Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦ ☞⑥☞ Alfonso de l | Reyan Records

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑥☞ Alfonso de lamartin አልፎንስ ደ ላማርቲን/ (ፈረንሳዊ ፀሐፊ፣ ገጣሚ፣ በፈረንሳይ አብዮት እና በናፖሊዮን አገዛዝ መካከል የነበረው ‹‹ሁለተኛው ሪፐብሊክ›› መንግሥት እንዲመሠረት ዓይነተኛ ሚና የተጫወተ፣ እንዲሁም የፈረንሳይ ባንዲራ አሁን በሚታወቅበት መልኩ እንዲቀጥል ያደረገ የፖለቲካ ሰው) ‹‹የዓላማ ግዝፈት፣ የማሳኪያ መንገድ ማነስ እና አስገራሚ ድል ለሰው ልጅ ድንቅ ስኬት መለኪያ መሥፈርቶች ከሆኑ በዘመናዊው የዓለም ታሪክ ማነው ደፍሮ ሙሐመድን ከሌላ ጋር ማወዳደር የሚችል? ከሰዎች መካከል ዝነኛነትን የተጎናጸፉትኮ የፈጠሩት መሣሪያን፣ ሕግን እና ግዛትን ብቻ ነው፡፡ ከቁሳዊ ኃይል የዘለለ ስኬት የላቸውም… እርሱም በዓይናቸው ሥር ሲፈረካከስ ያዩት (ጊዜያዊ) ኃይል ነው፡፡… ፈላስፋ፣ አንደበተ ርቱእ፣ ነቢይ፣ ሕግ አውጪ፣ የሐሳብ አስገባሪ፣ የምክንያታዊ እና ምስል አልባ እምነት መልሶ አቋቋሚ፣ የሃያ ምድራዊ እና የአንድ መንፈሳዊ ግዛት መሥራች -ሙሐመድ! የሰው ልጅ ታላቅነት ሊለካባቸው በሚችሉ መሥፈርቶች ብንለካው ‹ከእርሱ የላቀ ሰው አለን?› ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡››
Histoire de la Turquie, Paris 1854, Vol II, pp. 276-77:
https://t.me/Reyan_Records