Get Mystery Box with random crypto!

ለመሄድ የተዘጋጀን ልብ ቻው የማይል ሰውነትን አትገንቡ። ስለመሄዳቸው የወሰኑ ሰዎችን ሁሉ ያለምንም | Reyan Records

ለመሄድ የተዘጋጀን ልብ ቻው የማይል ሰውነትን አትገንቡ።
ስለመሄዳቸው የወሰኑ ሰዎችን ሁሉ ያለምንም ግፊት ተሰናበቱ። ቅያሜን በእርቅ ለውጣቹ ለልባቹ እረፍት ስጡ። ነገሮች ረፍደው በቁጭት አለንጋ ከመገረፍ በፊት ያላችሁን ጊዜ ሁሉ በአግባቡ ተጠቀሙ። በመሀላቹ ቅራኔ ወይ መቀያየም ቢኖር እንኳ ቻው ለመባባል ምክንያት አይሁናቹ። ቻው በሉ፣ልባችሁ ያላችሁን ሁሉ በሉ፣በልባችሁ ያለውን ሁሉ ስጡ፣ ተቃቀፉ፣ሻይ ወይ የሆነ ነገር  ጠጡ፣ከቻላቹ ደብዳቤም ፃፉ፣በመሐላቹ የሆነ ማስታወሻ አስቀሩ፣ስለመውደዳችሁ ሳትነግሩ የቁጭት ነገ ሳይመጣ መውደዳችሁን ግልፅ አድርጉ፣የቆዩ ትዝታዎቻችሁን ሁሉ አውሩ፣የትናንትን ዛሬ በምናብ ኑሩት፣የመጨረሻ ጊዜዎቻችሁን ለዚህ ሁነት አውሱት፣ ብቻ ሁሉም ደስ ይላል። ቻው ደስ ይላልም ያሳዝናልም።
ምናልባትም ደግሜ ላላገኘው በምችልበት መልኩ ዛሬ ለመሄድ የወሰነ አንድ ወዳጄን ከአጠገቤ ሸኘው። ማለት እየተዋደዱ መለያየት ውስጥ አንድ ክፉ የሆነ ስሜት አለ። ውስጥን የሚበላ ሆድ የሚያባባ አይነት። እየተዋደዱ ግድ የሆኑ መለያየቶች ከምንም በላይ ይከብዳሉ። ተቀያይሞ ከመራራቅ ይልቅ እየተዋደዱ መለያየት ይከብዳል።
ቢከብድም ቻውን የመሰለ አይነት የለም። ቢያንስ ቢያንስ ከቁጭት ያስጥላል።

(አብድልቃድር ኑር)