Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-22 18:43:47 #የኔ እይታ 37

የረመዳን ፆም ፈርድ ከተደረገብን(ቡሉግ ከደረስን) ጀምሮ የፆምናቸውን ረመዳኖች እናስባቸው እስኪ.....
ብዙ ጊዜ አኽትመን፣ ብዙ ለሊቶችን ሰግደን፣ ብዙ በእምባ የተሞሉ ዱአወችን አድርገን ነበር አይደል? ግን ዛሬ ላይ የትኛውን ተግባር አስቀጥለነዋል? ብዙወቻችን ረመዳንን የምንገዛ እንጂ አላህን የምንገዛ አንመስልም አይደል?
ሰላት የማይሰግድ ሰው ረመዳን ላይ ይሰግዳል፣ ቁርአን ያልቀራ ሰው ከአሊፍ ይጀምራል፣ በሳምንት አንድ ቀን ጁመአ ሱረቱል-ካህፍን መቅራት የሚከብደው ሰው በአንድ ሳምንት ያኸትማል፣ ሱና ሰላት የሚከብደው ሰው ይጠነክራል፣ ለወራት የተሸከመውን የወንጀል ብዛት ሊያራግፍ በተውበት እምባ ይርሳል፣ የሀራም ፍቅር ውስጥ የሚባክኑ ወጣቶች ረመዳን ሲመጣ ያቆማሉ፤.....
ከዛ ግን ረመዳን ሲያልቅ መስጂዶች ባዶ ከሆኑ፣ ሰላት የጀመረው ሰው ካቆመ፣ ቁርአን መቅራት የጀመሩ ምላሶች ከዘነጉ ፣ልባችን በወንጀል እየጠቆረ ተውበት ከማድረግ ከተቆጠበ፣ የሀራም ግንኙነቶች ከቀጠሉ... የረመዳን ትርፉ ምንድን ነው?
በአላህ ይሁንብን የዘንድሮው ረመዳን ቢያንስ ፈርድ ነገርን ጀምረን የማንተውበት፣ ሀራም ነገርን ካቆምን በኋላ የምንቀጥልበት አይሁን!
ለመስገድ፣ ቁርአን ለመቅራት፣ ሀራም ነገርን ለመተው ስንነይት ለረመዳን ብቻ አይሁን!
በስልካችን ሀራም ነገርን በመመልከት በሽታ የወድቅን ሰወች፣ የሀራም ግንኙነት ውስጥ ያለን ወጣቶች፣ ሰላትን የተውን ሰወች፣ ቁርአንን የረሳን ሰወች ረመዳን ላይ ብቻ ሳይሆን ከዛ በኋላም ላንመለስበት ረመዳንን የመልካም ተግባሮች ልምድ ማስጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አናድርገው!
ረሱል (ሰ ዐ ወ)አንድ ግዜ እንዲህ አሉ"አንተ አብደላህ እንደ እከሌ አትሁን ለይል ሰላት ይሰግድ ነበር ተወው!"በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ የኛ ተጨባጭ ነው።
በሌላ ሀዲስ መልዕክተኛው(ሰ ዐ ወ)" አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስራ ትንሽም ብትሆን ሰውየው ጀምሮ የፀናባት ናት"ማለታቸውን እናስታውስ!
በእርግጥ ሁሉም ኢባዳወቻችን ረመዳን ላይ ከሌላው ቀን የተለዩ ሊሆኑ ይገባል! ወሩ ሸይጣን የሚታሰርበት በመሆኑ ከኢባዳ ከሚያሳንፈን ትልቅ ጠላት አላህ ጠብቆናል ፣ በተጨማሪ ሱና ኢባዳወች በፈርድ ደረጃ የምንመነዳበት በመሆናቸው እና ከእሳት ነፃ የምንባልበት ልዩ VVIP ወር በመሆኑ ከማንኛውም ግዜ የተሻለ አቢድ መሆን ይገባናል! በዛው ልክ የምንሰራው ሀራም ነገርም ከሌላው ጊዜ በበለጠ ስለሚያስቀጣ ልንጠነቀቅ ይገባናል! ይህ ግን ሂወታችን ላይ ለውጥ የሚፈጥረው ከረመዳን በኋላም ማስቀጠል ስንችል ነው ብዬ አምናለው! እንደዛች ፈትሏ ከጠነከረ በኋላ እንዳፈረሰችው ሴት እንዳንሆን ኒያችንን በማሳመር ብንጀምር አትራፊወች እንሆናለን ኢንሻ አላህ!

