2022-10-06 20:56:29
#Stoicism #ስቶይሲዝም
የስቶይሲዝም አስተምህሮ በዜኖ (Zeno 334-262 ቅ.ል.ክ) አማካኝነት በግሪክ ቢወለድም ያደገውና የተስፋፋው ግን በሮማ ውስጥ ነው፡፡ በጣም የታወቀው ስቶይክ ፈላስፋ ደግሞ Epictetus ነው (50 – 135 ዓም) ነው የኖረው ። በወቅቱ ስቶይሲዝም በጣም ከመወደዱ የተነሳ አብዛኛው ሰው ፈላስፋዎችም ምሁራኖቹም ባለሥልጣኖችም ራሳቸውን "እኔ ስቶይክ ነኝ" እያሉ ይጠሩ ነበር፡፡
ልክ በ20ኛው ክፍለዘመን ፈረንሳይ ውስጥ "እኔ Existentialist ነኝ" ማለት ፋሽን እንደነበረው ሁሉ ሮም ውስጥም "እኔ ስቶይክ ነኝ" ማለት የአዋቂነት ማሳያና ፋሽን አድርገው ይወስዱት ነበር፡፡ የስቶይክ ት/ቤቶች በአቴንስ፣ በሮም፣ በአሌክሳንደሪያ (ግብፅ) እና በመካከለኛው ምስራቅ (ለምሳሌ ባቢሎን) ይገኙ ነበር።
ክርስትናም ሲወለድ አንዱና ዋነኛ ተገዳዳሪው የነበረው የስቶይክ አስተምህሮ ነው፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስም ጳውሎስ ከስቶይኮችና ኤፒኩሪያንስ ጋር እንደተገናኘና በጳውሎስ የትንሳኤ-ሙታን” ትምህርት እንዳፌዙበት ተፅፏል (ሐዋ 17: 18-34)። ስቶይሲዝም በዚህ ጥንካሬውና ስፋቱ በክርስትና መሸነፉ አስገራሚ ነው።
ወደ አስተምህሯቸው ስንመጣ እንደ ሲኒኮች ሁሉ ስቶይኮቹም ራሳቸውን በመገደብ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ስቶይኮች ከሲኒኮች በሁለት ነገሮች ይለያሉ፡፡
የግድየለሽነት (ስቶይሲዝም) ሥነ-ዓለማዊ መሰረት The Metaphysical foundation of Stoicism)
የስቶይኮች የግዴለሽነት ሜታፊዚካል መነሻቸው "ከእኛ ውጭ ሆኖ ይሄንን ዩኒቨርስ የሚያስተዳድር ሎጎስ (Reason) አለ" የሚል ነው፡፡
ይህ ሜታፊዚካዊ መሰረት ወደ ሞራል ሲመጣ "በዓለም ላይ የሚሆነው ነገር ሁሉ በምክንያት ነው አንድም ነገር ያለምክንያት የሚሆን ነገር የለም፡፡ ይሄ ምክንያትም በጎ ነው" የሚል ትርጉም አለው፡፡
ስቶይኮች የሚታወቁበት ትልቁ ልዕልናም Virtue ) "Indifference” ይባላል፤ "ለነገሮች ግድየለሽ መሆን" ወይም "አይሞቀው አይበርደው" ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡
ይሄም ማለት ከዚህ ዓለምም ሆነ ከሰዎች ምንም አለመጠበቅና በማንኛውም ነገር በስሜት አለመነካት ነው፡፡ ምክንያቱም "መጠበቅ/Expectation" ካልተሳካልን የሥነ ልቦና ስብራትና የስሜት መፍረክረክ ያጋጥመናል።
Expectation leads to frustration !!!
በዚህም የተነሳ ስቶይኮች በቀላሉ በስሜታቸው የማይነኩ የማያዝኑ፣ የማይደሰቱ፣ ስሜታቸውን በበቂ ሁኔታ የመቆጣጠር አቅም ላይ የደረሱ ናቸው፡፡
ስቶይኮቹ እንደዚህ ዓይነት ስብዕናን ለማዳበር የቻሉበት አስተሳሰብ እንዲህ የሚል ነው፣
" በዓለም ላይ የሚሆነው ነገር ሁሉ በምክንያት ነው፤ ያ ምክንያት ደግሞ በጎ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ ውጫዊ የሆነን ነገር እኛ መቆጣጠር አንችልም፤ ከእኛ አቅም በላይ ነውና፡፡ ልንቆጣጠር የምንችለው ስለነገሮች ያለንን አመለካከት ብቻ ነው፡፡ ይሄም ማለት፣ ውስጣዊ የሆነው ነገር ላይ ሥልጣን ያለን ሲሆን፣ ውጫዊ የሆነው ነገር ላይ ግን ሥልጣን የለንም፡፡ በመሆኑም፣ ሥልጣን በሌለን ነገር ላይ ለመቆጣጠር መሞከር ደስታችንን ይነጥቀናል፡፡ ስለዚህ፣ ደስታ ልናገኝ የምንችለው ልንቆጣጠረው በምንችለው ነገር ላይ ብቻ በመቆጣጠር ነው፡፡"
JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
860 viewsAbu Ki, 17:56