Get Mystery Box with random crypto!

Venue

የቴሌግራም ቻናል አርማ venuee13 — Venue V
የቴሌግራም ቻናል አርማ venuee13 — Venue
የሰርጥ አድራሻ: @venuee13
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.06K
የሰርጥ መግለጫ

መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር!
:
መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ
ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-02 19:10:52
410 viewsነጃት ሀሰን, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:10:27
መቼስ እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ ኣ? የወደዱትን ለሚወዱት እንኩ ማለት ደስ ይላል። በመፅሀፍ ግብዣ ተገናኘን። የሀገር ፍቅር ስሜታችን ቋፍ ላይ በተንጠለጠለበት ወቅት ስላነበብኩት እጅግ መልሶኛል። የውስጥ ድካሜ አይሎብኝ ነበርና የሚገርም ተነሳሽነትን ፈጥሮልኛል። ከሁሉም ደግሞ ከሀገሬ ሰማይ ስር እንዲህ ያለ ከውከብ ዶክተር ስላለ እጅግ ተደሰትኩ። መፅሀፉ ላይ አይደፈሬ የተባሉ የልብ ሰርጀሪዎች እንዴት በብቃት እንደተከወኑ ያትታል። መጨረሻ ላይ ከዛ ስቃይ እፎይ ያሉ የታካሚዎችን ምስክርነት አካቷል...እንዴት አንጀት ይበላሉ በጀሊል! ከሰውኛ የማዘን ስሜቴ ጋር አገናኝቶኛልና ታነቡት ዘንድ ጋበዝኩ።

የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ
በዶክተር ፈቀደ አግዋር


(ነጃት ሀሰን)
:
@Venuee13
@Venuee13
384 viewsነጃት ሀሰን, edited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:41:36 ስለ'ሷ...
(ነጃት ሀሰን)
:
ልቧ ሳቂታ ነው። በሙሓባ ጥርሶች ያሸበረቀ። ስትወድ እስካትጠላ ድረስ ነው። መንገዱ ሩቅ ነዋ...ከመውደድ እስከመጥላት ያለው?
እነዛን የፍቅር ጥርሶች አረጋግፈህ ስትሄድ ሌላ አበቀለች እንጂ በድዱ አልረገመችህም። ስለራሷ ህፀፆች ተብሰለሰለች እንጂ ስለክህደትህ ማሰቢያ ወቅት አልፈጀችም። ዘመን ተሻግረህ ብትከሰትም ያው ተፍነክናኪ ልብ ነው ምታገኘው...እሷ ስለሆነች!!

