Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-05 18:42:32 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑦☞ Dr. Arthur Bertrand  ዶ/ር አርተር በርትራንድ (የፈረንሳይ የሕክምና ሳይንቲስት እና ደራሲ)
“ ትልቅ አላማን በጥቂት የገቢ ምንጭ በመጠቀም አስደናቂ ውጤት ማስገኘት መቻል የሰው ልጅ የላቀ አዕምሮ መለኪያ ሶስት መስፈርቶች ቢሆኑ ማን ነው በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ ያለ ትልቅ የሚወዳደር? አብዛኛዎቹ የታወቁ የሚባሉ ገናና ሰዎች ሰራዊት፣ ህግና ግዛቶችን ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ የመሰረቷቸው ቁሳዊ ሃይሎች ብዙውን ጊዜ አይናቸው ፊት ለፊት ሲፈርሱ ይታያሉ፡፡ ይህ ሰው ያንቀሳቀሰው ሰራዊትን፣ ስነ ህግን፣ ግዛቶችን ፣ህዝቦችን እና ስርወ መንግስታትን ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠር የአለምን አንድ ሦስተኛ ነዋሪ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንበሮችን ጣዖቶችን ሃይማኖቶችን ሃሳቦችን እምነቶችን እና ነፍሶችን የነቀነቀ ነበር….
ለድል ያለው ትዕግስት ፣የጋለ ፍላጎቱ ባጠቃላይ ለአንድ ሃሳብ ነበር፡፡ የንጉሠ ነገሥት ግዛት የመመስረት ፍላጎት አልነበረውም፡፡
Reyan Records
https://t.me/Reyan_Records
43 viewsGlamor, edited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 11:12:15 Semir ami


ብዙ ምርኩዞች... "ድጋፍ ነን" ብለው ሲመፃደቁ፤

መቆም ቻልን ና
ብንለቃቸው...ይሄው ወደቁ፤
7 viewsGlamor, 08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 07:19:16 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑥☞ Alfonso de lamartin አልፎንስ ደ ላማርቲን/ (ፈረንሳዊ ፀሐፊ፣ ገጣሚ፣ በፈረንሳይ አብዮት እና በናፖሊዮን አገዛዝ መካከል የነበረው ‹‹ሁለተኛው ሪፐብሊክ›› መንግሥት እንዲመሠረት ዓይነተኛ ሚና የተጫወተ፣ እንዲሁም የፈረንሳይ ባንዲራ አሁን በሚታወቅበት መልኩ እንዲቀጥል ያደረገ የፖለቲካ ሰው) ‹‹የዓላማ ግዝፈት፣ የማሳኪያ መንገድ ማነስ እና አስገራሚ ድል ለሰው ልጅ ድንቅ ስኬት መለኪያ መሥፈርቶች ከሆኑ በዘመናዊው የዓለም ታሪክ ማነው ደፍሮ ሙሐመድን ከሌላ ጋር ማወዳደር የሚችል? ከሰዎች መካከል ዝነኛነትን የተጎናጸፉትኮ የፈጠሩት መሣሪያን፣ ሕግን እና ግዛትን ብቻ ነው፡፡ ከቁሳዊ ኃይል የዘለለ ስኬት የላቸውም… እርሱም በዓይናቸው ሥር ሲፈረካከስ ያዩት (ጊዜያዊ) ኃይል ነው፡፡… ፈላስፋ፣ አንደበተ ርቱእ፣ ነቢይ፣ ሕግ አውጪ፣ የሐሳብ አስገባሪ፣ የምክንያታዊ እና ምስል አልባ እምነት መልሶ አቋቋሚ፣ የሃያ ምድራዊ እና የአንድ መንፈሳዊ ግዛት መሥራች -ሙሐመድ! የሰው ልጅ ታላቅነት ሊለካባቸው በሚችሉ መሥፈርቶች ብንለካው ‹ከእርሱ የላቀ ሰው አለን?› ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡››
Histoire de la Turquie, Paris 1854, Vol II, pp. 276-77:
https://t.me/Reyan_Records
9 viewsGlamor, edited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 20:48:11
https://t.me/Reyan_Records
13 viewsGlamor, edited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 13:57:58 ሩሖች ከስጋ ሳይዋኃዱ፣ ስጋዎች ከአፈርም ከፍትወት ጠብታም ሳይገነቡ፣ ምድርን ሰፋሪዎች ሳይሰፍሯት ምድር ሳትዋቀር በልዕላነ-አለሙ እንዲህ ሆኖ ነበር።

በሩሆች መከማቻ ስፍራ ህልቆ መሳፍርት ሩሆች ከሚገኙበት መንፈሰ-አለም ውስጥ አላህ 124 ሺህ
ሩሆችን መርጦ ከችሎተ - መለኮት ፊት አቆማቸው።

