Get Mystery Box with random crypto!

#ወሎ የወሎ ሰው ጨዋታ አዋቂና ወግ አሳማሪ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡ ለምስክር እንዲሆን | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

#ወሎ

የወሎ ሰው ጨዋታ አዋቂና ወግ አሳማሪ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡ ለምስክር እንዲሆን ከሱፊስቶች ጋር የሚመሳሰል ጨዋታቸውን ከብዙ በጥቂቱ እነሆ፡፡ [በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጨዋታ የነገሩኝ ወዳጆቼን አመሰግናለሁ]

የቡና ቁርስ

ወሎ ውስጥ ነን፡፡ አንድ እንግዳ ቡና እንዲጠጣ ከጎረቤቶቹ ጥሪ ይደርሰዋል፡፡ ቤታቸው ሄዶ ቁጭ እንዳለ ቡና ከመቅረቡ በፊት ምግብ እንዲቀምስ የእጅ ውኃ አመጡለት፡፡ እንግዳው በቅርብ ስለበላ ቡና ብቻ መጠጣት እንደሚፈልግ ይነግራቸዋል፡፡ ሰዎቹም ፤ እንግዳው ሊያፍር ይችላል በሚል እጁን እንዲታጠብ ገፋፉት፡፡ በቀላሉ እንደማይለቁት ሲያውቅ መብላቱን በመሀላ አስረግጦ ተናገረ፡፡ ይሄን ጊዜ ሴትዮዋ ሳቅ አሉና፤

"ተው?! ወጡን ቀምሶ ነበር ወላሂ ማለት" አሉ፡፡ እነሆ ጨዋታ . . .

[አቦል]

ደሴ ውስጥ የነበረ ምግብ ቤት አሉ፡፡ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በጋራ ይጠቀሙበታል፡፡ ከፈለጋችሁ ስሙን "ቄስ መሐመድ" ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ የክርስቲያን እና የእስላም ምግቤት ይላል፡፡ አንድ ከመሀል አገር የሄደ ሰው በከተማው ሲዘዋወር ምግቤቱን ያየዋል፡፡ ከድሮ ጀምሮ ስለ ወሎ ሙስሊምና ክርስቲያን ተስማምቶ መኖር ይሰማ ነበር፡፡ እንዴት እንደሚኖሩ ለማየት ፍላጎት ስላደረበት ጎራ አለ፡፡

ፈራ ተባ እያለ ወደ ምግብ ቤቱ ገቤቶ የቤቱን አንድ ምግብ እንድያመጡለት አዞ ቁጭ አለ፡፡ ብዙ ሳይቆይ የታዘዘው ምግብ ቀረበ፡፡ ማዕዱን ሲያይ ከመደነቁ የተነሳ ከጉርሻው በፊት ሳቁ ቀደመ፡፡ የቀረበለት ሽሮ ነበር! የምግብ ቤቱ ስም ኀብረታቸውን ለማጠናከር ያደረጉት መላ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ገባው፡፡

[ቶና]

አንድ በመንደሩ የታወቀ ጀግና አንድ ቀን ምንሽሩን ታጥቆ ከቤት ወጣ፡፡ ሰው ሁሉ አገር አማን ብሎ በተቀመጠበት ወደ ሰማይ ካልተኮስኩ ብሎ ይገላገል ጀመር፡፡ አንድ ወዳጁ ደርሶ ምን ለማድረግ እንዳሰበ ይጠይቀዋል፡፡

"አላህን ልገለው ነው!" አለ ፈርጠም ብሎ፡፡ ሰውዬውም ቀበል አድርጎ፤

"ካገኘኸው ገላገልከን፡፡ ከሳትከው ግን አስጨረስከን" አለው፡፡

[በረካ]

ይህቺ ደግሞ ባቲ ውስጥ ያለች አነስተኛ ምግብ ቤት ነች፡፡ [ አሉ ናት ] የምግብ ዝርዝር መጻፊያ "ሜኑ" የላትም፡፡ በቤቱ የሚዘጋጀው ሁለት ዓይነት ምግብ ብቻ ስለሆነ የምግቡ ዓይነት እና ዋጋ ግድግዳው ላይ ነው የተጻፈው፡፡

1. ቀይ ወጥ

2 .ስፔሻል ቀይ ወጥ

አንድ እንግዳ ወደ ምግብ ቤቷ ገብቶ አስተናጋጁን ጠራና ምሣ ምን እንደደረሰ ይጠይቀዋል፡፡ አስተናጋጁም ወደ ግድግዳው እየጠቆመ፡፡ "ቀይ ወጥ፣ ስፔሻል ቀይ ወጥ" ይለዋል፡፡ እንግዳው ትንሽ ካሰላሰለ በኋላ ስፔሻሉ ቀርቶ ቀይ ወጥ ብቻ እንዲመጣለት አዘዘ፡፡

ምግቡ ቀርቦ መብላት ሲጀምር በቤት ውስጥ ያሉ ድመቶች፤ ሠላሳ ይሆናሉ፡፡ በሙሉ ወደ እሱ መጡ፡፡ አንዳንዶቹ የሚበላውን ለከፉበት፡፡ ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆን የሚበላውን ትቶ በዛውም ስፔሻል ቀይ ወጡን ለማየት ሌላ ምግብ አዘዘ፡፡

ትንሽ ቆይቶ አስተናጋጁ ያንኑ ቀይ ወጥ ከዱላ ጋር ይዞለት መጣ፡፡

[ምርቃት]

አንድ ደረሳ [ዲያቆን እንደማለት ነው] ብዙ ዓመት አብራው የኖረች ሚስቱ ትሞትበታለች፡፡ ጓደኞቹ የሐዘኑን ክብደት አይተው ሌላ እንዲያገባ አግባቡት፡፡ እርሱ ግን እንደ ሚስቴ የሚሆን አላገኝም በሚል እምቢ አለ፡፡

ከሁለት ዓመት ውትወታ በኋላ አንድ ጓደኛው አንዲት ልጅ ፈልጎ ይድረዋል፡፡ ዐዲስ ሕይወትም ይጀምራል፡፡ ለሱ ሁሉም ነገር እንግዳ ስለሆነበት በጣም ተገረመ፡፡ በተለይ አልጋ ላይ ያለው ቆይታ ከጠበቀው በላይ አስደሳች ሆኖ አገኘው፡፡

አንድ ቀን ይሄ ወዳጁ ትዳር እንዴት ነው ለማለት እሱ ዘንድ ይሄድና፤

"እህ ልጅት እንዴት ናት አንተው?" ብሎ ይጠይቀዋል፡፡

"አጃኢብ ነው ወላሂ፡፡ መቼም አላህ አያልቅበትም፤ ምነው ይቺንም በገደላት"

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology