2022-07-03 11:05:45
<< ባቢ ድሮ የምትወዳት ልጅ ነበረች? >> ከጁመዓ እየተመለስን እያለ ትንሹ ወንድሜ ነው ይህን የጠየቀኝ። ልክ እንደተፈጠረ ያለ ሰው የሚባል አይነት ነው ባህሪው።
<< ምነው ለምን ጠየቅከኝ? >>
<< ማወቅ ፈልጌ ነው ዝም ብዬ >> እስክስታውን ጀምሯል። ዘፈኑ ነበር የቀረው። ሊነግረኝ የነበረው ገብቶኛል ተመቻቸሁለት።
<< አዎ ነበረች። አንተስ አለህ? >> እየተሽኮረመመ ደስ የምትለው ልጅ እንዳለች ነገረኝ። ሀፍረቱ በራሱ ፈገግ ያስብላል። እኔ መጠየቄን ቀጠልኩ። << ምን አስበህ ነው ግን ምኗን ነው የወደድከው?
<< አንተ ምን አስበህ ነው ምኗን ነበር የወደድከው? >> ጥያቄውን ወደኔ አዞረው። ይቺን ጊዜ እኔም ልነግረው የምፈልገውን ለመንገር ተጠቀምኩበት።
<< እኔ የምወዳት የነበረችው ልጅ እናትና አባቷ የሚሏትን ትሰማለች። ጎበዝ ነች። እና እኔ እንደሷ መሆን ስለምፈልግ ነው የወደድኳት። አንተ ምኗን ነው የወደድከው? >> ካዳመጠኝ በኋላ።
<< እኔ የወደድኩት እውቀቷን ነው። >> አለኝ።
<< እንዴት? >> ስል ማብራርያ እንዲጨምርልኝ ግርምት በሚመስል መልኩ ፈታ ብዬ ጠየቅኩት።
<< በቃ ጎበዝ ነች። >>
<< እንደሷ መሆን ስለምትፈልግ ነው የወደድካት? >>
<< አዎ! >>
<< በል ይመችህ። አባና እማ የሚሉህን ከሰማህ እንደሷ ሰው ይወድሀል። >>
<< እሺ! >> ሲል መለሰ። በጊዜው ፈገግ አለማለት አልቻልኩም። ልቤ የሱን ያህል ንፁህ አለመሆኑን ሳስብ እኔነቴ ያሳዝነኛል። ለማንኛውም ታናናሾቻችሁን አታሸማቋቸው። በመጡበት መንገድ የሚያስፈልጋቸውን ሹክ በሏቸው።
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13
420 views𝕭𝖆𝕭𝖎, 08:05