የዙፋኑ ጌታ ችሎቱን ያስደምጥ ጀመር።

«እናንተ ነብያት ሆይ! ወደ ምድር ወርዳችሁ ከኔ የሚመጡትን ትዕዛዛት ለባሮቼ ለማስተላለፍ መፃሕፍትን እና ጥበብን በሰጠኋችሁ ግዜ ሙሐመድ የተሰኘው ነብይ በእናንተ ዘመን ቢመጣ በሱ አምናችሁ ልትተባበሩትም ትገደዳላችሁ።»

ስፍራው በዝምታ ተውጧል።

የዙፋኑም ባለቤት ንግግሩን ቀጥሏል፦«ተስማምታችኋልን....? አሁን ባልኳችሁም በሙሀመድ ጉዳይ ቃል ኪዳንን ያዛችሁን? »

«ተስማምተናል፤ ታዛዦች ነን» ብለው ለነቢ ደረሳ ለመሆን እጅ ነሱ።
«እንግድያውስ ለመስማማታቹ ማስረጃ ይሆን ዘንድ በነፍሶቻችሁ ላይ መስክሩ፤ እኔም ከመስካሪዎች ነኝ» አለ።

«ነገር ግን...» የዙፋኑ ባለቤት ንግግሩን ቀጠለ።
«ይህን ቃል ኪዳን ከገባችሁ በኋላ ከእናንተ ውስጥ ሙሀመድን ከመታዘዝ የሚያፈነግጥ ካለ እሱ ወራዳ ይሆናል»

ነብያት ቃል ኪዳን ገብተው ሙሀመድንም አልቀው ለመታዘዝ ተስምተው የቃል ኪዳን ስፍራውን ለቀቁ።

ምድር ተዋቅራ ነዋርያኑን ማስተናገድ በጀመረችበት ግዜም ነብያቱ በየተራቸው ይተካኩ ጀመር። ሁሉም ነቢያት ያላዩትን ሙሀመድ ሰዐወ ሲናፍቁ የናፍቆት ጥማቸውን ሳይቆርጡም ዱንያን ተሰናበቱ።

ከሱ በፊት የነበሩትም ሆኑ ከሱ በኋላ የሚመጡ ህዝቦች ሲናፍቁት የሚኖሩለት ክቡር ስብዕና።

ቁጥር ማያካብበው የሰለዋት እና የተብሪካት አይነቶች በመለኮት መአዛ ታውደው እስከ እለተ ቂያማ ድረስ በነቢያቱ ንጉስ ላይ ይሁኑ።
20 viewsGlamor, 10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 07:14:32 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑤☞ Micheal H. Hart /ማይክል ኤች ሃርት/ (አሜሪካዊ የሥነ-ጠፈር ተመራማሪ /አስትሮፊዚስት/፤ The 100: A Ranking of the Most Influential Persons in History (100ዎቹ፡ በሰው ልጅ ታሪክ ተጽእኖ ያሳደሩ ሰዎች በደረጃ) በሚለው መጽሐፉ እውቅና ያገኘ፤ ‹‹በታሪክ ተጽእኖ ያሳደሩ ሰዎችን ደረጃ ስመድብ ሙሐመድን በአንደኝነት ማስቀመጤ ብዙዎችን ሊያስገርም እና ሊያጠራጥር ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እሱ በሃይማኖታዊም ሆነ በዓለማዊ ደረጃ እጅግ በላጭ ስኬት ማስመዝገብ የቻለ ብቸኛ ሰው ነበር፡፡››
The 100: A Ranking of the Most Influential Persons in History, New York: Hart Publishing Company, Inc. 1978, page. 33
https://t.me/Reyan_Records
24 viewsGlamor, edited  04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 19:21:16 ''ቁንጅና ኃጢአት ቢሆን.....አንቺ የፊርደውስ ነበርሽ'' አልኳት   ደስም አላት !
36 viewsᗰᗴᒍᑎᑌᑎ ●, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 18:10:01
https://t.me/Reyan_Records
40 viewsGlamor, edited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 17:04:07
https://t.me/Reyan_Records
36 viewsGlamor, edited  14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 14:45:46 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራስ ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞④☞ አለማችን እንደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያለ ብርሃናማ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች እጅግ በጣም ያስፈልጋታል፡፡ ይህንን
ዘመናዊ ዓለም እንደ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያለ ሰው ቢመራት አለም ካለችበት ችግር መፍትሄ ከመስጠት ባሻገር ሰላምና ደስታ ያጎናጽፋት ነበር” የእንግሊዝ ፀሐፊ ተውኔት ☞George Bernard Shaw (The Genuine Islam; vol 1, No.8 1936)

Reyan Records
https://t.me/Reyan_Records
36 viewsGlamor, edited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