Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @yegna_psychology
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.64K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ አስተሳሰባችንን የሚያሳድጉ የሳይኮሎጂ እና የፓለቲካ ፅሁፎች ይቀርቡበታል።
የኛ ሳይኮሎጂ ይተነተናል እንዲሁም ታዋቂ የሥነ-ልቦና ሊሂቃን (theory) ይዳሰሳል።
🌟ማሳሰብያ ለውድ ተከተዮቻችን:➪አባላትን ለማብዛት በምናደርገው #የማስታወቂያ ልውውጦች እንዳትሰላቹብን ለማለት እንወዳለን።

[ ራሳችንን በመቀየር ድርሻችንን እንወጣ! ]

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-08-23 19:45:18
ኢትዮጵያን ከነብጉሯ ያሳየች ተዋናይት!


እረኛየን በደንብ ተከታትየዋለሁ! በብዙ ብዙ መስፈርት የማይታመን ብቃት ያየሁባት ተዋናይት ይች ነች! የትወና ብቃቷ ከገሀዱ ዓለም አኗኗር ንፋስ እንኳን በማያስገባ ርቀት የተጠጋ፣ በእምነት ይሁን በባህል ሳትሸፋፈን ራሷን የሆነች ምርጥ ገፀባህሪ! እንደውም ማስመሰሉን ትተን ዙሪያችንን ብንመለከት ኢትዮጵያ በ"እማማ ቸርነት" ሳይሆን በዚች (ወላንሳ)ገፀ ባህሪ ነው የምትወከለው ለእኔ! ጉስቁልናዋ ፣ ብረት የሆነ ጠንካራ የእናትነት መንፈሷ ፣(እናትነት ደግነት ብቻ አይደለም ለቤተሰብ አነር መሆንም አለበት) ሚስትነት (እንደብዙሀኖቹ ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ሚስቶች ከጓዳ ሁና እራሷ ብትጎሳቆልም አደባባዩን የምትዘውር! ) ወንዱኮ በአደባባይ ዘራፍ ይላል እንጅ መሪዎቹ እንደዚች አይነት ሚስቶች ናቸው! እና ባሏን ቱግ ሲል የምታቀዘቅዝበት ሲፈዝ የምታነቃበት መንገድ ! ንቃቷ! አንድም ጊዜ ለእኔ ስትል አትታይም ፤ቤተሰቧ ነው ህይወቷ! ቤተሰቧ ነው ህልሟ! ህመሟም ደስታዋም ቤተሰቧ ነው! ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ገፀ ባህሪ ማለት ይች ነች! ኢትዮጵያዊነትን ከነብጉሩ ያሳየች! ስትጀምር ብቻዋን ሲያልቅም ከአቋሟ ንቅንቅ ሳትል ከሰፈርተኛው ጋር ሳትንጋጋ ብቻዋን! የእውነት አስደምማኛለች! እንደገፀ ባህሪም በግል በትወና ብቃቷም ! ከዚህ በፊት የሰራችው ፊልምም ይሁን ድራማ ይኖር ይሆን? እና ስሟ ማነው? የእውነት አስገርማኛለች!!
JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.1K viewsAbu Ki, edited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 19:42:30 #ርሃብን_ማመንፈስ_መንፈሳዊነት_አይደለም!


ርሃብ እና ድህነትን መንፈሳዊ ሊያደርጉ የሚጣጣሩ ሰዎች አያለሁ! ለማሳመን የሚያባክኑት ሀይል እርሻ ላይ ቢውል ሄክታር መሬት ያለማል! እንደውም ርሀብን ፅድቅና ወደአምላክ መቅረብ አድርገው ሊሰብኩን ይዳዳቸዋል! ይህን በመስበክ ራሳቸው ከድህነት ያመልጣሉ አገርና ህዝብ ግን "አሜን" እያለ በጠኔ እንዲኖር ይፈርዱበታል!

ርሃብና ፆም ይለያያል ጓዶች! (መቸም ለእናተ አልነግራችሁም)
ፆም ፈቅደህና ወደህ መብላት እየቻልክ ይቅርብኝ ብለህ የሚፈፀም መንፈሳዊ ልምምድ ነው ! ርሀብ ግን ምክንያቱ ምንም ይሁን ማጣት እግር ከወርች አስሮህ የሚላስ የሚቀመስ ማጣት ነው! አደጋ ነው፣ ችግር ነው፣ገዳይ ነው፣ ሰቆቃ ነው! ርሃብ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ እድሜ ልክ ሊዘልቅ ይችላል! ህፃናት በወጉ ካልተመገቡ ነፍሳቸው ቢተርፍ እንኳን በአካልም በአስተሳሰብም ይቀነጭራሉ! ርሃቡ አልፎ እንኳን የአካልና ስነልቦና ቅንጨራው አብሯቸው ይኖራል!

