Get Mystery Box with random crypto!

ዕለተ ሐሙስ ክፍል አስራ አንድ   አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቲ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ዕለተ ሐሙስ
ክፍል አስራ አንድ
 
አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቲዩብ (ቻናል)



ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ መኾኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትናንና ፍቅርን እንደዚሁም የአገልግሎትን ትርጕም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› በመባልም ይጠራል፡፡ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜም፡- «… ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?…
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስኾን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ
ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል፤›› በማለት የእርሱን አርአያነት መከተል እንደሚገባ አስተምሯል (ዮሐ. ፲፫፥፲፪-፳)፡፡


ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ‹‹… ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው
ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው፤
ከእርሱ ጠጡ
፤›› በማለት ምሥጢረ ቍርባንን የመሠረተበት የጀመረበት ቀን በመኾኑ ‹የምሥጢር ቀን› ተብሎም ይጠራል (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱)፡፡ ይኸውም ምእመናን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን፤ ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ አይሁድ ጌታችንን የያዙበት ቀን ስለ ኾነ በዚህ ዕለት በለኆሣሥ (ብዙ የድምፅ ጩኸት ሳይሰማ) የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ መላው ሕዝበ ክርስቲያን የሕጽበት፣ የምሥጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሐ ታጥበው፣ ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአፅንዖት ታዛለች!

አዘጋጅ   ዲያቆን ፍቅረ አብ
ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ



https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join