2022-08-14 12:02:32
እውነት አንፃራዊ ነች?
ስለ እውነት አንፃራዊነት አልያም objectivity ጥያቄን ለመመለስ ከ matter of knowledge እና matter of opinion አንፃር ነገሮችን ከፍለን እስኪ እንመልከታቸው፡፡
በ እውቀትና በopinion መካከል ደግሞ ሰፊ ልዩነት አለ በእርግጠኝነት እና በprobability መካከል ያለው ልዩነት ከ እውቀትና opinion ልዩነት ጋር ይያዛል።
እናም ከአንደኛው opinion ሌላኛው opinion የትኛው ይሻላል የሚለውን የምንወስነው ከመሆን ዕድላቸውና ከጥቅማችን አንፃር ነው፡፡
የግል ዕይታህ opinion) የሚመሰረተው ከፍላጎትህ ፣ከጥቅምህ ፣ከምትወደው አንፃር ነው፡፡ እውቀት በእውነት ላይ የተመሰረተና እንዳለኸም የምታውቀው ነገር ነው።ምክንያቱም የምታስበው ነገር ለምን እውነት እንደሆነ ታውቃለህና፡፡ በopinion ግን እውነት እንዳለህ በእርግጠኝነት ላይ የተመሰረተ አይደለም።የተናገርከው እውነት ይሁን ውሸት እርግጠኛ መሆን አችልም፡፡ያልከው ነገር እውነታ ቢኖረው እንኳን ለምን እውነት እንደ ሆነ አታውቀውም።
ሌላው ሊነሳ የሚገባው ነጥብ opinion(የግል ዕይታ) እውነትም ውሸትም ሊሆን መቻሉ ነው።opinion ትክክልም አልያም ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ እውቀት ግን ውሸት ሊሆን አይችልም የውሸት እውቀት የለም። የተሳሳተ እውቀትም የለም። የውሸትና የተሳሳተ እውቀት ሊሆን የማይችል ነገር ነው፡፡ ሌላው የሚለያቸው ነጥብ | በእውቀት(እውነት) አስገዳጅ መስማማት ውስጥ እንደሚጥለን ነው ፣ Opinion ግን ከእምነት ሊመነጭም መቻሉ ነው፡፡
ለምሳሌ
1+2=3 ይህንን አውቃለው ለምን እንደሆነም እረዳዋለው፡፡ይህን አይደለም ብዬ ልከራከርበት አልችልም "አምንበታለው"ልልም አልችልም። እምነት እዚህ ጋር ቦታም የለውም። እኔም "1+2=3" መሆኑን አላምንበትም እንደሆነ አውቃለው እንጂ፡፡ግን አሁን ተነስቼ "ባህላችን ለሀገራዊ አንድነት ፈር ቀዳጅ ናቸው" ብል የመስማማትም ያለመስማማትም ዕድሉ አላቹ ምክንያቱም ( it's not a statement of knowledge ) Opinion እስከሆነ ድረስ ደግሞ የመስማማትም ሆነ ያለመስማማት ዕድሉን ይከፍትላችዋል።
ሌላ ምሳሌ በሁለት ሉዓላዊ ሀገራት መካከል ምንጊዜም የቀዝቃዛ አልያም የጦፈየመሳሪያ) ጦርነት አለ ብል እውነት ነው ማናችንም እውነት ለምን እንደሆነ እንረዳዋለን።ነገር ግን " ከቀጣይ 25 ዓመት በኋላ የአለም ጦርነት ይካሄዳል" ብል Opinion ነው። ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ማረጋገጫ የለንም።
አንዳንዶቻችን ልናምንበት፣አንዳንዶቻችን ደግሞ ልንቃወመው እንችላለን ነገር ግን it is not a statement of knowledge
መልካም ሰንበት
JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
4.7K viewsAbu Ki, 09:02