Get Mystery Box with random crypto!

ዓምር ግብፅን ወደ ኢስላማዊ ግዛት አቅንቶ ግዙፍ መሰጂድ በከተማዋ ለመስራት መምረጥ ጀመረ። መስጂ | Reyan Records

ዓምር ግብፅን ወደ ኢስላማዊ ግዛት አቅንቶ ግዙፍ መሰጂድ በከተማዋ ለመስራት መምረጥ ጀመረ። መስጂዱ ሊሰራበት ከታሰበው ቦታ አጠገብ በዕድሜ የገፋች የሌላ እምነት ተከታይ ቤት ነበር።
ቤትሽን እንግዛሽ ብለው ብዙ ገንዘብ ቢያቀርቡላትም
አዛውንቷ ግን ፈቃደኛ አልሆነችም። አቋሟን እንደማትቀይር ሲገባቸው ያለ ፈቃዷ በግድ ቤቷን ወደ መስጂድነት አጠቃለሉት።

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

የሐገሩ ቀሳውስቶች በመሪው ውሳኔ በእጅጉ አምርራ እያለቀሰች ቢያይዋት አቤቱታሽን ለበላይ አካል አሰሚ ብለው መከሯት። "መዲና ሂጂ ጉዳዩን ለዑመር ኢብኑል ኸጣብ አቅርቢ ስሞታሽን ንገሪ" አሉ ቀሳውስቱ።
ስንቋን ቋጥራ እቃዋንም ሸክፋ አገልጋይዋን እያስከተለች ከእልህ አስጨራሽ የድካም ጉዞ በኋላ መዲና ደረሰች።
"የመሪያችሁን ቤተመንግሥት አሳዩኝ አሚሩን ለማግኘት ረዥም ርቀት ተጉዤ መጣሁ" አለች ላገኘቻቸው የከተማዋ ነዋሪዎች።

ከአንዲት ዛፍ ስር አሮጌ ጫማውን ተንተርሶ አስራ ሁለት ቦታ በብጣሽ ጨርቅ የተጣፈች ልብስ ለብሶ የተኛውን ሰው አመላከቷት።
ዑመርን ነው እኮ የፈለኩት አለች።
አዎ እሱ ነው ኡመር አሏት።
የዓለምን ግማሽ ምድር የሚያስተዳድር ባለስልጣን እዚያ ዛፍ ስር ተኝቶ ስትመለከት
"ድካሜ ውሃ በላው ይህ ነው ጉዳዬን የሚፈታልኝ?!" አለች ተስፋ በቆረጠ አንደበቷ። ቢሆንም ግን ስሞታዋን ለመናገር ወደ ዑመር ተጠጋችና በእግሯ ነካ አደረገችው። የተሸፈነበትን ስስ ጨርቅ ገለጥ አድርጎ ምን ልርዳሽ? አላት

አንተ ኡመር ነህ?? አለቻቸው
አዎ
በግብፅ የተሾመው መሪ ያደረሰባትን ግፍ በሙሉ ተናገረች። ኡመር ፊታቸው ተለዋወጠ። በንዴት አይናቸው ቀላ። ከአጠገባቸው የወደቀ ነገር አነሱና ደብዳቤ ፃፉ። "ከአሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ለግብፁ አስተዳደር ዓምር ኢብኑል አስ:-
የአላህ ሰላም በአላህ ባሮች ላይ ሁሉ ይስፈን። አምር ሆይ! ፍትህን በማሰፈን የፐርሺያው ንጉስ ከእኛ የተሻለ ሊሆን አይችልም!!!
ሰላም ባንተ ላይ ይስፈን ወስሰላም"
የሚል አጭር ፅሁፍ ፃፉና ይህንን ወስደሽ ለመሪያችሁ ስጪው በማለት አቀበሏት።

በንዴት በገነች። በተስፋ መቁረጥ ተዋጠች። ወደ ሀገሯ ለመመለስ መንገድ ጀመረች። ከከተማው እንደወጣች ደብዳቤ የተፃፈበትን አጥንት ወርውራ ጣለች።
ከኋላዋ ይከተላት የነበረ አገልጋይዋ የወደቀውን መልዕክት አንስቶ በያዘው የከረጢት ቦርሳ ውስጥ አስገባና ተከተላት።

ግብፅ ደረሰች። የእሷ እምነት ተከታዮች የተባለችውን ለመስማት ጓጉተዋል። ምን ተባልሽ በማለት ጠየቋት።
በሆነች አጥንት ስባሪ ደብዳቤ ፅፎ ሰጥቶኝ ነበር ምን ሊፈይድ ብዬ ጣልኳት አለቻቸው።
ቀሳውስቱ ለምን ሲሉ ወቀሷት።
አገልጋይዋ ከቦርሳው አውጥቶ ከመሬት ያነሳውን ደብዳቤ ለቄሶቹ አቀበላቸው።

ቀኑ ጁመዓ ነበር አምር ወደ መስጂድ ሊገባ ከበር ደርሷል። አዛውንቷ ሰባራዋን አጥንት አቀብላው ከፊቱ ቆመ። አነበባት። ፊቱ ተለዋወጠ።
"የጁሙዐን ሰላት እንስገድና መስጂዱ ይፈርሳል። ቤትሽም ይገነባል። እስከምንሰግድ ከታገስሽን መልካም። ካልሆነም ሳንሰግድ እናፈርሰዋለን ፈቃዱ ያንቺ ነው"
አላት።

ጆሮዋን ጠረጠረች። ግርማ ሞገስ የተሞላበት የግብፁ መሪ የዕንባ ቋጠሮው ተፈቶ ማልቀስ ይዟል። ሴትዮዋም ጠየቀች እውነት በዚህ አጥንት ላይ ባለ መልዕክት ነው የተሸነፍከው? ይህ ነው ኢስላም?! ሁኔታው በጣም ገረሟታል። እስልምናን ተቀበለች።
"ቤቴን ለመስጅዱ ወቅፍ ሰጠሰቻለሁ" አለች።
ቀሳውስቱ ሸሀዳን እየነቀሉ አቀርቅረው አነቡ።

ዛሬ ኢትዮጵያ በፍትህ እጦት ድርቅ ትታመሳለች። ሚስኪኖች ይሰቃያሉ። የደካሞች ቤት በጨካኞች ይፈርሳል።
ላባቸውን እያፈሰሱ የሰሩት ቤት ለመናፈሻ እየተባለ በዶዘር ይመነገላል። ደካሞች ያለ መጠለያ ይቀራሉ። የግፍ መሪዎች ለሐብታም መዝናኛ ይገነቡበታል!!

ፍትህን ማየት ከፈለጋችሁ
ኑ ወደ ኢስላም ቤታችሁ