ርሃብ አደጋ ስለሆነ በዜና ይነገራል! " ይሄን ያህል ህዝብ ለረሃብ ተጋለጠ" ሲባል የምንሰማው እሱን ነው! " ይሄን ያህል ህዝብ ለፆም ተጋለጠ " ሲባል ሰምተን እናውቃለን? ስለፆምክ ትራባለህ ፣ስለተራብክ ግን አትፆምም!!

ፆመኞች ርሃብተኞች፣ ርሃብተኞችም ፆመኞች አይደሉም! ፆመኞች ናፍቆታቸው የመንፈስ ርሃባቸውን የሚያረካ የፈጣሪን ፊት መፈለግ ሲሆን ርሃብተኞች ህልማቸው ርሃባቸውን የሚያስታግስ ቁራሽ ማግኘት ነው! ፆም ወደፈጣሪ በመንፈስ ሲያቀርብ ርሃብ ፈጣሪን እስከመካድ ሊያደርስ ይችላል! በየትኛውም እምነት "ተቀበሉ" ከሚለው ቃል ይልቅ "ስጡ መፅውቱ " የሚለው በዝቶ ታገኙታላችሁ ! የሚልስ የሚቀምሰው ያጣ አይሰጥም! እንደውም የርሃብን አስከፊነት እንደመፅሐፍ ቅዱስ ያስነበበን የለም!

ሁለት እናቶች እንደዳቦ ህፃናት ልጆቻቸውን ደርድረው "ዛሬ ያንችን እንብላው ነገ የእኔን "ተባብለው እስከመብላት ደርሰዋል ! ወንጀል እና ድህነት መንታ ችግሮች ናቸው የሚባለው ለዛ ነው ! ርሃብ በስብከትም በፉከራም አይጠፋም! ወይ በእርዳታ ታስታግሰዋለህ አልያም ሰርተህ በክንድ ከስሩ ትነቅለዋለህ! የሚሟጭረንን የድህነት ጥፍር ቀለም እየቀባን ከማስዋብ "የድህነታችን ምክንያት ምንድነው?" ብሎ ማሰቡ ይሻለናል ...ከየትኛው ሰባኪ ከየትኛውም ምሁር በላይ ርሃብ ራሱ የሚሰጥህን ህመም አዳምጥ ... ርሃብ " የመንፈስ ፍሬ" አይደለም!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.0K viewsAbu Ki, 16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:13:31 ኢትዮጵያ "ዓለም የሚፈራት" አገር!


"ዓለም ኢትዮጵያን አብዝቶ ይፈራታል" የሚል ትንቢት ይሁን ቅዤት በዚህ ዘመን የሚያወሩ "ምሁራን" አሉ! ከፈረደባቸው ግብፅና ሱዳን በስተቀር (እነሱም በዚህ የአባይ ጉዳይ ባለባቸው ስጋት) ኢትዮጵያን የሚፈራ አንድም አገር በዓለም ላይ የለም!! በታሪክ የተመዘገበ ራስን ከወረራ የመከላከል አኩሪ ታሪክ አለን! አሁንም ወረራንና ቅኝ ገዢነትን የማይቀበል እምቢ ባይ መንፈስ አለን። በተረፈ ራሳችንን ከመከላከል አልፎ ሌላውን ዓለም የሚያስፈራ የጦር አቅም ፣ የኢኮኖሚም ይሁን የዕውቀትም ደረጃ ላይ አይደለንም! ራሳችንን መግበን ማደር እንኳን አልቻልንም! በተቃራኒው እርስ በርሳችን የምንፈራራ፣ አንዱ ክልል ሌላውን የሚፈራ ፣ አንዱ ህዝብ ሌላውን እንዲፈራ ፣ ህዝብ መንግስትና ባለስልጣናትን እንዲፈራ የሚሰበክባት አገር ህዝቦች ነን! ሌላውን ማስፈራራቱ ይቆየንና በራሳችን አገር ሳንፈራ ሳንሰጋ ፣የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ እንደዜጋ አንገት ማስገቢያ ጎጆ አግኝተን በሰላም ውለን ካደርን ትልቅ ስኬት ነው!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.4K viewsAbu Ki, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:02:36 #ኢትዮጵያዊ_ለመሆን_መስፈርቱ_ምንድነው?


