Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox1 — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox1 — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
የሰርጥ አድራሻ: @orthodox1
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.52K
የሰርጥ መግለጫ

✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ፅሁፎች ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞
@orthodox1
ሁሉም እንዲያነበው share ያርጉ
ለማንኛውም መረጃዎች ለመጠየቅ @drshaye
ማናገር ይችላሉ
🇪🇹 ✝✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹
Join Us Today And Lets learn Together ✝✝✝
@orthodox1

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-20 19:36:03
የደብረ ዘይትን ሳምንት ለውይይት! 

ሳምንቱን ለተከታታይ ፬ቱ ቀናት እንደ ሥሉስ ቅዱስ መልካም ፈቃድ በተደጋጋሚ ከሚደርሱኝ ጥያቄዎች በተከታዮቹ  ፬ት  ሰንበትን የሚመለከቱ  ጉዳዮች ዙሪያ ከመምህራንና  ከመጻሕፍት ያገኘኋቸውን ጥቂት ሐሳቦች በዝርዝር ሐተታ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።

እስከዛው ግን የሚሰማችሁን ሐሳብና ጥያቄ  ብታሰፍሩ ለመማማር እድሉን እንደሚያሰፋልን እምነቴ ነው።

፩]  ታቦተ ሰንበት
☞ ለሰንበት ታቦት ይቀረጻል?  በሳማ ሰንበት፣ በመናገሻ ጋራው መድኃኔዓለም ፣ በምሑር ኢየሱስ ፣ በአጤ ዋሻ…   «ታቦተ እግዚኣ ለሰንበት» ፣ «ታቦተ ደብረ ዘይዝ» …  መባሉ ስለምን ነው?
      ⚀ ሰኞ መጋቢት ፲፩ በሠርክ የሚመለስ

፪] ሰንበትና ስግደት
☞  «በዕለተ ሰንበት የተከለከለው የጸጋ ስግደት እንጂ የአምልኮ ስግደት አይደለም» በሚል የሚሠጠው የጊዜው ‘ትምህርት’ እንዴት ይታያል ?
       ⚁ ማክሰኞ መጋቢት ፲፪ በሠርክ የሚመለስ

፫] ዕለተ ሰንበት
☞ በክብረ ሰንበት ዙርያ አንዳንዶች ሰንበት ዕለተ ‘ቀዳሚት’ ብቻ ናት ሲሉ  ሌሎች ለክርስቲያኖች ‘እሑድ’ ሰንበት እንጂ ቀዳሚት ሰንበት ምናቸው ናት?   የሚሉ አሉ፤ እኛስ ሁለቱንም በጋራ ለማክበርና ለመዘከር ማስረጃችን ከወዴት የተገኘ ነው?
        ⚂ ረቡዕ መጋቢት ፲፫ በሠርክ የሚመለስ

፬] ተግባረ ሰንበት
☞ የሰንበት ዕረፍት ፣ የሰንበት መብራት ፣ የሰንበት ውኃ … የሚሉት ትውፊቶች በሐዲስ ኪዳን እንዴት ይታያሉ? 
       ⚃ ሐሙስ መጋቢት ፲፬

ምናልባት ተጨማሪ ማየት የሚገባን የሰንበት ጉዳይ ካለ ⚄ ዓርብ መጋቢት ፲፭ ከማጠቃለያ ጋር የምንመለስ ይሆናል!


ኦርቶዶክስ መልስ ናት!  ኦርቶዶክሳዊ መልስ አለው።
199 viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), edited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 05:45:17 ╔​✞═┉✽✥ ✥✽┉═✞╗
❀…#ሥራሽ_ያውጣሽ! …❀
╚✞═┉✽✥ ✥✽┉═✞╝

† ከዚህም በኋላ ተርቢኖስን ሚስትህ የነበርኩ ዕሌኒ እኔ ነኝ አንተ ግን በብረት ሣጥን አድርገህ ወደ ባሕር ስትጥለኝ ዐመፅን ክፋትን የምትሠሪ አንቺ ክፉ ሴት #ሥራሽ_ያውጣሽ [ይከተልሽ]
☞ ሥራሽ መልካም ከሆነ ያድንሽ ክፉ ከሆነ ግን ያጥፋሽ ብለህ ተናገርከኝ ይህንንም እያልክ ከጥልቅ ባሕር ውስጥ ጣልከኝ። ለእኔ ግን ንጹሕ የሆነ ሥራዬ በጎ እውነተኛ ሃይማኖቴ ተከትሎኝ ክብር ይግባውና ፈጣሪዬና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ብዛት አሁን ከአለሁበት ደረጃ ላይ አደረሰኝ አለችው።

