Get Mystery Box with random crypto!

#አንዳንዴ 14 (አብዱልሀኪም ሰፋ) : > : @Venuee13 | Venue

#አንዳንዴ 14
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
<< ለምንወዳቸውና ለሚወዱን ሰዎች ብቻ ሳይሆን ማጣት ላይ፣ መለያየት ላይ፣ ናፍቆት ላይ ፈገግ!
ገዳይ ላይ፣ ጨካኝ ላይ ፈገግ!
የውስጥ ህመምን ለማሳቀቅ ፈገግ!
ውድቀታችንን የሚፈልግ ላይ ፈገግ!
ህልሞቻችንን ቅዠት ብሎ በሚሳለቅ ላይ ፈገግ!
የትም አትደርሱም በሚሉን ላይ ፈገግ!
ነፃ እንወጣለን ስንላቸው እንደ እብድ በሚቆጥሩን ላይ ፈገግ!
በሚንቁን ሰዎች ላይ ፈገግ!
ፈገግታ ትርጉሙ ጥልቅ ነው። #አንዳንዴ ከንግግር የበለጠ ፈገግታ የሚያሸብረው አለ። ምንም ቢሆን ምን እንደምንም እንደ ፍልስጢን ሰዎች ፈገግ በሉ። አንዳንድ በረካ የሆኑ ፈገግታዎች አሉ ፈገግ ማለትን የሚያስታውሱ። #አንዳንዴ…>>
:
@Venuee13