አላህ ሂወታቸውን ሙሉ የሚቀይር ረመዳን ከሚፆሙ ባሮቹ ያድርገን!

ረመዳን ሙባረክ

rehima hussen

@rehimahu
@rehimahu
ለአስተያየትዎ
@rehimahu
45 viewsGlamor, 15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 13:23:58 ሁሉም በልክ ሲሆን ያምራል
~
ዑለማዎች የተለያዩ ሃሳቦችን ከማንፀባረቃቸው ጋር ሳይወጋገዙ የተላለፉባቸው የፊቅህ ርእሶች ብዙ ናቸው። በመሰል ጉዳዮች ላይ ሆደ ሰፊ ልንሆን ይገባል። በንዲህ አይነት ርእሶች ላይ መለያየትና መተላለፍ ጥንትም የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ሐቅ ነው። የተለያዩ ዓሊሞች ቀርቶ አንድ ዓሊም እንኳ በአንድ ርዕስ ላይ የተለያዩ አቋሞችን የሚያንፀባርቅበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ። ይሄ ብዙ ምሳሌ የመጣበት ጉዳይ ነው።

የዑለማዎችን ትንታኔዎች የሚከተሉ ተማሪዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ፍቅሃዊ አቋሞችን ሊያንፀባርቁ ይችላሉ። ስለሆነም ከስሜታዊ ዝንባሌ እስከተራቀ ድረስ ትላንት "ይፈቀዳል" ያልነውን ጉዳይ ዛሬ "አይፈቀድም" ብንል፣ ዛሬ "ዋጂብ ነው" ያልነውን ነገ "ሙስተሐብ ነው" ብንል የሚያስወቅስም የሚያስገርምም አይደለም። እንዲያውም እንደዚያ ነው መሆን ያለብን። ትላንት ሚዛን የሚደፋ የመሰለን አቋም ከሆነ ጊዜ በኋላ ልክ እንዳልሆነ ከተሰማን "አንዴ ብያለሁ፣ ሰውስ ምን ይለኛል?" አይባልም። ያለ ምንም ማቅማማት ለደረሱበት መረጃ እጅ መስጠት ይገባል። በዚህ መልኩ የሚከሰቱ የአቋም ልዩነቶችን መነሻ አድርጎ ለትችት የሚነሳ ሰው ወይ አላዋቂ ነው። ወይ ደግሞ "በምን ላጥቃ?" እያለ በጉጉት የሚጠብቅ ቂመኛ ነው። አቡ ሐኒፋህ ረሒመሁላህ "እኛ ዛሬ አንድን አቋም እንመርጥና ነገ ከሱ ልንመለስ እንችላለን" ይላሉ።

