Get Mystery Box with random crypto!

ሰሀባዎች የትውልድ ቀዬአቸውን መካን በድል የተቆጣጠሯት እለት ሰፊው የካዕባ ቅጥር ግቢ በሰዎች ተጥ | Reyan Records

ሰሀባዎች የትውልድ ቀዬአቸውን መካን በድል የተቆጣጠሯት እለት ሰፊው የካዕባ ቅጥር ግቢ በሰዎች ተጥለቅልቆ ነበር። ከህዝቡ ትርምስ መሀል ካዕባ በር ላይ ነቢ ሰዐወ ቁመዋል።
#ድል

‹‹ቢላል የት ነው ያለው? ቢላልን ጥሩልኝ›› ነቢ በአይናቸው ያማትራሉ።
ቢላል እስኪጠራላቸው ድረስ ነቢ ሰዐወ ወደ መካ ነዋሪያን እየተመለከቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ፦‹‹ቁረይሾች ሆይ! ወላሂ ቢላልን እዚህ ካዕባ ደጃፍ ላይ ትገርፉት የነበረውን ግርፍያ መቼም አልረሳውም››
#መስዋዕትነት

ቢላል የህዝቡን ትርምስ እያቆራረጠ መጣ። ከነቢ ሰዐወ ፊት ቆመ፦‹‹ቢላል ሆይ! ዛሬ ካንተ ሌላ ማንንም ወደ ካዕባው ውስጥ ይዤ ገብቼ መስገድ አልፈልግም›› ብለው ይዘውት ገቡ።
#ውለታ

ከካዕባው ውስጥ ሰላታቸውን አጠናቅቀው ሲወጡ ነቢ ሰዐወ፦‹‹ቢላል ና እስኪ ከካዕባው ላይ ውጣ›› አሉት።
#የሀበሻ_ክብረት

ቢላል ለመውጣት ሲሞክር የካዕባው ርዝመት አላስመችህ አለቅ። ነቢ ሰዐወ ግራ ቀኝ ሲያማትሩ ዑመርን እና አባ በክርን ተመለከቱ። ቢላልን ሁለትም ተሸክመው እንዲሰቅሉት አዘዟቸው። ቢላልም የሁለቱን ትከሻዎች ረግጦ ከካዕባው ላይ ወጣ።
#ክብር

ቢላል ከካዕባው ላይ ወጥቶ ሲቆም ነቢ ቀና ብለው ተመለከቱት፦‹‹ቢላል! ወላሂ ይህ ካዕባ አላህ ዘንድ እጅግ ክቡር ነው፤ ግና ዛሬ አንተ ከካዕባም በላይ ክቡር ሁነሃል››
#ከፍታ

በብዙ አስርት ሺሆች የሚቆጠሩ ሰሐባዎች ከታች ሁነው ሽቅብ እየተመለከቱት ቢላል ከካዕባው ላይ ሁኖ ታሪካዊ አዛኑን አሰማ። ቢላል የሀባሻን ክብርም ማንም ከማይደርስበት ራቅ አድርጎ ሰቀለውም።
#ኢስላም

Sefwan Sheik Ahmedin