† ወእምድኅረዝ ትቤሎ ለተርቢኖስ አነ ይእቲ ዕሌኒ ብእሲትከ አንተሰ እንዘ ትገድፈኒ ውስተ ባሕር ገቢረከ በሣፁን ነበብከኒ እንዘ ትብል ኦ ብእሲት እኪት ገባሪተ ዐመፃ ወእከይ #ዝ_ግብርኪ_ለይትሉኪ ወለእመ ኮነ ሠናየ ያሕዩኪ ወለእመሰ ኮነ እኩየ ያህጕልኪ።
☞ ወዘንተ ቃለ እንዘ ትብል ወገርከኒ ውስተ ባሕር ዕሙቅ። ወሊተሰ ዘተለወኒ ግብርየ ንጹሕ ወምግባርየ ሠናይ ወሃይማኖትየ እሙን አብጽሐኒ ኀበ ዝንቱ ኀበ ሀሎኩ ቦቱ በብዝኀ ኂሩቱ አምላኪየ ወእግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት።
[ድርሳነ መስቀል]
"ወይመጽእ ዳግመ በስብሐት ወበዐቢይ ክብር ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ወይፈድዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ ⇨ ዳግመኛም ፡ በሕያዋንና ፡ በሙታን ፡ ይፈርድ ፡ ዘንድ ፡ በታላቅ ፡ ክብርና ፡ ጌትነት ፡ ይመጣልና ፣ ፡ ለሁሉም ፡ እንደእየ ፡ ሥራው ፡ ይከፍለዋል"
[መጽሐፈ ዲድስቅልያ 30:33]


479 viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 02:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 07:01:40 ይህንን ዝማሬ ተጋበዙ









681 viewsDrshaye Akele, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 10:27:38 ይህች "ቤተ ሳይዳ" ዘይሁዳ ምሣሌቷ ብዙ ኅብር ያለው ነው። ለአብነትም ያህል ምሳሌ፦
፩· ውኃው የቤተ አይሁድ ምሳሌ አምስት መመላለሻ የሕግጋተ ኦሪት የአምስቱ መፃሕፍተ ሙሴ በነዚያ ታጥረው ለመኖራቸው። ቀድሞ የገባባት አንዱ እንዲድን እነሱም አንድነት ቤተ እስራኤል ተሰኝተው ለመኖራቸው ምሳሌ ነው።

፪· በሌላ አገባብ
፠ በዚያ ውኀውን ለማወክ የወረደው መልአክ = ቀሳውስት(ካህናት) "ለቀድሶተ ማየ ጥምቀት" የመውረዳቸው ምሳሌ ነው።
፠ የመጠመቂያ ውኀው = የማየ ጥምቀት ምሳሌ ሲሆን
፠ በቤተ ሳይዳ ያለው አምስቱ እርከን(መመላለሻ) =የአምስቱ አእማደ ምስጢር በዚያ ሊያምኑ ያሉ ተስፈኞችና ያመኑባትም ልጅነትን ያገኙባታልና።
፠ አምስቱ ዓይነት ድውያንም የአምስቱ ጾታ ምዕመናን ከነ ፈተናቸው የተመሳጠረበት ምሳሌ ነው (አእሩግ=በፍቅረ ነዋቅይ....ወራዙት=በዝሙት.... አንስት=በትውዝፍት በምንዝር ጌጥ....ካህናት=በትእቢት አእምሯችን ረቂቅ መዓረጋችን ምጡቅ እያሉ... መነኮሳት=በስስት ምግብን በሹት ጊዜ ባያገኙት ይልቁንም አጽንኦ በአት እየፈቱ በአንሰሐስሖ ዘበከንቱ ይፈትናቸዋል) ምሳሌ ሆኖ ይነገራል።

፫· ለአዲስ ኪዳን ድኅነተ ነፍስ ምስጢራዊ ምሳሌ አገባብም አለው፤
፠ ቤተሳይዳ የበጎች በር በመባልዋ እና በኦሪቱ በጎች ወደ ቤተ መቅደስ ወጥተው ለመስዋዕት ከመቅረባቸው አስቀድሞ የሚታጠቡበት ውኀ ያለበት በመሆኑ ለበአዲስ ኪዳንም የመንፈስ ቅዱስ ልጅነት የሚገኝባትን ወደ አማናዊ መስዋዕት ቅዱስ ቁርባን የምታደርስ የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ
፠ አምስቱን መመላለሻየምታደርስ ደግሞ ወደ ፍፃሜ ሕግ ፍቅረ ቢጽና ፍቅረ እግዚአብሔር አልፎም ፍጽምት ወደሆነች ወደ ሕግጋተ ወንጌልም የምታደርስ የአምስቱ ብኄረ ኦሪት መፃሕፍተ ሙሴ ምሳሌ ያደርጋቸዋል።
፠ ለሁከተ ማይ የወረደው መልአክ የሰማዩ አቃቤ ሥራይ የክርስቶስ ምሳሌ ነው
፠ ከአንድ ብቻ በቀር ሕሙም በአንድ ዕለት አለመዳኑ በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር አምነው ያሉ ምዕመናንና ምዕመናት ብቻ ድኅነተ ነፍስ እናዳላቸው ያሳያል።
፠ የውኀው መናወጽ የሰቃልያነ ክርስቶስ "ሁከተ አይሁድ" ምሳሌ ጥንቱን "ስቅሎ ስቅሎ " የሚለው ያ ቁጣ የዕለተ ዓርብ መድኃኒት መገኛ ነውና።
እስኪ ደግሞ በማጠቃለያው ወደ መፃጉዕ ታሪክ እንመለስና ጥቂት ፍሬ ነገር ለሕይወታችን እንስማ።

ቀድሞ በቤተ ሳይዳ እያለ የነበረበትን ያንን ሁሉ ጭንቅ ኋላ በሊቶስጥሮስ የፍርድ ገበታ ቆሞ በረሳ ጊዜ " ታዲያ ቢያድነኝ በከንቱ መች ሆነና የገዛ አልጋዬን ትቼለት የመጣሁ ለመዳኔ ዋጋ የከፈልኩበት አይደለምን?" እንኳ እንዳይል ያለ ተረፈ ደዌ አንስቶት ያለህን ይዘህ ሂድ እኔ ከአንተ አንዳች አልሻም ባሰኘ ቃል ሸኝቶታል። ግን ታዲያ ይህ ምስኪን መፃጉዕ "ሰው የለኝም" ብሎ የደረሰለትን ሰው ረሳ ማን እንደሆነ እንኳ አላወቀም። ወንጌላዊውም "ዘሐይወ ኢያእመረ ዘአሕየዎ …የዳነውኋላ የተፈወሰው ያዳነውን አላወቀውም" ( ዮሐ.፭፥፲፫) ይለዋል። ያዳነው ማን እንደሆነ ሲጠየቅ ለምሥጋና ያይደለ ለክስ ነበር ስሙን የፈለገው። በኑሮው የማንነቱ መገለጫ "ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ፥ እኔንም ጣለኝ።" ተብሎ ለናቡከደነፆር በነቢዩ እንደተነገረ ያለ ነው (ኤር.፶፩፥፴፬ ) በአገራችንም ካለው ብሂለ አበው "ታሞ የተነሳ ፈጣሪውን ረሳ" የሚለው እንደነዚህ ያሉትን በሚገባ ለመግለጽ የተነገረ ነው። ሊቀ ነቢያት ሙሴን በዘዳግም ፲ ቁጥር ፳፩ ላይ እንዲህ ይላል "ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።" ነገር ግን ይህን ሁሉ ያደረገውን አምላክ ብዙዎች የነበሩ "ህዝበ እስራኤል" ረስተው አሳዝነውት በምድረበዳ በከንቱ ወድቀው ቀሩ .....

ዛሬም

ከደዌው :ከማጣቱ :ከችግሩ: ከሥጋ ኑሮ ጉድለቱ ዳግመኛ ለመታረቅ እንደ መፃጉዕ አምላኩን ያልረሳ ማነው?

