Get Mystery Box with random crypto!

#አንዳንዴ 16 (አብዱልሀኪም ሰፋ) : #አንዳንዴ አልቅጥ እንቸኩላለን። ሁሉንም ነገር የምንረዳ፣ | Venue

#አንዳንዴ 16
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
#አንዳንዴ አልቅጥ እንቸኩላለን። ሁሉንም ነገር የምንረዳ፣ ሁሉንም ነገር የምናውቅ፣ ሁሌም ልክ የሆንን ይመስለናል። ከአስተሳሰባችንና ከምናምንበት ተቃራኒ የሆነ ነገር ሲገጥመን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ስለምንሰጠው ምላሽ ያስጨንቀናል። #አንዳንዴ ትክክል እየሰራን ባይሆንም ልክ አይደላችሁም መባል አንፈልግም። #አንዳንዴ እራሳችንን ጣኦት አድርገን እናመልካለን። እኛ ያልነው ብቻ ልክ እኛ ያልነው ብቻ ትክክል አድርገን በጭፍን ተቀብለን በአመክንዮ ስህተቶቻችንን ለማስረዳት የሚጥሩትን እናወግዛለን። #አንዳንዴ ተሳስታችኋል መባል ያሸማቅቀናል። የአውቃለሁ ጉራችን ያሰቃየናል። #አንዳንዴ እንሰለቻለን። ያደነቅነው ውበት ያስጠላናል፣ የናፈቅነው ትርጉም አልባ ይሆንብናል፣ ያገኘነው እርካታችንን ይነጥቀናል። #አንዳንዴ የፍቅራችን እድሜ ከፈስ ድምፅ ያጥራል። የቱንም ያህል ብንታገል እንደማናዛልቀው አይነት ይሆናል። #አንዳንዴ ሁሌም የምንጠቃ ይመስለናል። ወሬዎች ሁሉ ስለኛ፣ ቀልዶች ሁሉ ስለኛ፣ አሽሙር ሁሉ እኛን ለመንካት ይመስለናል። #አንዳንዴ ከራሳችን ጋር አኩኩሉ እንጫወታለን። እውነታውን አውቀን ለራሳችን << ነጋ >> ለማለት እየፈራን << አልነጋም >> እያልን ሰበቦችን እየቆጠርን መኖር እንለምዳለን። #አንዳንዴ የገፉንን እየናፈቅን የደገፉንን እንንቃለን። #አንዳንዴ ዘንበል ብለን ቀጥ ያልን ይመስለናል። ተንጋለን ወድቀን ተኝቼ ነው የቆምኩት እንላለን። በውስጣችን ስለብዙ ነገሮች ማብሰልሰላችን አይቀርም። ምንም ይሁን ምን ብቻ #አብሽሩ!
:
@Venuee13
@Venuee13