Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የሰርጥ አድራሻ: @seratebtkrstian
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.55K
የሰርጥ መግለጫ

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2023-04-13 07:40:13 #ጸሎተ ሐሙስ


አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቲዩብ ወቻናል


ምስባክ ዘህጽበተ እግር


ትነዝኃኒ በአዛብ ወእነጽሕ
ተሐጽበኒ እምበረድ ወእጸዓዱ
ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወሀሴተ

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን ዕብ 12÷2-18
ን/ዲ 1ጴጥ 3÷15-20
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 10÷30-40

#የዕለቱ_ምስባክ

መዝ 20÷5

ወሠራዕከ ማዕደ በቅድሜየ
በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ
ወአጽሐድከ በቅብዕ ርእስየ



#የዕለቱ_ወንጌል

ማቴ 26፥20 -30

ቅዳሴ፦ ኤጲፋንዮስ



አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian


join
1.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 07:38:22 ጸሎተ ሐሙስ


#አዘጋጅ_ዲያቆን_ፍቅረ_አብ_ለሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን_ቲዩብ_(ቻናል)_የተዘጋጀ!



#ጉልባን

ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው

ህፅበተ እግር (እግርን መታጠብ)

እግርን ማጠብ እንግዲህ ያስተማረን ያጠበው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!

ሐዋርያትን (ደቀ መዛሙርቱን) እግራቸውን አጠበ! ትህትናን ሲያስለምረን!

ይህን ድንቅ ትህትና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንዴት ነው?

እግር ማጠቢያ ይዘጋጃል የሚዘጋጀው ከምንድን ነው ?

መልስ

ካህኑ አልባስ እና መጎናፀፊያ ወገቡ ላይ ይጠመጥማሉ ! ከዛም የፀሎት ስርዓቱ ሲያልቅ እርስ በእርሳቸው መጀመሪያ የሚያጥጡት ይታጠባሉ ከዛም ደሞ እኚህን ያጠባቸው በተራው የታጠቡት ያጥባሉ ከዛም  ጳጳሳት ከዛም ኤጲስ ቆጶሳት ከዛም ቀሳውስት ከዛም ዲያቆናት ከዛም የሚቆርቡ ምህመናን ከዛም ሁሉም ሰው በተራ በተራ ይታጠባል!

አስተጣጠቡ እንዴት መሠላቹ እግራቹህን ሳፋው ውስጥ ታደርጋላቹ ከዛም እግራችሁ ካህኑ ወይም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ጳጳሱ እግራችሁን ያጥባሉ ከዛም እጃችሁን አንዴ አጠብ ከዛም ትገለብጡታላችሁ ከዛም አጠብ  (እንደ መጥረግ ነገር)  ከዛ በቃ እቤት ሄዳቹ መታጠብ የለም በእዛው ውላቹ አድራቹ በማግስቱ አርብ ጠዋት መታጠብ ትችላላቹ!

ይህን የፃፍኩት ግራ እንዳይገባቹ ነው!

ዋናው ነገር ደሞ ሥጋ ወደሙ የተሠጠበት ቀን ነው እና ሥጋ ወደሙ ተቀበሉ ግን አስባችሁበት ትናንትና ሻወር የወሰዳችሁ እናም ፆሙን ከመጀመሪያ የፆማችሁ መሆን አለበ!


መልካም ጸሎተ ሐሙስ ይሁንላችሁ!

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


እኔ እኮ ግርም የምትሉኝ አንባችሁ የምትወጡት ነገር ምን አለበት ሼር ብታደርጉ ለጓደኞቻችሁ ብታሳውቁ ብትረግሩ ? መልሱን ለእናንተ እተዋለሁ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join
1.8K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 07:35:51 ጸሎተ ሐሙስ
ክፍል አስራ ሁለት

በሰሙነ ሕማማት (ሀሙስ) በየሰዓቱ የሚደረገው በጸሎተ ሀሙስ የህጽበተ እግር ሥነ ስርዓት

በጸሎተ ሀሙስ በ፱ ሰዓት የሚደረግ የህጽበተ እግር ሥርዓት:- ማስታወሻ! 6_7 ሰአት ድረስ ቅዳሴ ይገባል ይህን የሚያረጉት ሰአቱን በማጠጋጋት እና ለምዕመናኑ በማሰብ ወደ9 ሰአት አካባቢ እስከ 10 ሰአት ለመጨረስ ይሞከራል!!


ምስባክ ዘህጽበተ እግር


ትነዝኃኒ በአዛብ ወእነጽሕ
ተሐጽበኒ እምበረድ ወእጸዓዱ
ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወሀሴተ

ቄሱ በመጀመሪያ ውኃውን ያቅርብ : ከወንጌል ንባብ በኋላ ቄሱ ውኃውን እንዲህ እያለ ይባርክ:-

ይ.ካ ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አሃዜ ኲሉ ዓለም አምላክነ : ወቡሩክ ወልድ ዋህድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ለመድኃኒተ ዚአነ : ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሒ ለኲልነ : ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።

ይ.ሕ አሜን

ከዚህ በኋላ ቄሱ በታላቅ ድምጽ በዜማ የሚከተለውን ይበል:-

ይ.ካ አሐዱ አብ ቅዱስ : አሐዱ ወልድ ቅዱስ : አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።

ይ.ሕ በአማን አብ ቅዱስ : በአማን ወልድ ቅዱስ : በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።

ይ.ካ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ኲልክሙ አሕዛብ።

ይ.ሕ ወይሴብሕዎ ኲሎሙ ሕዝብ።

ይ.ካ እስመ ጸንዓት ምህረቱ ላዕሌነ።

ይ.ሕ ጽድቁሰ ለእግዚአብሔር ይሄሉ ለዓለም።

ይ.ካ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ይ.ሕ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ይ.ካ ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ካ ወለዓለመ ዓለም አሜን ሃሌ ሉያ።

ከዚህ በኋላ ቄሱ የካህናቱን እግር ይጠብ  ከዚያም የሕዝቡን ሁሉ እግር ይጠብ በመቀጠልም መዘምራኑ የሚከተለውን ክብር ይእቲ ከመዝሙር ፻፶ ጋር አያይዘው ይበሉ:-

ክብር ይእቲ

ሐዋርያቲሁ ከበበ : እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ : ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሀሮም ጥበበ : ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እንዘ ንብል ኢንትኀጎል።

በቁርባን ሰዓት መዘምራኑ የሚከተለውን ይበሉ:-

ዕጣነ ሞገር

ሃሌ ሉያ ሐጸበ እግረ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ አነኒ ሐጸብኩ እገሪክሙ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ።
       
  ምስባኩን እና ንባቡን ቀጥዪ አዘጋጃለሁ....

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join
1.8K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 07:31:06 ዕለተ ሐሙስ
ክፍል አስራ አንድ
 
አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቲዩብ (ቻናል)



ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ መኾኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትናንና ፍቅርን እንደዚሁም የአገልግሎትን ትርጕም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› በመባልም ይጠራል፡፡ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜም፡- «… ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?…
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስኾን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ
ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል፤›› በማለት የእርሱን አርአያነት መከተል እንደሚገባ አስተምሯል (ዮሐ. ፲፫፥፲፪-፳)፡፡


ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ‹‹… ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው
ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው፤
ከእርሱ ጠጡ
፤›› በማለት ምሥጢረ ቍርባንን የመሠረተበት የጀመረበት ቀን በመኾኑ ‹የምሥጢር ቀን› ተብሎም ይጠራል (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱)፡፡ ይኸውም ምእመናን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን፤ ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ አይሁድ ጌታችንን የያዙበት ቀን ስለ ኾነ በዚህ ዕለት በለኆሣሥ (ብዙ የድምፅ ጩኸት ሳይሰማ) የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ መላው ሕዝበ ክርስቲያን የሕጽበት፣ የምሥጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሐ ታጥበው፣ ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአፅንዖት ታዛለች!

አዘጋጅ   ዲያቆን ፍቅረ አብ
ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ



https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join
2.1K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:37:50
በሕማማት የማይፀለዩ ፀሎቶች እንዳሉ ያውቃሉ
አሁኑኑ ገብተው ያንብቡት ለሌሎችም ሼር

➦ ሕማማት መጽሐፍ በPDF

➦ በሕማማት የማይፀለይ ፀሎት አለ?

➦ ለምን አይፀለይም?

➦ ማማተብ ለምን አይቻልም?

➦ መሳሳም ለምን አይቻልም?

➦ በሕማማት ለምን እንሰግዳለን?

➦ ስንሰግድ ምን እያልን እንሰግዳለን?

ሙሉ ትምህርት ስለ ሕማማት

https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
353 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:17:22
በሕማማት የማይፀለዩ ፀሎቶች እንዳሉ ያውቃሉ
አሁኑኑ ገብተው ያንብቡት ለሌሎችም ሼር

➦ ሕማማት መጽሐፍ በPDF

➦ በሕማማት የማይፀለይ ፀሎት አለ?

➦ ለምን አይፀለይም?

➦ ማማተብ ለምን አይቻልም?

➦ መሳሳም ለምን አይቻልም?

➦ በሕማማት ለምን እንሰግዳለን?

➦ ስንሰግድ ምን እያልን እንሰግዳለን?

ሙሉ ትምህርት ስለ ሕማማት

https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
892 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 13:19:07
#ሙሽራው_ዲያቆን


በናዝሬት መካነ ጻድቃን አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነው #ሙሽራው_ዲያቆን_ኤፍሬም_መለሰ_አገኘሁ (ቸሩ)  ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ!


ሙሽራው ዲያቆን ኤፍሬም (ቸሩ) በናዝሬት አዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሙሉ የዲቁና ትምህርቱን ከተማረ ካጠናቀቀ  በኋላ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምስራቅ ሸዋ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ማዕረገ ዲቁናን ተቀብሎ በናዝሬት በመካነ ጻድቃን አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ለዓመታት በዲቁና ሲያገለግል የቆየ እና በትህትናው  የሚያወቀው ወንድማችን ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም 04/08/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አርፏል!


ቀብሩ ሚያዚያ 4 / 2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 በናዝሬት ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ሊቃውንት ካህናት ቀሳውስት ዲያቆናት ጓደኞቹ እና እንደ ዐይኑ ብሌን የሚሳሳላቸው ቤተሰቦቹ በተገኙበት ይፈጸማል!


ለቤተሰቦቹ ለጎደኞቹና ለወዳጆቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን!

ነፍስ ይማር

ዲ/ን ፍቅረ አብ
መጠየቂያ
@Men_Lerdawobot


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube Subscribe በማድረግ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

@seratebtkrstian


አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
@Men_Lerdawobot
2.1K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 21:52:59 ሠላም እደሩ
ዲ/ን ፍቅረ አብ
ናዝሬት አዳማ
ኢትዮጵያ
750 viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 15:39:36 የማክሰኞ ሥርዓተ ሥግደት ተጠናቀቀ... የደከማችሁ እግዚአብሔር ያበርታችሁ!
1.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 11:57:01 የማክሰኞ ቀን 6 ሰዓት ሥርዓት

ክፍል አስር

በመጀመሪያ ስድስት ሰዓት ሲደርስ
ዲያቆኑ ሦስት ጊዜ እየዞረ ቃጭል ያሰማል !
ይህም የሁሉም ዕለታት የጸሎት መጀመርያ ምልክት ነው !(እዚህ ጋ ለምንድነው ቃጭል የሚቃጨለው ?ለሚል ጥያቄ መልስ ነው!)

ከዚህ በኋላ በጋራ ሆነው ጸሎቱን ይጀምሩ !
ካህኑ የአስርቆት ጸሎት ካደረሰ በኋላ
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ይሰጣል! ከዚህ ቀጥለው ሰላም ለኪ ብለው ውዳሴ ማርያም ከአንቀጸ ብርሃን ጋር ይድገሙ !

መልክዓ መልክዓ ማርያምና መልክዓ ኢየሱስ አይደገምም!

ካህኑ ከውዳሴ ማርያም በኋላ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ይሰጣል!

አቡነ ዘበሰማያት ከተሰጠ በኋላ በመሪ እየቀደመ በተመሪ እየተከተለ
ለከ ኃይል ይላሉ መሪና ተመሪ በግራና በቀኝ እየተቀያየሩ ያደርሳሉ!

የለከ ኃይል ጸሎትና ስግደት ካለቀ በኋላ ሕስ 21÷3_17 ይነበባል ከዛም ሢራ 4÷20_31 ይነበባል!ሃይማኖተ አበው ይቤ ቅዱስ አብ ብንያሚ 89÷1_12 ሊቃውንት ቄርሎስ  ዮሐንስ አፈወርቅ ሳዊሮስ ቀለሜንጦስ መጽሐፈ ስንክሳር መጽሐፈ ተአምር

ምንባባቱ ካለቁ በኋላ ምንተኑ አአስየኪ እሴተ ይባልና በሰላመ ገብርኤል መልአክን ሃሌ ሉያ ለአብንና ናሁ አግብርትኪ ከተባለ በኋላ
በአራራይ እንደ ሥርዓቱ መቅድመ ተአምርንና ተአምረ ማርያምን ተአምረ ኢየሱስስን ያንብቡ!

ከተአምረ ኢየሱስ በኋላ ዲያቆኑ ምስባክ ይላል!

ምስባኩም!ይህ ነው!

አድኅነኒ እግዚኦ እምጸርየ
ወአንግፈኒ እምዕለ ቆሙ ላዕሌየ
ወባልሐኒ እምገበርተ ዐመጻ!

ቀጥሎ ካህኑ ወንጌል ያነባል! የዮሐ 8÷12 _20 ቀጥሎ ድኅረ ወንጌል ቀጥሎ ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ መካን ይላል!

በመሪ በኩል አያይዘው ኪርያ ላይሶን ጸሎትና ስግደት እንደ ሥርዓቱ ይደርሳል! ቀጥሎ የሰዓቱ መልክዓ ሕማማት ይደርሳል !

ወንጌል ያነበበ ካህን ድምፁን አሰምቶ አርባ አንድ ጊዜ ኪርያላይሶን እንበል ይላል ! ሕዝቡም ይቆጥራል!

ዲያቆኑ  በዘማ ማኅዘኒ በወርድ ንባብ ሑሩ በሰላም ውስተ አቢያቲክሙ ንዑ ወተጋብኡ በጊዜ...........ሰዓተ ሌሊት(ሰዓተ መዓልት)  ለጸሎት ብሎ ያውጃል (ካህኑም ቢለው ችግር የለውም)

የማክሰኞ 6 ሰዓት ሥርዓተ ስግደት በዚህ ይናቀቃል!

አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join
2.0K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