Get Mystery Box with random crypto!

Venue

የቴሌግራም ቻናል አርማ venuee13 — Venue V
የቴሌግራም ቻናል አርማ venuee13 — Venue
የሰርጥ አድራሻ: @venuee13
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.06K
የሰርጥ መግለጫ

መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር!
:
መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ
ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-06-29 07:27:18
< ሳይታወቃቸው ብዙ ፈረንጅ የሚያመልኩ ሰዎች ገጥመውኛል። እውቀት ሁሉ፣ ጥበብ ሁሉ፣ ፍቅር ሁሉ፣ ሁሉንም ነገር ሁሉ ለፈረንጅ ብቻ የተሰጠ አድርገው የሚያምኑ ሰዎችን ታዝብያለሁ። ዓለም ላይ ብዙ ከማይመቹኝና ከማይጥሙኝ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የቁንጅና ውድድር ነው። የተለያየ ውበትና ቁንጅና ያላቸውን በአንድ አይነት መስፈርት እንዲያልፍ ማድረግም ስህተት ይመስለኛል። ቀይ ሁሉ ውብ አይደለም። ጥቁር ሁሉ አያስጠላም። ነገር ግን በታህተ ህሊናችን ላይ ሳናስበው የተቀመጡ አስተሳሰቦች ተጭነውናል። ውብ እና ቆንጆ ብለን ስንል ምክንያቱን በደንብ እናውቀው ይሆንን? ምክንያቱንስ እውነት አምነንበት ፈትሸነው ነው ወይስ መስፈርት ተብሎ በብዙሀኑ ስለታመነበት? እኔ ግን ሁሉም ያደነቀውና የወደደው ሁሉ ተውቦ አይታየኝም፣ ሁሉም የጠላውና ያጠለሸው አስቀያሚ አልልም። >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
393 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:24:18 " ማስጠንቀቅያ ለባለቤቴ " 10
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
ደህና ሰው መስዬሽ ቶሎ እንዳገባሽ በዱዓ የበረታሽው የማላውቅሽ ባለቤቴ ሆይ እንደምን አለሽ? እኔ ይኸው ዝናብና ብርድ ሲበዛ ትዝ አለሺኝ። ደግሞ ብርድ ምናምን ስለ አልባሌ ነገር አስቢ አሉሽ ደግሞ። ለነገሩ……ብቻ ተዪው። የኔ ቋቋቲያም አሮጊት ለምንድን ነው የማታገቢው? ምን ልሁን ብለሽ ነው እኔን የምትመኚው? ኧረ እንደው አላህ ቀልብ ይስጥሽ። እስቲ አርፈሽ አግቢ። በነገራችን ላይ እውነቱን ስነግርሽ አንቺ ኢንኩቤተር ማለት ነሽ። አሀ…አረጋጊው እንጂ ላስረዳሽ። ምን መሰለሽ……እንደውም ተዪው ድሮም ማስጠንቀቅያው ነው የሚያዋጣው። ከዚህ ቀደም ብዙ ማስጠንቀቅያዎች አስፍሬልሽ ነበር። እንግዲህ በብዙ ነገር የሚያስጠነቅቀኝ ስለበዛ ተጨማሪ ማስጠንቀቅያዎችን እንደሚከተለው አስፍርያለሁ እያየሽ ግቢበት።
ውዷ የማላውቅሽ ቀልበ ቢሷ ባለቤቴ ሆይ ሒውማን ሔር ነጋዴ ሆኜልሻለሁ። በሀገራችን የሚገኙ መላጣ ሴቶችን ሁሉ መለየት ችያለሁ። ይገርምሻል ባለፈው አንዱ አንዷን ሊያገባት ፈልጎ ፎቶዋን እያሳየኝ << እኔ ምልህ ይቺ ልጅ መላጣ ነች እንዴ? >> ብሎ ጠየቀኝ። ልጅቷ ደግሞ በቅርቡ የሀያ ሺህ ብር ሒውማን ሄር የሸጥኩላት ነበረችና ደንበኛዬን ላለማስቀየም ስል << ኧረ ዞማ ነው ፀጉሯ> > ብዬ መለስኩ። ይኸውልሽ እኔ ፀጉር እወዳለሁ። ያንቺ ፀጉር እንደሆነ ስታስነጠሺ ሁላ ይፈታል። ግን ፀጉርሽን ባትንከባከቢው ወየውልሽ። ባለሽ ነገር ከመዋብ ይልቅ ተቀጥላ ነገር የሚማርክሽ ከሆነ አለቀልሽ።
ስሚኝማ አስሬ በዱዓሽ ስሜን እያነሳሽ አከሳሺኝ አኮ። ምነው እቴ አልበዛም እንዴ! ደግሞ ነግሬሻለሁ የራስሽ ካረግሺኝ በኋላ ዓለም በቃኝ አይነት ጨዋታ እጫወታለሁ ብትዪ! ላንቺ ያለኝ መውደድ እንደ ኑሮ እንዲሆን በደንብ እራስሽን መጠበቅ አለብሽ። እንዲህ ስልሽ ታድያ ሳማ በድንብላል በሰናፍጭ እና በአሮጊት ፈስ ደበላልቀሽ ፊትሽን ተቀቢ አሉሽ ደግሞ። አንቺ እንደሆነ አታደርጊውም አይባልም። አሁን እኮ ተዋቡ እና እራሳችሁን ጣሉ ተምታቱብን። እንግዲህ ወደፊት ማስጠንቀቅያዎችን እንደ ሁኔታው ማሻሻያና ጭማሪ አደርግባቸዋለሁ። ለማንኛውም እኔን አላህ ይጠብቅልሽ። አሚን ባትዪም ይጠብቀኝ።
:
@Venuee13
@Venuee13
404 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