Get Mystery Box with random crypto!

ጸሎተ ሐሙስ #አዘጋጅ_ዲያቆን_ፍቅረ_አብ_ለሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን_ቲዩብ_(ቻናል)_የተዘጋጀ! | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ጸሎተ ሐሙስ


#አዘጋጅ_ዲያቆን_ፍቅረ_አብ_ለሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን_ቲዩብ_(ቻናል)_የተዘጋጀ!



#ጉልባን

ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው

ህፅበተ እግር (እግርን መታጠብ)

እግርን ማጠብ እንግዲህ ያስተማረን ያጠበው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!

ሐዋርያትን (ደቀ መዛሙርቱን) እግራቸውን አጠበ! ትህትናን ሲያስለምረን!

ይህን ድንቅ ትህትና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንዴት ነው?

እግር ማጠቢያ ይዘጋጃል የሚዘጋጀው ከምንድን ነው ?

መልስ

ካህኑ አልባስ እና መጎናፀፊያ ወገቡ ላይ ይጠመጥማሉ ! ከዛም የፀሎት ስርዓቱ ሲያልቅ እርስ በእርሳቸው መጀመሪያ የሚያጥጡት ይታጠባሉ ከዛም ደሞ እኚህን ያጠባቸው በተራው የታጠቡት ያጥባሉ ከዛም  ጳጳሳት ከዛም ኤጲስ ቆጶሳት ከዛም ቀሳውስት ከዛም ዲያቆናት ከዛም የሚቆርቡ ምህመናን ከዛም ሁሉም ሰው በተራ በተራ ይታጠባል!

አስተጣጠቡ እንዴት መሠላቹ እግራቹህን ሳፋው ውስጥ ታደርጋላቹ ከዛም እግራችሁ ካህኑ ወይም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ጳጳሱ እግራችሁን ያጥባሉ ከዛም እጃችሁን አንዴ አጠብ ከዛም ትገለብጡታላችሁ ከዛም አጠብ  (እንደ መጥረግ ነገር)  ከዛ በቃ እቤት ሄዳቹ መታጠብ የለም በእዛው ውላቹ አድራቹ በማግስቱ አርብ ጠዋት መታጠብ ትችላላቹ!

ይህን የፃፍኩት ግራ እንዳይገባቹ ነው!

ዋናው ነገር ደሞ ሥጋ ወደሙ የተሠጠበት ቀን ነው እና ሥጋ ወደሙ ተቀበሉ ግን አስባችሁበት ትናንትና ሻወር የወሰዳችሁ እናም ፆሙን ከመጀመሪያ የፆማችሁ መሆን አለበ!


መልካም ጸሎተ ሐሙስ ይሁንላችሁ!

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


እኔ እኮ ግርም የምትሉኝ አንባችሁ የምትወጡት ነገር ምን አለበት ሼር ብታደርጉ ለጓደኞቻችሁ ብታሳውቁ ብትረግሩ ? መልሱን ለእናንተ እተዋለሁ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join