Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ሊቃውንት ይህን ይላሉ #ማክሰኞ_የጥያቄ_ቀን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ም | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

አንዳንድ ሊቃውንት ይህን ይላሉ

#ማክሰኞ_የጥያቄ_ቀን

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ ማቴ. 21፣23-27፣ ማር. 11፣7-35፣ ሉቃ. 21፣23-27፣ ማር. 11፣27-33፣ ሉቃ. 20፣1-8