Get Mystery Box with random crypto!

#አይዞን ! በዓለም ላይ ካሉ እድለቢስ ዜጎች መሀል እጣችን ወድቆ ዓመቱን ሙሉ የጅምላ እልቂ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

#አይዞን !


በዓለም ላይ ካሉ እድለቢስ ዜጎች መሀል እጣችን ወድቆ ዓመቱን ሙሉ የጅምላ እልቂት ፣ ጦርነት፣ ርሀብ፣ ስጋት ሰቆቃ እንስማና በዚህ ውስጥ እናልፍ ዘንድ ተገደናል! ቢሆንም አይዞን!

እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ የኑሮ ውድነት ውስጥ በማይገባን የኑሮ ደረጃ ፣የዓመታት ድካምና ልፋታችንን በማይመጥን አሳዛኝ ኑሮ እየኖርን ነው ቢሆንም አይዞን!

በስደት በመንከራተት ፈፅሞ ባላሰብነው መንገድ ያላሰብነው ቦታ ተገኝተን ይሆናል ...አይዞን!

እንደህዝብ በብዙ ፈተናና በብዙ አጣብቂኝ ውስጥ ያለንም ቢሆን የትኛውም ችግር ፀሐያችንን የጋረደ ደመና እንጂ ጨርሶ ተስፋ የሚያሳጣ የማይነጋ ፅልመት አይደለምና አይዞን!

አጉል ጎረመስኩ ባልኩባቸው አመታት አጓጉል ይመስሉኝ የነበሩ አስተሳሰቦች አሁን ላይ ስሜት ይሰጡኝ ጀምረዋል! በዋናነት "ጊዜ ይዞ የሚመጣው አይታወቅም" ይሉትን ብሂል ወደማመኑ ነኝ ...አይዞን "አዲስ ዓመት" እንዲሁ ልምድ አይደለም ... በሁላችን ልብ ውስጥ አዲስ ተስፋ የሚያስቀምጥ በእርግጥም አዲስ ጊዜ ነው! ተስፋ ሁሉም ነገር ነው ! በጊዜ ተስፋ እናድርግ ፣በተስፋም የጊዜን ተዓምር እንጠብቅ፤ ሁሉም ነገር አዲስ ይሆናል ... እንደሰው የምንከበር፣ እንደሰው የምንወደድ እና እንደሰው በሰው ክብር ልክ የምንኖርበት ጊዜ ይመጣል ! ተስፋችንን ብቻ አንጣል ...አይዞን !! እደግመዋለሁ አይዞን !

መልካም አዲስ ዓመት!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology