Get Mystery Box with random crypto!

Venue

የቴሌግራም ቻናል አርማ venuee13 — Venue V
የቴሌግራም ቻናል አርማ venuee13 — Venue
የሰርጥ አድራሻ: @venuee13
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.06K
የሰርጥ መግለጫ

መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር!
:
መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ
ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:02:21 #አንዳንዴ 16
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
#አንዳንዴ አልቅጥ እንቸኩላለን። ሁሉንም ነገር የምንረዳ፣ ሁሉንም ነገር የምናውቅ፣ ሁሌም ልክ የሆንን ይመስለናል። ከአስተሳሰባችንና ከምናምንበት ተቃራኒ የሆነ ነገር ሲገጥመን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ስለምንሰጠው ምላሽ ያስጨንቀናል። #አንዳንዴ ትክክል እየሰራን ባይሆንም ልክ አይደላችሁም መባል አንፈልግም። #አንዳንዴ እራሳችንን ጣኦት አድርገን እናመልካለን። እኛ ያልነው ብቻ ልክ እኛ ያልነው ብቻ ትክክል አድርገን በጭፍን ተቀብለን በአመክንዮ ስህተቶቻችንን ለማስረዳት የሚጥሩትን እናወግዛለን። #አንዳንዴ ተሳስታችኋል መባል ያሸማቅቀናል። የአውቃለሁ ጉራችን ያሰቃየናል። #አንዳንዴ እንሰለቻለን። ያደነቅነው ውበት ያስጠላናል፣ የናፈቅነው ትርጉም አልባ ይሆንብናል፣ ያገኘነው እርካታችንን ይነጥቀናል። #አንዳንዴ የፍቅራችን እድሜ ከፈስ ድምፅ ያጥራል። የቱንም ያህል ብንታገል እንደማናዛልቀው አይነት ይሆናል። #አንዳንዴ ሁሌም የምንጠቃ ይመስለናል። ወሬዎች ሁሉ ስለኛ፣ ቀልዶች ሁሉ ስለኛ፣ አሽሙር ሁሉ እኛን ለመንካት ይመስለናል። #አንዳንዴ ከራሳችን ጋር አኩኩሉ እንጫወታለን። እውነታውን አውቀን ለራሳችን << ነጋ >> ለማለት እየፈራን << አልነጋም >> እያልን ሰበቦችን እየቆጠርን መኖር እንለምዳለን። #አንዳንዴ የገፉንን እየናፈቅን የደገፉንን እንንቃለን። #አንዳንዴ ዘንበል ብለን ቀጥ ያልን ይመስለናል። ተንጋለን ወድቀን ተኝቼ ነው የቆምኩት እንላለን። በውስጣችን ስለብዙ ነገሮች ማብሰልሰላችን አይቀርም። ምንም ይሁን ምን ብቻ #አብሽሩ!
:
@Venuee13
@Venuee13
200 viewsBabi, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:23:54 @Venuee13
261 viewsBabi, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:28:30
#አብሽሩ!

@Venuee13
172 viewsBabi, edited  15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:17:06 #አንዳንዴ 15
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
<< ውድ ነገራችን ምንድን ነው? ክብራችን? ፍቅራችን? ወይስ ምን? #አንዳንዴ ምን ውድ ነገር እንዳለን አናውቅም።
ውድ ነገራችንን ስለምንሰጣቸው ሰዎች ግድ ሰጥቶን ያውቃል? #አንዳንዴ ከምንም የማንቆጠረው እራሳችንን ስላረከስን ነው። ተው ርካሽ ከሚያድርጓችሁ ጋር ልምምጥ አቁሙ። መለያየትን በመፍራት ሰበብ የማይደርቅ ቁስላችሁን አትከኩ። በተለይ አጓጉል አፍቅርያለሁ በሚል እራሳችንን አናዝረክርክ። ይሄ ለፍቅር ምንም ቢከፈል አይቆጭም የምትል ዝርክርክ አባባላችሁን ጣሉት። #አንዳንዴ የተረት ተረት ንግርቶች የምር እንዳንኖር እያደረጉን ነው። #አንዳንዴ…>>
:
@Venuee13
@Venuee13
223 viewsBabi, edited  11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:20:20 " ስጠረጥር " 13
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
ስለ እንቅልፍ ትንሽ እናውራ እስቲ። ልጠይቃችሁማ የላጤና የባለትዳር እንቅልፍ አንድ አይነት ነው እንዴ?(እስቲ ባለትዳሮች እና ላጤዎች ትንሽ ማብራርያ ብትሰጡን ጥሩ ነው። አሀ ማወቅ አለብና። )
እንጠርጥር እንዴ?………እ……እንጠርጥር?
ምን ጣጣ አለው እንጠርጥራ ታድያ!
ላጤ እንቅልፍ፣ ባለትዳር እንቅልፍ የሚባል ነገር ለምንድን ነው የሌለው ቆይ?( ኧረ ወገን የሆነ ነገር በሉ)
ላጤ የሆነ ሰው ባለትዳር እንቅልፍ ሊይዘው ይችላል?
እንደውም ቆይ…
ህልም የምናየው ላጤ እንቅልፍ ሲይዘን ነው ወይስ ባለትዳር እንቅልፍ ሲይዘን? እኔኮ……አልጠርጥር!
ለማንኛውም እያንቀላፋችሁ ማነው እየተኛችሁ አቦ መልካሙን ተመኘሁ!
:
@Venuee13
@Venuee13
273 viewsBabi, edited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:46:13 አያቴን ምንም ቢከሰት ምን እንዴት ኖት ስላቸው ሁሌም << በጣም ደህና ነኝ። ጊዜዬ ነው። >> ይሉኛል። እኔም ምንም ቢከሰት ምን ሁሌም በበረካው ደህና ነኝ። ብዙ ስላዳመጥኳቸው ብዙ ነገር መክረውኛል። ከዚህ ቀደም እንደነገርኳችሁ ባቢዮ ወይም ሀኪም ነው ብለው የሚጠሩኝ። ከአያቴ ፋጢማ(ሰወት) ንግግሮች መካከል ትንሽ ላካፋላችሁ። ንግግሮቻቸውን ማስተንተን እና በጥልቀት መረዳት የእናንተ ድርሻ ይሆናል።

<< አላህ ክብር ይስጥህ። >>

<< የሚያውቅ ምከረው ለማያውቅ ምን ብዬ ልምከረው። >>

<< ጥሩም ስራ መጥፎም ስራ በልጅህ ታገኘዋለህ። >>

<< ወልደህ እየው። >>

<< ያንቺን በሆድሽ ይዘሽ በኔ ልጆች ትጫወቻለሽ?>>(ያልወለዱ ሰዎች ልጆቻቸውን ሲቆጧቸው የሚሉት ነው)

<< ኧረ ተፈርቶ ሊሞት ነው ወይ >>

<< ሞት እየወደድክ አይገልህም። >>

<< እያለው ከሚቸገር ሰው ሰላም። >>

<< እራስህ ያልቻልከው የሰው ሆድ አይችለውም። >>

<< ጥሩ ዘር ሁን። >>

እነዚህ ንግግሮች ከኔ ጋር ስናወጋ በቀልቤ መዝግቤ ካስቀረኋቸው ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። #በማካፈል_ውስጥ_ደስታ_አለ። ለዚህም ለእናንተ ማካፈልን ወደድኩ። እናንተም ጋር ካለ አካፍሉን። በዱዓችሁ አስታውሱን።
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13
358 viewsBabi, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:22:41
#አንዳንዴ 14
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
<< ለምንወዳቸውና ለሚወዱን ሰዎች ብቻ ሳይሆን ማጣት ላይ፣ መለያየት ላይ፣ ናፍቆት ላይ ፈገግ!
ገዳይ ላይ፣ ጨካኝ ላይ ፈገግ!
የውስጥ ህመምን ለማሳቀቅ ፈገግ!
ውድቀታችንን የሚፈልግ ላይ ፈገግ!
ህልሞቻችንን ቅዠት ብሎ በሚሳለቅ ላይ ፈገግ!
የትም አትደርሱም በሚሉን ላይ ፈገግ!
ነፃ እንወጣለን ስንላቸው እንደ እብድ በሚቆጥሩን ላይ ፈገግ!
በሚንቁን ሰዎች ላይ ፈገግ!
ፈገግታ ትርጉሙ ጥልቅ ነው። #አንዳንዴ ከንግግር የበለጠ ፈገግታ የሚያሸብረው አለ። ምንም ቢሆን ምን እንደምንም እንደ ፍልስጢን ሰዎች ፈገግ በሉ። አንዳንድ በረካ የሆኑ ፈገግታዎች አሉ ፈገግ ማለትን የሚያስታውሱ። #አንዳንዴ…>>
:
@Venuee13
373 viewsBabi, 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 06:51:49 #እያሰብን 26
:
<< ትንሽ ነገርን የማተለቅ፣ ኢምንትን የማግዘፍ በሽታ ያለባቸው ሰዎች አሉ። አላህ ይማራቸው። ሕፃን ልጅ የሚጫወትበት አፉፋ ወደቀብኝ ብላችሁ ያዙኝ ልቀቁኝ የምትሉ ሰዎች በሰላም ነው ግን? ኧረ እያሰብን! >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13
324 viewsBabi, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:09:40 #አንዳንዴ 13
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
የሚሰማሽን ለመግለፅ ቃል አጥተሽ አታውቂም? ኡፍ! ኤጭ! የሚሉ ቃላት ምንም አልገልፅ ብለውሽ አያውቅም? ሁሌም ከፋኝ፣ አመመኝ፣ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ማለት ስልችት አላለሽም? ከዚህ ቀደም የሚያዳምጡሽ የነበሩ ሰዎች አመለኛ አድርገውሽ የሆነ ነገር ልትነግርያቸው ስትይ << ጀመረሽ ደግሞ፣ በቃ ሌላ ወሬ የለሽም? >> እያሉ ምርር እንዳላቸውና የምትነግርያቸው ሁሉ ስልችት እንዳላቸው ሹክ አላሉሽም? የምትተማመኚበት ምንም ስራ ሳይኖርሽ መሞትን አልናፈቅሽም? ከዚህ የባሰ ብዙ የሚሰሙሽ ስሜቶች አሉ ይኖራሉም። ደግሞ ከሞተ ትዝታሽ ጋር አትጓተቺ የወደድሽው ወይም የወደደሽ ልጅ እንደድሮው አያይሽም። የራሳቸውን ሕይወት እየኖሩ አንቺን በሆነ ነገር የሚጎነትሉሽ ሰዎችን የራሳችሁ ጉዳይ በያቸው። የቤተሰብ ጉዳይም አንቺ ስትስተካከዩ ይስተካከላል። #አንዳንዴ ጅል ጥሩነት አለ። ለማይገባቸው የዋህነትሽን አትስጫቸው። በእርግጥ #አንዳንዴ ትንፋሽሽ ሁላ ይከብደሻል። ግን #አብሽሪ! መኖር ጀምሪ! ጠባሳዎችሽን ለማጥፋት ንቅሳት አትነቀሺ። #አንዳንዴ ጠባሳዎች ጥሩ ናቸው ካላፈርንባቸው። እና ደግሞ ተንፍሺ! ጌታሽን እየተውሽው የሚተውሽ ነገሮች ላይ አትሯሯጪ። እስከዛሬ ጠይቄው ምን አደረገልኝ ካልሽ እንግዲህ ተበርቸ ሰላም ብያለሁ። #አንዳንዴ አጠያየቅና ለመጠየቅ ብቁ መሆናችንን ሳናውቅ በዘፈቀደ እንደወሬ እየጠየቅን ጠይቀን አልተሰጠንም እንላለን። ተንፍሺ………አየር አይደለም። እና ደግሞ #አብሽሪ! #አንዳንዴ…
:
@Venuee13
@Venuee13
367 viewsBabi, 15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:02:01 የኔ...
(ነጃት ሀሰን)
:
ወደቅኩ አልኩት... ውድቀቴ ግርጌ የተገነባልኝን ማማ ሳላስታውል!

ብቻዬን ተውከኝ አልኩት... ከስብስቤ ክፋት እንደጠበቀኝ ትዝም ሳይለኝ!

ውበቴም ፍቅሬም ዓለሜም ባንተው ተሰራ አሏህዋ...ብዙ ምስጋና ላንተው ይገባ...አልሐምዱሊላህ!

አሏህዋ ከህመም መሻሪያ የምትሆንን... ከውድቀት መነሻ... ከክህደት መዳኛ የምትሆነንን ሰላምና ደህንነት በአበባችን በነብያችን ሙሐመድና በባልደረቦቻቸው እንዲሁም በቤተሰቦቻቸው ላይ አስፍን!

ሰናይ ጁመዓ
:
@Venuee13
@Venuee13
360 viewsነጃት ሀሰን, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