መውደዷን ስትክድም፡ በለይል ዱዐዋ ስምህን ታወሳለች...እሷን ማጣትም መበደልህ...ላንተ ትልቁ ክስረት ይመስለኛል...ከክስረት ይጠብቀንና!!
:
@Venuee13
@Venuee13
353 viewsነጃት ሀሰን, 14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 17:23:20 ሰዎች ማለት…
የሚዘነጉ የሚታወሱ
በሀዘን በደስታ የሚቀመሱ
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13
396 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 09:45:04
" አይገባኝም "
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
<<……ጥፍራም ቃላት ሰድጄ ልብ የምቧጭር፣ ሀገር የሚያህል ግዴለሽነት ይዤ ፈላጊዬን የማስጨንቅ፣ አዝራዒል ወዳጄ የሆነ ይመስል ለፍርሀት ዋስትና በመስጠት የምሸነግል። እንዲህ ነው መኖር ስለሚፈልጉ ስለ አዝራዒል አያወሩም። እራሳችሁን በደንብ አልፈተሻችሁትም ይሆናል እንጂ ከአላህ የበለጠ ለአዝራዒል ልባችሁ መደንገጥን ይዟል። ዝብርቅርቅ ያለ ሀሳብ ለምን እንዳወራሁ አላውቅም። በእርግጥ ማወቅ ስለምትፈልጉ ትፈርዳላችሁ። አልፈርድም ብላችሁ ልትዋሹ አይቻላችሁም። እስካሁን ባለው ሕይወታችሁ ሳትፈርዱ አልተገኛችሁም። ብቻ ምንም ይሁን ምን ግን አይገባኝም።…… >>
(Loading)
:
@Venuee13
401 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 17:31:19 " እውነት እውነቱን "
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
ሰላም ድንብርብር የምትለው ደንባራው ሕዝቤ ሆይ እንግዲህ ከረጅም ጊዜ በኋላ ቢሆንም ልክ ልክህን ልንገርህ። እየመረረህም ቢሆን አጣጥመው። እኔ እንደሆነ ግድ የለኝ።
ህዝቤ ሆይ አስመሳዮች ነን። #እውነት_እውነቱን ስንነጋገር በማስመሰል የተካንን ቂሎች ነን። እየጠላን እንዳፍቃሪ ይሰራራናል፣ የልባችንን ከሰራን በኋላ እናላዝናለን፣ ለቅሶ ቤት ሔደን እንኳ ሟችና ቤተሰቡን በሀሜት እጥብ እያደረግናቸው አፅናኝ እንመስላለን። #እውነት_እውነቱን ስንነጋገር አንተማመንም። ልከክልህ እከክልኝ ጨዋታ መጫወት ደስ የሚለን እከካሞች ነን። #እውነት_እውነቱን ስንነጋገር እናስጠላለን። የሌለንን ነገር እንዳለን ለማስመሰል የምንጋጋጥ ስራ ፈቶች ሆነናል። ሁላችንም እያስመሰልን ምንም የማናውቅ እንመስላለን። ህዝቤ ሆይ አጉል ሐይማኖተኛ፣ እራሳችንን ንፁህ አድርገን ብንመለከትም አስመሳይነታችን ይጎላል። #እውነት_እውነቱን ስንነጋገር አናስመስል። ካስጠላን አስጠላን፣ ከወደድን ወደድን፣ ካላወቅን አላወቅም ማለት እንልመድ። ምንድን ነው ወደንም፣ አፍቅረንም፣ ናፍቀንም፣ ምንም እንደማያቅ የሚያደርገን? ምንድን ነው ምንም ነገር ሳይገባንና ሳናምንበት ሌሎችን ስላየን ብቻ የአዞ እንባ የምናፈሰው? ማስመሰል ኩራትን በደንብ አድርጎ ያደልባል። እንደው ምንም ማድረግ የማንችልበት ሁኔታ ቢሆን እንኳ ምነው ዞር ማለት ብንችል። #እውነት_እውነቱን ስንነጋገር አስመሳይነታችንን ላለማመን ለድርጊቶቻችን የተለያየ ትርጉም ለመስጠት የምንሞክር አስመሳዮች ሆነናል። ነፍስ ከችሎታዋ በላይ እንደማትገደድ በግልፅ ተቀምጦልን ምንድን ነው እንዲህ እይታ ለመሳብ መዝረክረክ! እንግዲህ #እውነት_እውነቱን ስነነጋገር የሚመራችሁ፣ የምትኮፈሱ፣ ልክ ነው የሚል ሀሳብ ያሰባችሁ፣ ምንም ያልመሰላችሁ በሙሉ አታስመስሉ። ህዝቤ ሆይ እንግዲህ መረረም ጣፈጠ #እውነት_እውነቱን ዋጥ ስልቅጥ አድርጉት። ይኸው ነው እንግዲህ!
:
@Venuee13
@Venuee13
383 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 07:29:12 የሆነው ሁሉ ሁኖና እየሆነ...መኖር መልካም ነው...ማምሻም እድሜ ነውና!!