ኢትዮጵያዊ ለመሆን መስፈርቱ (ሌላውን የህግ ጣጣ ትተነው) ኢትዮጵያ ምድር ላይ መወለድ ነው! በቃ! አስር ጊዜ በየወንዙ ኢትዮጵያዊ ነኝ እያሉ መማማል ፣ መፎከር ፣ ሰባት ትውልድ መቁጠር ፣ የአርበኛ የልጅ ልጅ መሆንህን ማስመስከር ፣ ክንድህም ላይ ይሁን ሆድህ ላይ የኢትዮጵያን ካርታና ስም መነቀስ ወይም ባንዲራ አናትህ ላይ ማሰር ኢትዮጵያዊ አያደርግም! ጀግና ሁነህ ደምህን ብታፈስላት ፣ ታታሪ ሁነህ በዓለም በበጎ ብታስነሳት ኢትዮጵያን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ የሚጠይቀውን ሃላፊነት የተወጣ ራሱን ያከበረ በሌሎችም የተከበረ ዜጋ እንጅ ዜግነት ሰጭና ነሽ አትሆንም!መልካምነት ምንድነው የሚለው እንዳለ ሁኖ መልካም ዜጋ ለ"መጥፎ ዜጋ" ዜግነት የመስጠትም ሆነ የመንጠቅ መብት የለውም! መልካምነት ስልጣን አይደለም!

እና በተቃራኒው ኢትዮጵያን ስትራገም ብትውል፣ ድድ ማስጫ ተጎልተህ ብትቦዝን ፣ ኢትዮጵያዊነትህን ብትጠላ፣ ኢትዮጵያዊያንን ብትፀየፍ ፣ ምለህ ተገዝተህ ብትክዳት ባንዳ ሆነህ ብትወጋት ፣ሙሰኛ ሁነህ ብትዘርፋት ፣ከሀዲ ሁነህ መውደቂዋን ብትቆፍር ፣ በሌሎች ብታሰድባት ምድሯ ላይ ስለተወለድክ ክፉ ኢትዮጵያዊ ትሆናለህ እንጅ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ልትባል አትችልም! አንድ ጀርመናዊ ባለስልጣን እንዳሉት "ሂትለር ጀርመናዊ ነው፤ ግን ጀርመን የምታፍርበት ጀርመናዊ ነው! "
አሌክስ አብርሃም

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.3K viewsAbu Ki, edited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:01:22
#Ethiopia
2.9K viewsAbu Ki, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 21:58:25 ራስህን ከማንም ጋር አታፎካክር!


በምድር ስትኖር ደስተኛና ሰላማዊ ህይወት መምራት ከፈለክ ራስህን
ከማንም ጋር አታፎካክር! ፋክክር ያንተን መንገድ ሳይሆን የሰውን ጎዳና አመልካች ነውና ። የራስህን መንገድ ዘርጋ! የራስህን አለም ፍጠር! በራስህ አለም ተደሰት!
ውድድርህ ከሰው ጋር መሆኑ ቀርቶ ከትናንትናህ ጋር ይሁን! ከትናንትህ ከተሻልክ በየቀኑ አሸናፊው አንተ ነህ!
በህይወት ሜዳ ላይ ከራስህ ጋር ብቻ ተፋለም ፣ ከራስህ ጋር ብቻ ተወዳደር ፣ ከራስህ ጋር ብቻ ታገል ፣ ራስህን ብቻ አሸንፍ! ምንም ከፍ ብትል ሰው ያልረገጠውን ከፍታ አትረግጥምና! ቀለል ብለህ በራሰህ መንገድ ፣ በራስህ ጎዳና ኑር ጀግናዬ !!!

ሰናይ የራስነት ምሽት!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.6K viewsAbu Ki, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:37:56 #መላክ_የሆነ_ጓደኛ_ከፈለግህ_ማረፊውን_ገነት_ፍጠርለት!!!

አንዳንዴ እኛ መልካም ነገሮች ወደ ሕይወታችን ማምጣት እንፈልጋለን እነዛን
መልካም ነገሮችን ለማስተናገድ የሚሆን መልካምነት ግን እኛጋ የለም ።
እኛ ቁምነገረኛ ሳንሆን ቁምነገረኛ የሕይወት አጋር የምንፈልግ ብዙዎች ነን!
ነገሮች ከኛ መጀመር እንዳለባቸው በራሳቸው ወደኛ ከመጡም መልካም
ነገሮችን በመፍጠር ከኛ ጋር የሚሆኑበትን መንገድ ለመክፈት ቁልፉ በኛ እጅ መሆኑን አንዳንዴ እንዘነጋዋለን ።
ይሄንን ያመጣው ከራሳችን የመስጠት ሳይሆን ከሰው ብቻ የመጠበቅ ፍላጎትን
ብቻ የማድመጥ አባዜአችን አይመስላችሁም...??
መልአክ የሆነ ጓደኛ ከፈለግህ ማረፊያውን ገነት ልትፈጥርለት ይገባል
ምክንያቱም መልአክ ሲኦል ውስጥ አይቀመጥምና ።
.....አንዳንዴ መነሻው እኛ መሆናችንን መዘንጋት የለብንም እኛጋ መልካምነት ሳይኖር ግን መልካም ነገር በኛ ሕይወት እንዲፈጠር የምንፈልግ ስንት ራስ ወዳዶች በየቤቱ እንኖር ይሆን...?? ስንቶቻችን ውስጣችን ነዲድ እሳትን ተላብሶ መልካም እሳቤዎችን አቃጥሎ ይሆን..
/ከካህሊል_ጂብራን አንደበት/

የመልካምነት ቀን ያድርግልን!!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.7K viewsAbu Ki, edited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:38:51 #ትናንት_የዛሬ_ባሪያ #ዛሬ_ለነገ_ንጉስ_ነው !!

