Get Mystery Box with random crypto!

ይችን መብት ለሚስቴ ... የአሜሪካ ፖሊሶች በሆነ ወንጀል ጠርጥረውህም ይሁን እጅ ከፍንጅ ሲ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ይችን መብት ለሚስቴ ...


የአሜሪካ ፖሊሶች በሆነ ወንጀል ጠርጥረውህም ይሁን እጅ ከፍንጅ ሲይዙህ ( ያው አጉል ካልተሳፈጥክና ካልተፈራገጥክ በስተቀር እንዲሁም ሰኔና ሰኞ ካልገጠመብህ ማለቴ ነው ) በካቴና የሚቀፈድዱህ ሳይሆን የእጮኝነት ቀለበት የሚያጠልቁልህ ነው የሚመስሉት! ካቴናውን እያጠባበቁልህ ረጋ ባለ ድምፅ Anything you say can and will be used against you in a court of law. You have the right to an attorney...You have the right to remain silent....ምናምን ይሉሀል ...እና አንድ ሚስኪን አበሻ እያሳዩኝ ነው ...የአእምሮ ህመምተኛ ነው አሉኝ! ከሰባት አመት በፊት ሰይጣን አሳስቶት፣ የአሜሪካ ኑሮ ራሱን በጥብጦትና ተበሳጭቶ አውርታ የማታባራ ሚስቱን "አፍሽን ዝጊ አንች ሴትዮ" ይልና ፀጉሯን ጨምድዶ ቢላዋ አንስቶ ይዝትባታል ሬስቶራንት ውስጥኮ ነው ደግሞ!

እንደልብ የሚዛትባት አገር ዜጋ ነውና ...ዛቻውን ረስቷት አገር ሰላም ብሎ ወደቤቱ ሲመለስ የፖሊስ መኪና እያንባረቀ አስቆመዋ!የሆነ ሰው ደውሎ ጠቁሞ ነው... የሬስቶራንቱን ሴኪውሪቲ ካሜራ አይተውታል ! እና ከመኪናው ውረድ አሉና እጁን እያሰሩ ....You have the right to remain silent.... (ምንም ያለመናገር መብት አለህ) ...ሲሉት
"አይ ይችን መብት ለሚስቴ በሰጣችሁልኝ " ብሎ ዝም አለ ዝም አለ ! በቃ ዝም አለ ...ፍርድ ቤት ዝም ፣እስር ቤት ሲልኩት ዝም ፣እስሩን ጨርሶ ሲወጣ ዝም ፣ይሄው ሰባት አመቱ ዝም!!ፀበል ቢባል ህክምና ቢባል ዝም !! በሉ የምታውቁት ሰዎች ስም እንዳትጠቅሱ!

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology