Get Mystery Box with random crypto!

አያቴን ምንም ቢከሰት ምን እንዴት ኖት ስላቸው ሁሌም > ይሉኛል። እኔም ምንም ቢከሰት ምን ሁሌም | Venue

አያቴን ምንም ቢከሰት ምን እንዴት ኖት ስላቸው ሁሌም << በጣም ደህና ነኝ። ጊዜዬ ነው። >> ይሉኛል። እኔም ምንም ቢከሰት ምን ሁሌም በበረካው ደህና ነኝ። ብዙ ስላዳመጥኳቸው ብዙ ነገር መክረውኛል። ከዚህ ቀደም እንደነገርኳችሁ ባቢዮ ወይም ሀኪም ነው ብለው የሚጠሩኝ። ከአያቴ ፋጢማ(ሰወት) ንግግሮች መካከል ትንሽ ላካፋላችሁ። ንግግሮቻቸውን ማስተንተን እና በጥልቀት መረዳት የእናንተ ድርሻ ይሆናል።

<< አላህ ክብር ይስጥህ። >>

<< የሚያውቅ ምከረው ለማያውቅ ምን ብዬ ልምከረው። >>

<< ጥሩም ስራ መጥፎም ስራ በልጅህ ታገኘዋለህ። >>

<< ወልደህ እየው። >>

<< ያንቺን በሆድሽ ይዘሽ በኔ ልጆች ትጫወቻለሽ?>>(ያልወለዱ ሰዎች ልጆቻቸውን ሲቆጧቸው የሚሉት ነው)

<< ኧረ ተፈርቶ ሊሞት ነው ወይ >>

<< ሞት እየወደድክ አይገልህም። >>

<< እያለው ከሚቸገር ሰው ሰላም። >>

<< እራስህ ያልቻልከው የሰው ሆድ አይችለውም። >>

<< ጥሩ ዘር ሁን። >>

እነዚህ ንግግሮች ከኔ ጋር ስናወጋ በቀልቤ መዝግቤ ካስቀረኋቸው ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። #በማካፈል_ውስጥ_ደስታ_አለ። ለዚህም ለእናንተ ማካፈልን ወደድኩ። እናንተም ጋር ካለ አካፍሉን። በዱዓችሁ አስታውሱን።
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13