ጊዜ ውስጥ ትናንት ትዝታ ነገ የተስፋ ጎተራዎች ናቸው ከሔደው ትናንት ያልመጣው ነገ ይሻላል ከሁሉም ከሁሉም ግን ዛሬ ይበልጣል።
/ከሌላ ሰው ገፆች/
ምን ይዞ እንደሚመጣ ለማይታወቀው መጪው ጊዜ መፈንጠዝና በምኞት ፈረስ መጋለብ ካላቆምክ፣ ትናንትናንና ነገን ትተህ ዛሬን መኖር እስካልጀመርክ ነፃ አትወጣም። ነፃነት አሁን እዚህ ናት።
/ከኦሾ ገፆች/
ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም፡፡ ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም። ምክንያቱም ነገን መኖር ስንጀምር ዛሬ ተብሏል፡፡ ቡዙዎቻችን ግን ሁሌም ብሩህ ነገን ለመኖር ስንናፍቅ ብዙ ዛሬያችን ያልፈናል፡፡ እናም ብሩህ የሚባል ቀን ሳይኖረን እናልፋለን፡፡ ብሩህ ቀን ማለት በእጃችን ያለው ዛሬ ነው!
/ከጠበኛ እውነቶች ገፆች/
ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ነው ።
/ከሜሎሪና ገፆች/
የእምነት የቅርብ ወዳጁ እና ጓደኛው ተስፋ ነው። ተስፋ ነገ ሲሆን እምነት ደግሞ ዛሬ ነው። ተስፋ ነገን አይቶ ሰው እንዲደሰት የማድረግ አቅም ሲኖረው እምነት ደግሞ ተስፋውን ሄዶ ያመጣውና ዛሬ ላይ ያደርገዋል ።
ተስፋ ነገ ላይ ሆኖ መደሰት ሲሆን እምነት ደግሞ ዛሬ ላይ ሆኖ መደሰት ነዉ ። ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሸዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን፡፡
ትናንት የዛሬ ባርያ ፣ ዛሬ ለነገ ንጉስ ነው!!!
/ከሬማ እና ሌጎስ ገፆች/
የዛሬ ሰው ያድርገን!!

መልካም ምሽት

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
4.3K viewsAbu Ki, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:37:10 ራስን ማወቅ

"ራስን ማወቅ ሌላውንም ማወቅ ይሆናል። ካወክ ዘንድ ለራስህ የምትሻውን ለሌላውም ትመኛለህ። ለራስህና ለሰው ልጅ ሁሉ በጎ ፍቃድና ፍቅር ይኖርሃል። ከዚህ ዕውቀት ደረጃ ላይ ስትደርስ ለምታደርገው ነገር ሁሉ ምስጋናም ሆነ ጥቅም ከሰው ዘንድ አትሻም። ልብህ ጥቅም ላይ ካተኮረ የተፈጥሮን በጎ ምግባር ትስታለህ።"


JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
7.3K viewsAbu Ki, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 14:32:38 ይቅርታ!! የፅድቅ ህይወት ጋሻ

የይቅርታ ልብ ከሌለህ ሠውን ባትወድና ባታፈቅር ይሻልሀል ሠው ሆኖ የማይሳሳት የለምና መሣሣት የሠው ባህሪ ነው። ልክ ለምን ታመምኩ ሳይሆን አንተ ፈውሰኝ እንደሚባል ሁላ ለምን ተሳሳተ አይባል። የስህተት ሁሉ ምንጭ ብዙ ነውና፣ ከጥልቁ ምርመራ ከክፋ ፈረጃ ርቀህ ይቅርታን አስብ።

ይቅርታን መጠየቅ ሥህተትን የሚያክም ፍቱን መድሀኒት ሢሆን ይቅር ባይነት ደግሞ የታላላቅና የባለብሩህ አዕምሮ ሠዎች ሀብት ነው!!
ይቅርታ!! የፅድቅ ህይወት ጋሻ...የቂም ማርከሻ ቃል ኪዳንን ማደሻ ነው!!
የበደለንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር ፣ ቀንነትን መዝራት ፣ ህይወትን ማደስ ነው።
ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበትና ይቅር የሚል ብሩህ ልብ ይስጠን!!!

ይቅርታ!! የፅድቅ ህይወት ጋሻ

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
6.2K viewsAbu Ki, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