2023-04-07 22:40:20
#ሥርዓተ_ቅዳሴ_ዘሆሳዕና
ክፍል ስምንት
ሥርዓተ ቅዳሴ አገባቡን በክፍል 6 ተምሰናል ከአሐዱ ጀምሮ እስከ ጸልዩ በእንተ ሠላም ድረስ ተመሣሣይ ነው! ጸልዩ በእንተ ሰላም ብለህ ሰግደህ ወደ መቅደስ ስትገባ የዛኔ ነው ይሄንን ትላለህ
ይ ዲ· · ጸልዩ በእንተ አበዊነ ጳጳሳት ወአበዊነ ኤጲስ ቆጶሳት ወአበዊነ ቀሳውስት ወአኀዊነ ዲያ ቆናት ! ጸልዩ ውሉደ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን በእንተ መሃይምናን ወመሃይምንት !ወካዕበ ጸልዩ በእንተ ደናግል ወመነኮሳት በእ ንተ ደቂቅ ወሕፃናት ወበእንተ ኣዕ ሩግ ወወራዙት ወመዓስባት ቁሙ ሠናየ ቁሙ ከመ ሰላሙ ለእግዚ አብሔር የሃሉ ምስለ ኵልክሙ ።
ካህን ንባብ
ይ ዲ ንነጽር ስነ ስብሐቲሁ
ለአምላክነ!
ካህን ንባብ
ይ ዲ እለ ትነብሩ ተንሥኡ ።
ካህን ንባብ
ይ ዲ ውስተ ጽባሕ ነጽሩ ።
ካህን ንባብ
ይ ሕ: ተዘከረነ ።
ካህን ንባብ
ይ ዲ አውሥኡ
ይ ሕ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ....
ካህን ንባብ
ይ ሕ‧ በከመ ምሕረትከ ፫ተ ጊዜ
ካህን ንባብ
ይ ዲ: አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስት ።
ይሕ ነአምን ......
ካህን ንባብ
#ሥርዓተ_ዑደት_ውስተ_ቤተ_መቅደስ
ካህኑ እያነበበ ወደ ዜማ መለኮቶ አርአየ ብሎ ይቀይረዋል (ዑደተ ሆሳዕና አርአየ) ብሎ መጀመርም ይቻላል! ከዛ ካህኑ ሆሳዕና አአርያምን በዐቢይ ጥዑም ዜማ አዚሞ ሲጨርስ ሕዝብ ይርሱ ያለውን ልክ እንደ እርሱ ይላሉ! በዚህ ሰዓት ሕዝብ በሚል ሰዓት ዑደት አለ! ዑደቱ ሠራዒው ዲያቆን መሥቀልን ይዞ ከፊት ቀጥሎ ንፍቁ ዲያቆን ቃጭል እያቃጨለ ይከተላል ከዛ ሦስተኛው ዲያቆን (ፍሬ ሰሞን ) እርሱ ጧፍ ይዞ (ዘንባባ የሚይዙም አሉ ግን እንደ ለመዳችሁት ሥርዓት በሉ ) በመጨረሻ ንፍቁ ካህን ጽንሐውን ይዞ እያጠነ ዑደት ያደርጋሉ (መንበሩን ይዞሩታል) ከዛም እንዲህ እያሉ 3 ይባላል ይጨረሳል ከዛ ሠራዒው ዲያቆን ወደ ቀደመ ቦታው ተመልሶ ይህን ይላል!
ይ ዲ: በእንተ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ማትያስ ወብፁዕ ወቅዱስ ሊቀ ጳጳስነ አባ እገሌ (የሐገረ ስብከታቹን ሊቀጳጳስ) አባ ቲቶ ወአባ ፊልሞና ወአባ እንድራኒቆስ ወአባ ባስሊቆስ በእንተ እሉ አግብርቲከ አበዊነ ጳጳሳት ወአበዊነ ኤጲስ ቆጶሳት ወአበዊነ ቀሳውስት ወአኃዊነ ዲያቆናት ርቱዓነ ሃይማኖት ። ለእሉ አግብርቲከ መሐሮሙ ለኵሎሙ አዕርፍ ነፍሶሙ ወተሣሃሎሙ! እወ እግዚኦ አምላክነ ኅድግ ሎሙ አበሳሆሙ ወኢትነ ጽር ምግባረ ኃጢአቶሙ እለ ይቀር ቡሂ ለነሢአ ሥጋከ ቅዱስ ወለእለሂ ኢይቀርቡ በትእዛዘ ቃልከሰ ኵሉ ይነጽሕ ። ለእሉኒ ወለኵሎሙ አዕርፍ ነፍ ሶሙ ወተሣሃሎሙ ውስተ ኅፅነ አብርሃም ይስሓቅ ወያዕቆብ ወበእንተ እለ ተድኅራ ውስተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን መሐረነ ለኵልነ ወተሣሃለነ ለዓለመ ዓለም ።
ከዚህ በኋላ ያለው ተመሣሣይ ነው ከተለመደው ቅዳሴ ጋር
አዘጋጅ
ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
join
1.0K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 19:40