሃይማኖቱም አካባቢ ጥያቄን ማብዛት አምላክን እንደመፈታተን የአእምሮ ሰው እንደመሆን ነው የሚታየው። በትምህርት ቤትም በቤተ ክህነትም ነገሮችን በግልቡ እንድንቀበል ይጠበቃል። ከምርምር ይልቅ ግባታዊነትና ስሜታዊነት ክፉኛ የተጫነው መንፈሳዊነት እኛ ዘንድ በብዛት አለ። አእምሮን የሰጠን አምላክ አእምሮን አሽገን እንድናስቀምጠው እንደት ይፈልጋል? ዐዋቄ/አማሬ ኵሉ የሆነ ልዑል አምላክ ከትንሿ አእምሯችን የምትመነጨውን ትንኝ ጥያቄ የመመለስም ሆነ የማርካት ዐቅም ሊያጣ ወይም ለምን ተጠየቅሁ ብሎ ሊቁጣ እንደት ይችላል?

#ዶርክር_ተስፋዬ_ሮበሌ

መፀሀፍ (ሥነ አመክንዮ) ገፅ 40-43

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology