Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የሰርጥ አድራሻ: @seratebtkrstian
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.55K
የሰርጥ መግለጫ

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-04-11 10:57:48 በሕማማት የማይፈጸሙ ተግበራት !
             
ክፍል ዘጠኝ

የማይፈጸሙ ተግባራት

መስቀል መሳለም
ጥምቀት መጠመቅ
የፍትሐት ጸሎት
ታቦት ማውጣት
ታቦት ማስገባት
ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ መቀደስ
መሳሳም
መጨባበጥ
ዕልልታና ጭብጨባ
ሥርዓተ ማኅሌት
ከበሮ
ዝማሬ
የኑዛዜ ጸሎት


ይሄ ሕግ ነው አበቃ!

አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join
1.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:40:19 አንዳንድ ሊቃውንት ይህን ይላሉ

#ማክሰኞ_የጥያቄ_ቀን

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ ማቴ. 21፣23-27፣ ማር. 11፣7-35፣ ሉቃ. 21፣23-27፣ ማር. 11፣27-33፣ ሉቃ. 20፣1-8
1.7K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:39:32
ዕለተ ሠሉስ፣ ዕለተ ትምህርት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሠሉስ (ማግሰኞ) ስለ ፍርድ ቀንና ስለ ቤተ መቅደስ መፍረስ ሲያስተምር ውሏል። በወንጌል እንደተጻፈው በማለዳ ሲያልፉ ቅዱስ ጴጥሮስ በዕለተ ሰኑይ የተረገመችው የበለስ ዛፍ ከሥሯ መድረቋን አይቶ “እነሆ የረገምካት በለስ ደርቃለች” አለው። ጌታችንም ከዚህ በመነሳት በዚህች ዕለት ስለ እምነትና ስለ ይቅርታ አስተምሯል። (ማር. ፲፩÷፳-፳፮)
ጌታችን ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች መጥተው ‹‹ከምድራውያን ካህናት አይደለህ፣ ከምድራውያን ነገሥታት ወገን አይደለህ፣ ይህን የምታደርግ በምን ሥልጣን ነው?›› ብለው ጠየቁት፤ እርሱም መልሶ ጠየቃቸው፤ ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነው?›› እነርሱም ከሰማይ እንዳይሉ አያምኑበትም፤ ከምድር እንዳይሉ ሕዝቡን ፈሩና ‹‹አናውቅም›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹እኔም አልነግራችሁም›› ብሎ ረታቸው፡፡
(ማቴ.፳፩፥፲፫-፳፫፣ማር.፲፩፥፳፯፣ሉቃ.፳፥፳፩-፵) ‹‹በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋልና ያዘዟሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ፡፡ ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸውስ እንኳ ሊነኩት አይወዱም›› በማለት እየወቀሰ ተናግሯል፡፡ በዚህም ዕለቱ የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” በማለት እንዳስተማረን በሃይማኖታችን፣ በመንፈሳዊ ሕይወታችንና በሥነ ምግባራችን የጥርጥርና የክፋት ትምህርት ከሚዘሩ ሰዎች ራሳችንን መጠበቅና መጠንቀቅ ይገባናል። (ማቴ.፲፮÷፯)

ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረዥም ትምህርት በማስተማሩ ምክንያት ዕለተ ሠሉስ “የትምህርት ቀን” ይባላል።
1.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:13:23 ወደ አገልግሎቱ ከመግባቴ በፊት እንዴት አደራችሁ? ሠላም አደራችሁ? የት ናችሁ? ምን እያደረጋችሁ ነው? (ቤተ ክርስቲያን ነኝ እየሰገድኩ ነው) የሚል መልስ እጠብቃለሁ!
1.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 22:19:22 መልካም ዜና

የስቅለት አገልግሎት ቀደም ብሎ ይለቀቅልን (post) ይደረግልን ስትሉ ለነበራችሀ ሙሉ አገልግሎት ይኸው ብለናል!

ምስባኮቹ ሙሉ በዜማ

እስመ ቆሙ ሰማዕተ ዓመፃ በዜማ
አገቱኒ ከለባት በዙኃን በዜማ
ቀነውኒ አደውየ ወእገርየ በዜማ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ በዜማ
ግፍኦሙ በዜማ በዜማ
ለመስቀልከ ንሰግድ በዜማ
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ በዜማ
አምንስቲት
በዜማ ወዘተ....














2.7K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 21:47:49 ለዛሬ ብዙ ፕሮግራሞችን አስቤ ነበር ግን ሠው ባሰበበት አይውልምና ባላሠብኩበት ዋልኩኝ እና ምንም post ሳላደርግ ቀረሁ! እግዚአብሔር ከፈቀደ ከነገ ጀምሮ post ለማድረግ እሞክራለሁ!


ሠላም እደሩ
ዲ/ን ፍቅረ አብ
ናዝሬት አዳማ
ኢትዮጵያ
2.8K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 21:30:51
በሕማማት የማይፀለዩ ፀሎቶች እንዳሉ ያውቃሉ
አሁኑኑ ገብተው ያንብቡት ለሌሎችም ሼር

➦ ሕማማት መጽሐፍ በPDF

➦ በሕማማት የማይፀለይ ፀሎት አለ?

➦ ለምን አይፀለይም?

➦ ማማተብ ለምን አይቻልም?

➦ መሳሳም ለምን አይቻልም?

➦ በሕማማት ለምን እንሰግዳለን?

➦ ስንሰግድ ምን እያልን እንሰግዳለን?

ሙሉ ትምህርት ስለ ሕማማት

https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
375 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 20:55:10 ሠላም እደሩ
ዲ/ን ፍቅረ አብ
ናዝሬት አዳማ
ኢትዮጵያ
671 viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 10:57:33 ተፈታቹ?

እኔ ናዝሬት ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተፈትቻለሁ!

እናንተስ የት ተፈታችሁ?
2.1K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 22:02:44 የተከበራችሁ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች እንኳን አደረሳችሁ? እያልኩኝ በየግል እና በbot በኩል እየመጣችሁ ለጠየቃችሁኝ በሙሉ መልስ ይዢ መጥቻለሁ! ከወደ ላይ ባታዩት ነው እንጂ የተጠየቃችሁት በሙሉ ተመልሷል!

ለምሳሌ

ሥለ ሆሳዕና ማብራሪያ!
የሆሳዕና ሥርዓተ ማኅሌት ዋዜማ!
የሆሳዕና ሥርዓተ ሙሉ ማኅሌት በጽሑፍ!
ሥርዓተ ዑደት ሙሉ
ምስባክ
አቡን
ምልጣን
ምዕዋድ
የቅዳሴ አገባብ ሥርዓት
ሙሉ ቅዳሴ ሥርዓት

ከላይ አለላችሁ ወደላይ እዩ!
871 viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