ሰላም ከጉያችሁ ትሁን ቤተሰቦቻችን።
:
@Venuee13
@Venuee13
385 viewsነጃት ሀሰን, 04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 23:42:47 "ሰዐት እላፊ" ሀጅ
(ነጃት ሀሰን)
:
<ድርብርብ ወቅትን ከርሜ ልወቅስሽ አፍም የለኝ...እንዲሁ ግን በቅርብሽ ስላለው ብስራት ባወጋሽ ተመኘሁ... አምናና ከዛ በፊት በዚህ ጊዜ ስለ መካም፣ ስለመዲናም...ስለዘምዘም ስለሙዝደሊፋም...ስለአረፋ ስለ ሚናም...ስታልሚ ነግቶ ይመሽ ነበር ኣ? የናፍቆት ስንኝ ስትሰድሪ...የጥራኝ ውትወታ ስታነበንቢ ነበር ኣ? ሁሉንም ነበር ማለትስ ውስጥ አሁን ምን አሰረሽ የሚል ጥያቄን መስደዴ አይቀርም... ባያስችለኝ ነው መነዛነዜ!>

<<ልክ ነሽማ ሀያቲ... የሚሆነውም የሆነውም ሁሉ እንኳን ምኞትን፡ የገዛ ራስንስ ያስረሳ የለ? እንዲያ ሁኖብኝ ነው... ብዙ ሰበብ መደርደር እችል ይሆናል...ብቻ ተይውና አሏህዬ ይጥራንና ለበይክ እንበል ሀያታችን ሳይከላ!!>> እኔዋ።
:
@Venuee13
@Venuee13
384 viewsነጃት ሀሰን, 20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 16:55:09
#Venue_Propagation #16
:
#በማካፈል_ውስጥ_ደስታ_አለ

<< መጓጓዣ ስንጠቀም እንድረስ አንድረስ ሳናውቅ ቀድመን ከፍለን እንሔዳለን። ክፈሉ ስንባል እንኳ ካልደረስኩ ብለን ችክ አንልም። ምክንያቱም መሔድ እንፈልጋለና። ከሰዎች ጋር ለምን መተማመን ከበደን? >>
#እስቲ_ሀሳብ_ስጡበት_እይታችሁን_አካፍሉን
410 views𝕭𝖆𝕭𝖎, edited  13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:55:09 ስለ ማስታወቅያ እና ብዙ የቻናል ቤተሰቦችን ስለማፍራት በውስጥ ጥያቄዎች ይደርሱኛል። በእርግጥ ሀሳቦቻችን ብዙ ሰው ጋር እንዲደርሱ ከማሰብ የመነጨ እንደሆነ እረዳለሁ። በግል የመለስኩላችሁ እንዳለ ሆኖ ስለ ብዛት ጥያቄ ላላችሁ በዚሁ ልመልስ። በማስታወቅያ እየረበሹ መብዛት ብዙ ትርጉም አይሰጠኝም። ቬኑ ላይ ምንም አይነት ፕሮሞሽን እየተሰራ አይደለም። በግል ድንገተኛ አጋጣሚዎች ካልሆነ በቀር። በማስታወቅያ ስልችት አድርገውኝ የተውኳቸው ቻናሎች አሉ። እና የጠላነውን ማድረግ አለብን? ባይሆን ከወደዳችሁት ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ እናንተው ለሌላው አካፍሉ። በአሁን ጊዜ አዳዲስ ወዳጆችን ከማፍራት የበለጠ ወዳጆችን ማቆየት እየከበደ መጥቷል። እኛ በወዳጅነታችን እንሰንብት። ጉዳዩ ከመብዛትና ብዙ ከመታየት አይደለም። ደግሞም ምን ተሰራ ምን አለና ብዙ ሰው ካላየልኝ ተብሎ ችክ ይባላል? ያን ያህል አያሳስባችሁ! ባይሆን እንድንነጋገርባቸው ሀሳቦች ይነሳሉ እናም እናንተም ሀሳቦቻችሁን ለማካፈል አታመንቱ። ሌላው ትርፍ ነው።
:
@Venuee13
390 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