Get Mystery Box with random crypto!

#አንዳንዴ 13 (አብዱልሀኪም ሰፋ) : የሚሰማሽን ለመግለፅ ቃል አጥተሽ አታውቂም? ኡፍ! ኤጭ! የ | Venue

#አንዳንዴ 13
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
የሚሰማሽን ለመግለፅ ቃል አጥተሽ አታውቂም? ኡፍ! ኤጭ! የሚሉ ቃላት ምንም አልገልፅ ብለውሽ አያውቅም? ሁሌም ከፋኝ፣ አመመኝ፣ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ማለት ስልችት አላለሽም? ከዚህ ቀደም የሚያዳምጡሽ የነበሩ ሰዎች አመለኛ አድርገውሽ የሆነ ነገር ልትነግርያቸው ስትይ << ጀመረሽ ደግሞ፣ በቃ ሌላ ወሬ የለሽም? >> እያሉ ምርር እንዳላቸውና የምትነግርያቸው ሁሉ ስልችት እንዳላቸው ሹክ አላሉሽም? የምትተማመኚበት ምንም ስራ ሳይኖርሽ መሞትን አልናፈቅሽም? ከዚህ የባሰ ብዙ የሚሰሙሽ ስሜቶች አሉ ይኖራሉም። ደግሞ ከሞተ ትዝታሽ ጋር አትጓተቺ የወደድሽው ወይም የወደደሽ ልጅ እንደድሮው አያይሽም። የራሳቸውን ሕይወት እየኖሩ አንቺን በሆነ ነገር የሚጎነትሉሽ ሰዎችን የራሳችሁ ጉዳይ በያቸው። የቤተሰብ ጉዳይም አንቺ ስትስተካከዩ ይስተካከላል። #አንዳንዴ ጅል ጥሩነት አለ። ለማይገባቸው የዋህነትሽን አትስጫቸው። በእርግጥ #አንዳንዴ ትንፋሽሽ ሁላ ይከብደሻል። ግን #አብሽሪ! መኖር ጀምሪ! ጠባሳዎችሽን ለማጥፋት ንቅሳት አትነቀሺ። #አንዳንዴ ጠባሳዎች ጥሩ ናቸው ካላፈርንባቸው። እና ደግሞ ተንፍሺ! ጌታሽን እየተውሽው የሚተውሽ ነገሮች ላይ አትሯሯጪ። እስከዛሬ ጠይቄው ምን አደረገልኝ ካልሽ እንግዲህ ተበርቸ ሰላም ብያለሁ። #አንዳንዴ አጠያየቅና ለመጠየቅ ብቁ መሆናችንን ሳናውቅ በዘፈቀደ እንደወሬ እየጠየቅን ጠይቀን አልተሰጠንም እንላለን። ተንፍሺ………አየር አይደለም። እና ደግሞ #አብሽሪ! #አንዳንዴ…
:
@Venuee13
@Venuee13