Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦ ☞⑦☞ Dr. Arthur B | Reyan Records

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑦☞ Dr. Arthur Bertrand  ዶ/ር አርተር በርትራንድ (የፈረንሳይ የሕክምና ሳይንቲስት እና ደራሲ)
“ ትልቅ አላማን በጥቂት የገቢ ምንጭ በመጠቀም አስደናቂ ውጤት ማስገኘት መቻል የሰው ልጅ የላቀ አዕምሮ መለኪያ ሶስት መስፈርቶች ቢሆኑ ማን ነው በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ ያለ ትልቅ የሚወዳደር? አብዛኛዎቹ የታወቁ የሚባሉ ገናና ሰዎች ሰራዊት፣ ህግና ግዛቶችን ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ የመሰረቷቸው ቁሳዊ ሃይሎች ብዙውን ጊዜ አይናቸው ፊት ለፊት ሲፈርሱ ይታያሉ፡፡ ይህ ሰው ያንቀሳቀሰው ሰራዊትን፣ ስነ ህግን፣ ግዛቶችን ፣ህዝቦችን እና ስርወ መንግስታትን ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠር የአለምን አንድ ሦስተኛ ነዋሪ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንበሮችን ጣዖቶችን ሃይማኖቶችን ሃሳቦችን እምነቶችን እና ነፍሶችን የነቀነቀ ነበር….
ለድል ያለው ትዕግስት ፣የጋለ ፍላጎቱ ባጠቃላይ ለአንድ ሃሳብ ነበር፡፡ የንጉሠ ነገሥት ግዛት የመመስረት ፍላጎት አልነበረውም፡፡
Reyan Records
https://t.me/Reyan_Records