እንጂ ከስሜት የፀዳ ፍተሻ እስከተደረገ ድረስ በእንዲህ አይነት ሁኔታ የተለያዩ አቋሞችን ማንፀባረቅ የሚወደስ እንጂ የሚወቀስ አይደለም። ባይሆን በውሳኔዎች ላይ ከማስረጃዎች በተቃራኒ ስሜት ወይም ዝንባሌ ዳኛ ሊሆን አይገባም። የፖለቲካ መስመር ይመስል በቡድን መጓዝም አይገባም። በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ ያሉ ማስረጃዎች ፍንትው ያሉ መሆናቸው እየታወቀ አጉል መድረቅረቅ ውስጥ መግባትም አያዋጣም። እንዲሁም መለያየት የማይፈቀድባቸውን መሰረታዊ ጉዳዮችን መሬት ላይ ያለውን መለያየት መነሻ በማድረግ ብቻ እያቃለሉ የኢጅቲሃድ ርእስ ማድረግም ራስን ሸውዶ ሌሎችንም ማታለል ነው የሚሆነው።
ስለዚህ በሁሉም አቅጣጫ በልክ መቆም ይገባል። መተላለፍ በሚቻልበት ጉዳይ "እኛን ካልመሰላችሁ!" እያሉ ማስፈራራት፣ ማጠልሸት፣ አንድነትን መበጥበጥ፣ ህብረትን መናድ አይገባም። ይሄ የብስለት መቅለል ነው። በሌላ በኩል መሰረታዊ የዐቂዳ ጉዳዮችን፣ የማያፈናፍኑ መረጃዎችን በመደፍጠጥ በሐቅ ሂሳብ አንድነትን እናሳካለን ማለትም ዘበት ነው። ይሄ ኢስላማዊ ዐቂዳ ልባቸው ውስጥ የቀለለባቸው ደንታ ቢሶች አካሄድ ነው።
=
Ibnu munewor
24 viewsGlamor, 10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 21:34:16 ለመሄድ የተዘጋጀን ልብ ቻው የማይል ሰውነትን አትገንቡ።
ስለመሄዳቸው የወሰኑ ሰዎችን ሁሉ ያለምንም ግፊት ተሰናበቱ። ቅያሜን በእርቅ ለውጣቹ ለልባቹ እረፍት ስጡ። ነገሮች ረፍደው በቁጭት አለንጋ ከመገረፍ በፊት ያላችሁን ጊዜ ሁሉ በአግባቡ ተጠቀሙ። በመሀላቹ ቅራኔ ወይ መቀያየም ቢኖር እንኳ ቻው ለመባባል ምክንያት አይሁናቹ። ቻው በሉ፣ልባችሁ ያላችሁን ሁሉ በሉ፣በልባችሁ ያለውን ሁሉ ስጡ፣ ተቃቀፉ፣ሻይ ወይ የሆነ ነገር  ጠጡ፣ከቻላቹ ደብዳቤም ፃፉ፣በመሐላቹ የሆነ ማስታወሻ አስቀሩ፣ስለመውደዳችሁ ሳትነግሩ የቁጭት ነገ ሳይመጣ መውደዳችሁን ግልፅ አድርጉ፣የቆዩ ትዝታዎቻችሁን ሁሉ አውሩ፣የትናንትን ዛሬ በምናብ ኑሩት፣የመጨረሻ ጊዜዎቻችሁን ለዚህ ሁነት አውሱት፣ ብቻ ሁሉም ደስ ይላል። ቻው ደስ ይላልም ያሳዝናልም።
ምናልባትም ደግሜ ላላገኘው በምችልበት መልኩ ዛሬ ለመሄድ የወሰነ አንድ ወዳጄን ከአጠገቤ ሸኘው። ማለት እየተዋደዱ መለያየት ውስጥ አንድ ክፉ የሆነ ስሜት አለ። ውስጥን የሚበላ ሆድ የሚያባባ አይነት። እየተዋደዱ ግድ የሆኑ መለያየቶች ከምንም በላይ ይከብዳሉ። ተቀያይሞ ከመራራቅ ይልቅ እየተዋደዱ መለያየት ይከብዳል።
ቢከብድም ቻውን የመሰለ አይነት የለም። ቢያንስ ቢያንስ ከቁጭት ያስጥላል።

(አብድልቃድር ኑር)
18 viewsGlamor, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 20:12:03
ለቆረጠ ተጓዥ
መመለስ ምኑ ነው ለምንስ ይቆጫል
እውነታውን ሲኖር
........ እራሱን ላየበት
ልቅር የሚል ሀሳብ እንዴት ይመነጫል

ይልቅ ....
መሻቱ ጥልቅ ነው ውስጡን ለመከረ
አያፈገፍግም
.... እንደውም ይጓዛል እየጠነከረ

Mekdi
14 viewsGlamor, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 23:13:04
የንጉሱ ወታደር ወድቋል። ሩሁ ከጀሰዱ ተላቃ መሬት ተዘርሯል። ሊያነሳው ማንም አልደፈረም። ሊያድነውም የሞከረ የለም። ግርማዊነታቸው እያለፉ ስለሆነ ስለሱ ነፍስ መጨነቅ ፕሮቶኮል ማበላሸት ሆነ።

በዚያ በአረብ ባህረ ገብ በረሃ ከረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፊት አንድ ሰው እየተንቀጠቀጠ ቆመ።
እሳቸውም እንዲህ አሉት፡- "ንጉሥ አይደለሁምና ሰከን ረጋ በል። እኔ ደረቅ ሥጋ የምትመገበው የቁረይሿ ሴት ልጅ ነኝ"
ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
21 viewsGlamor, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 22:37:11
11 viewsᗰᗴᒍᑎᑌᑎ ●, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:53:44
እኔም ነይታለሁ...!

ዳሩል አርቀም ጀመአ ሰናይ ስራ ሲያመላክተን አያለሁ... እናንተም የበኩላችሁን በማድረግ ከጎናችን ትቆሙ ዘንድ መልካም የሆነ ትብብራችሁን እንፈልጋለንና ⋕challenge ውን በመቀላቀልና የበኩላችሁን ሰደቃ በመስጠት አብራችሁን ሁኑ...!

አካውንት ቁጥር :- 1000451773759

ስለበጎ ትብብራችሁ ጀነት ይመንዳልን!

⎡ ካለኝ በማካፈሌ ቢጨምር እንጂ አይጎድልብኝም⎤

ለበለጠ መረጃና የላካቹበትን ሪሲት ለመላክ @abu_adil1 ላይ ያገኙናል።
11 viewsGlamor, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 21:12:40 ሰሀባዎች የትውልድ ቀዬአቸውን መካን በድል የተቆጣጠሯት እለት ሰፊው የካዕባ ቅጥር ግቢ በሰዎች ተጥለቅልቆ ነበር። ከህዝቡ ትርምስ መሀል ካዕባ በር ላይ ነቢ ሰዐወ ቁመዋል።
#ድል

‹‹ቢላል የት ነው ያለው? ቢላልን ጥሩልኝ›› ነቢ በአይናቸው ያማትራሉ።
ቢላል እስኪጠራላቸው ድረስ ነቢ ሰዐወ ወደ መካ ነዋሪያን እየተመለከቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ፦‹‹ቁረይሾች ሆይ! ወላሂ ቢላልን እዚህ ካዕባ ደጃፍ ላይ ትገርፉት የነበረውን ግርፍያ መቼም አልረሳውም››
#መስዋዕትነት

ቢላል የህዝቡን ትርምስ እያቆራረጠ መጣ። ከነቢ ሰዐወ ፊት ቆመ፦‹‹ቢላል ሆይ! ዛሬ ካንተ ሌላ ማንንም ወደ ካዕባው ውስጥ ይዤ ገብቼ መስገድ አልፈልግም›› ብለው ይዘውት ገቡ።
#ውለታ

ከካዕባው ውስጥ ሰላታቸውን አጠናቅቀው ሲወጡ ነቢ ሰዐወ፦‹‹ቢላል ና እስኪ ከካዕባው ላይ ውጣ›› አሉት።
#የሀበሻ_ክብረት

ቢላል ለመውጣት ሲሞክር የካዕባው ርዝመት አላስመችህ አለቅ። ነቢ ሰዐወ ግራ ቀኝ ሲያማትሩ ዑመርን እና አባ በክርን ተመለከቱ። ቢላልን ሁለትም ተሸክመው እንዲሰቅሉት አዘዟቸው። ቢላልም የሁለቱን ትከሻዎች ረግጦ ከካዕባው ላይ ወጣ።
#ክብር

ቢላል ከካዕባው ላይ ወጥቶ ሲቆም ነቢ ቀና ብለው ተመለከቱት፦‹‹ቢላል! ወላሂ ይህ ካዕባ አላህ ዘንድ እጅግ ክቡር ነው፤ ግና ዛሬ አንተ ከካዕባም በላይ ክቡር ሁነሃል››
#ከፍታ

በብዙ አስርት ሺሆች የሚቆጠሩ ሰሐባዎች ከታች ሁነው ሽቅብ እየተመለከቱት ቢላል ከካዕባው ላይ ሁኖ ታሪካዊ አዛኑን አሰማ። ቢላል የሀባሻን ክብርም ማንም ከማይደርስበት ራቅ አድርጎ ሰቀለውም።
#ኢስላም

Sefwan Sheik Ahmedin
11 viewsGlamor, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:11:23 ዓምር ግብፅን ወደ ኢስላማዊ ግዛት አቅንቶ ግዙፍ መሰጂድ በከተማዋ ለመስራት መምረጥ ጀመረ። መስጂዱ ሊሰራበት ከታሰበው ቦታ አጠገብ በዕድሜ የገፋች የሌላ እምነት ተከታይ ቤት ነበር።
ቤትሽን እንግዛሽ ብለው ብዙ ገንዘብ ቢያቀርቡላትም
አዛውንቷ ግን ፈቃደኛ አልሆነችም። አቋሟን እንደማትቀይር ሲገባቸው ያለ ፈቃዷ በግድ ቤቷን ወደ መስጂድነት አጠቃለሉት።

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

የሐገሩ ቀሳውስቶች በመሪው ውሳኔ በእጅጉ አምርራ እያለቀሰች ቢያይዋት አቤቱታሽን ለበላይ አካል አሰሚ ብለው መከሯት። "መዲና ሂጂ ጉዳዩን ለዑመር ኢብኑል ኸጣብ አቅርቢ ስሞታሽን ንገሪ" አሉ ቀሳውስቱ።
ስንቋን ቋጥራ እቃዋንም ሸክፋ አገልጋይዋን እያስከተለች ከእልህ አስጨራሽ የድካም ጉዞ በኋላ መዲና ደረሰች።
"የመሪያችሁን ቤተመንግሥት አሳዩኝ አሚሩን ለማግኘት ረዥም ርቀት ተጉዤ መጣሁ" አለች ላገኘቻቸው የከተማዋ ነዋሪዎች።

ከአንዲት ዛፍ ስር አሮጌ ጫማውን ተንተርሶ አስራ ሁለት ቦታ በብጣሽ ጨርቅ የተጣፈች ልብስ ለብሶ የተኛውን ሰው አመላከቷት።
ዑመርን ነው እኮ የፈለኩት አለች።
አዎ እሱ ነው ኡመር አሏት።
የዓለምን ግማሽ ምድር የሚያስተዳድር ባለስልጣን እዚያ ዛፍ ስር ተኝቶ ስትመለከት
"ድካሜ ውሃ በላው ይህ ነው ጉዳዬን የሚፈታልኝ?!" አለች ተስፋ በቆረጠ አንደበቷ። ቢሆንም ግን ስሞታዋን ለመናገር ወደ ዑመር ተጠጋችና በእግሯ ነካ አደረገችው። የተሸፈነበትን ስስ ጨርቅ ገለጥ አድርጎ ምን ልርዳሽ? አላት

አንተ ኡመር ነህ?? አለቻቸው
አዎ
በግብፅ የተሾመው መሪ ያደረሰባትን ግፍ በሙሉ ተናገረች። ኡመር ፊታቸው ተለዋወጠ። በንዴት አይናቸው ቀላ። ከአጠገባቸው የወደቀ ነገር አነሱና ደብዳቤ ፃፉ። "ከአሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ለግብፁ አስተዳደር ዓምር ኢብኑል አስ:-
የአላህ ሰላም በአላህ ባሮች ላይ ሁሉ ይስፈን። አምር ሆይ! ፍትህን በማሰፈን የፐርሺያው ንጉስ ከእኛ የተሻለ ሊሆን አይችልም!!!
ሰላም ባንተ ላይ ይስፈን ወስሰላም"
የሚል አጭር ፅሁፍ ፃፉና ይህንን ወስደሽ ለመሪያችሁ ስጪው በማለት አቀበሏት።

በንዴት በገነች። በተስፋ መቁረጥ ተዋጠች። ወደ ሀገሯ ለመመለስ መንገድ ጀመረች። ከከተማው እንደወጣች ደብዳቤ የተፃፈበትን አጥንት ወርውራ ጣለች።
ከኋላዋ ይከተላት የነበረ አገልጋይዋ የወደቀውን መልዕክት አንስቶ በያዘው የከረጢት ቦርሳ ውስጥ አስገባና ተከተላት።

ግብፅ ደረሰች። የእሷ እምነት ተከታዮች የተባለችውን ለመስማት ጓጉተዋል። ምን ተባልሽ በማለት ጠየቋት።
በሆነች አጥንት ስባሪ ደብዳቤ ፅፎ ሰጥቶኝ ነበር ምን ሊፈይድ ብዬ ጣልኳት አለቻቸው።
ቀሳውስቱ ለምን ሲሉ ወቀሷት።
አገልጋይዋ ከቦርሳው አውጥቶ ከመሬት ያነሳውን ደብዳቤ ለቄሶቹ አቀበላቸው።

ቀኑ ጁመዓ ነበር አምር ወደ መስጂድ ሊገባ ከበር ደርሷል። አዛውንቷ ሰባራዋን አጥንት አቀብላው ከፊቱ ቆመ። አነበባት። ፊቱ ተለዋወጠ።
"የጁሙዐን ሰላት እንስገድና መስጂዱ ይፈርሳል። ቤትሽም ይገነባል። እስከምንሰግድ ከታገስሽን መልካም። ካልሆነም ሳንሰግድ እናፈርሰዋለን ፈቃዱ ያንቺ ነው"
አላት።

ጆሮዋን ጠረጠረች። ግርማ ሞገስ የተሞላበት የግብፁ መሪ የዕንባ ቋጠሮው ተፈቶ ማልቀስ ይዟል። ሴትዮዋም ጠየቀች እውነት በዚህ አጥንት ላይ ባለ መልዕክት ነው የተሸነፍከው? ይህ ነው ኢስላም?! ሁኔታው በጣም ገረሟታል። እስልምናን ተቀበለች።
"ቤቴን ለመስጅዱ ወቅፍ ሰጠሰቻለሁ" አለች።
ቀሳውስቱ ሸሀዳን እየነቀሉ አቀርቅረው አነቡ።

ዛሬ ኢትዮጵያ በፍትህ እጦት ድርቅ ትታመሳለች። ሚስኪኖች ይሰቃያሉ። የደካሞች ቤት በጨካኞች ይፈርሳል።
ላባቸውን እያፈሰሱ የሰሩት ቤት ለመናፈሻ እየተባለ በዶዘር ይመነገላል። ደካሞች ያለ መጠለያ ይቀራሉ። የግፍ መሪዎች ለሐብታም መዝናኛ ይገነቡበታል!!

ፍትህን ማየት ከፈለጋችሁ
ኑ ወደ ኢስላም ቤታችሁ
1 viewGlamor, 05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 06:35:32 አንዳንድ ሰው እንደአገር ነው፣ ሲለዩት ሆድ ያስብሳል፣
አንዳንዱ ደግሞ እንደሩሕ ነው፣ ከሱ መለየት ሞት ነው።
ሌላው ደግሞ እንደበሽታ ነው፣ ከሱ መራቅ ሕይወት ነው።

@Reyan_Records
5 viewsᗰᗴᒍᑎᑌᑎ ●, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