Get Mystery Box with random crypto!

#ሙሽራው_ዲያቆን በናዝሬት መካነ ጻድቃን አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነው #ሙሽ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

#ሙሽራው_ዲያቆን


በናዝሬት መካነ ጻድቃን አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነው #ሙሽራው_ዲያቆን_ኤፍሬም_መለሰ_አገኘሁ (ቸሩ)  ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ!


ሙሽራው ዲያቆን ኤፍሬም (ቸሩ) በናዝሬት አዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሙሉ የዲቁና ትምህርቱን ከተማረ ካጠናቀቀ  በኋላ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምስራቅ ሸዋ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ማዕረገ ዲቁናን ተቀብሎ በናዝሬት በመካነ ጻድቃን አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ለዓመታት በዲቁና ሲያገለግል የቆየ እና በትህትናው  የሚያወቀው ወንድማችን ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም 04/08/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አርፏል!


ቀብሩ ሚያዚያ 4 / 2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 በናዝሬት ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ሊቃውንት ካህናት ቀሳውስት ዲያቆናት ጓደኞቹ እና እንደ ዐይኑ ብሌን የሚሳሳላቸው ቤተሰቦቹ በተገኙበት ይፈጸማል!


ለቤተሰቦቹ ለጎደኞቹና ለወዳጆቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን!

ነፍስ ይማር

ዲ/ን ፍቅረ አብ
መጠየቂያ
@Men_Lerdawobot


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube Subscribe በማድረግ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

@seratebtkrstian


አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
@Men_Lerdawobot