Get Mystery Box with random crypto!

የማክሰኞ ቀን 6 ሰዓት ሥርዓት ክፍል አስር በመጀመሪያ ስድስት ሰዓት ሲደርስ ዲያቆኑ ሦስት | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የማክሰኞ ቀን 6 ሰዓት ሥርዓት

ክፍል አስር

በመጀመሪያ ስድስት ሰዓት ሲደርስ
ዲያቆኑ ሦስት ጊዜ እየዞረ ቃጭል ያሰማል !
ይህም የሁሉም ዕለታት የጸሎት መጀመርያ ምልክት ነው !(እዚህ ጋ ለምንድነው ቃጭል የሚቃጨለው ?ለሚል ጥያቄ መልስ ነው!)

ከዚህ በኋላ በጋራ ሆነው ጸሎቱን ይጀምሩ !
ካህኑ የአስርቆት ጸሎት ካደረሰ በኋላ
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ይሰጣል! ከዚህ ቀጥለው ሰላም ለኪ ብለው ውዳሴ ማርያም ከአንቀጸ ብርሃን ጋር ይድገሙ !

መልክዓ መልክዓ ማርያምና መልክዓ ኢየሱስ አይደገምም!

ካህኑ ከውዳሴ ማርያም በኋላ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም ብሎ አቡነ ዘበሰማያት ይሰጣል!

አቡነ ዘበሰማያት ከተሰጠ በኋላ በመሪ እየቀደመ በተመሪ እየተከተለ
ለከ ኃይል ይላሉ መሪና ተመሪ በግራና በቀኝ እየተቀያየሩ ያደርሳሉ!

የለከ ኃይል ጸሎትና ስግደት ካለቀ በኋላ ሕስ 21÷3_17 ይነበባል ከዛም ሢራ 4÷20_31 ይነበባል!ሃይማኖተ አበው ይቤ ቅዱስ አብ ብንያሚ 89÷1_12 ሊቃውንት ቄርሎስ  ዮሐንስ አፈወርቅ ሳዊሮስ ቀለሜንጦስ መጽሐፈ ስንክሳር መጽሐፈ ተአምር

ምንባባቱ ካለቁ በኋላ ምንተኑ አአስየኪ እሴተ ይባልና በሰላመ ገብርኤል መልአክን ሃሌ ሉያ ለአብንና ናሁ አግብርትኪ ከተባለ በኋላ
በአራራይ እንደ ሥርዓቱ መቅድመ ተአምርንና ተአምረ ማርያምን ተአምረ ኢየሱስስን ያንብቡ!

ከተአምረ ኢየሱስ በኋላ ዲያቆኑ ምስባክ ይላል!

ምስባኩም!ይህ ነው!

አድኅነኒ እግዚኦ እምጸርየ
ወአንግፈኒ እምዕለ ቆሙ ላዕሌየ
ወባልሐኒ እምገበርተ ዐመጻ!

ቀጥሎ ካህኑ ወንጌል ያነባል! የዮሐ 8÷12 _20 ቀጥሎ ድኅረ ወንጌል ቀጥሎ ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ መካን ይላል!

በመሪ በኩል አያይዘው ኪርያ ላይሶን ጸሎትና ስግደት እንደ ሥርዓቱ ይደርሳል! ቀጥሎ የሰዓቱ መልክዓ ሕማማት ይደርሳል !

ወንጌል ያነበበ ካህን ድምፁን አሰምቶ አርባ አንድ ጊዜ ኪርያላይሶን እንበል ይላል ! ሕዝቡም ይቆጥራል!

ዲያቆኑ  በዘማ ማኅዘኒ በወርድ ንባብ ሑሩ በሰላም ውስተ አቢያቲክሙ ንዑ ወተጋብኡ በጊዜ...........ሰዓተ ሌሊት(ሰዓተ መዓልት)  ለጸሎት ብሎ ያውጃል (ካህኑም ቢለው ችግር የለውም)

የማክሰኞ 6 ሰዓት ሥርዓተ ስግደት በዚህ ይናቀቃል!

አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join