ተአምራቱን አይቶ ቃሉን ሰምቶ አምላኩን ያስታወሰስ ማነው " ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠ የሰማስ ማን ነው?" (ኤር. ፳፫፥፲፰) ማንም። ጌታችን ባስተማረው ማሕየዊ ቃሉ ላይ እንኳ ሳይቀር ያመጹትን አይሁድ እስኪ ተመልከቱ " ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር።" ሉቃ ፲፮፥፲፬ እኛንም ቢሆን ከአዳም እስራት ነፃ ያደረገንን አምላክ ውለታ ዘንግተን በቃሉ የምናፌዝ ሁላችንን ወደ ልባችን እንድንመለስ ነቢዩ እንዲህ ሲል ይመክረናል "እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ " ( ኢሳ· ፳፰፥፳፪ ) ይመክረናል።

በፍፃሜ ሕይወቱ በአውደ ምኩናን የሀሰት ክስ የቀረበበትን ይህን የእውነትና የሕይወት ጌታ ቀድሞ ወደ መጠመቂያው እንኳ ለመቅረብ አቅም ያልነበረው ዛሬ ግን አልጋ ለመሸከም በበቃውና ያለ ተረፈ ደዌ በጸናው ኃይሉ የጌታውን ጉንጮች በጥፊ የመምታት ጉልበትና ድፍረት አገኘ። "ዘተሰብሐ ውስተ ገጸ ሙሴ በትስብእቱ ተጸፍአ ገጾ ወተቀስፈ ዘባኖ በእንቲአነ ከመ ይፈጽም ስምዓ ነቢይ ዘይብል መጠውኩ ዘባንየ ለመቅሰፍት ወመላትሕየ ለጽፍአት… በገጹ ነፀብራቅ የሙሴን ፊት ያበራ እርሱ በነቢዩ ጀርባዬን ለግርፋት ጉንጮቼንም ለጽፍአት ሰጠሁ ተብሎ የተነገረውን ለመፈጸም ለእኛ ሲል ፊቱን በጥፊ ተመታ ጀርባውንም ተገረፈ "እንዲል (ሰይፈ ሥላሴ)

አምላከ ምሕረት እግዚአ ለሰንበት ቀድሞ "ዑቅ ኢትአብስ ዳግመ እንከ ከመ ዘየአኪ ኢይርከብከ … ከዚህ የጠናው "ስለ ደዌ ሥጋ ፈንታ ደዌ ነፍስ" እንዳያገኝህ ሁለተኛ እንዳትበድል" (ቁ ፲፬) ያለውን ዘንግቶ ደዌ ዘኃጢአትን ጠርቶ ተወዳጃት፤ በዕለተ ዓርብ የጌታውን ጉንጮች የጸፉች እጁም ደርቃ ሰላ ቀርታለች አንዱ ሊቅ ይህን አልሰማ ባይ መፃጉዕ እና ይቅር ባይ አምላኩን እያደነቀ በጉባዔ ቃናው ይህን ተናገረ

"መፃጉዕ ይትዐረቅ ምስለ ብእሲት ደዌሁ
ሠላሳ አዝማነ እስመ ነበረት ምስሌሁ"

☞ መፃጉዕ ከሚስቱ ከደዌው ይታረቅ
ሠላሳ ዓመት አብራው ኖራለች ሳትርቅ

አብረው አያሌ ዓመታት የኖሩ ባልና ሚስት ሲፋቱ ተነፋፍቀው መለያየቱ እምቢኝ እንደሚላቸውና እንደሚታረቁ ሁሉ ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ተብሎ ሳለ ጌታውን ጸፍቶ መፃጉዕም ዳግመኛ ወደ ፴፰ ዓመት "የአልጋ ወዳጁ" ደዌ መመለሱን የቅኔው ምስጢር ያስተምረናል።

እንግዲህ እኛም በኃጢአት ከሚመጣ ደዌ ተጠብቀን በአባታዊ ምሕረቱ የሚጠብቀንን ቸሩ አምላካችንን እያመሰገንን በቤቱ እንድንጸና መፃጉዕን "ተነሳ" እንዳለው እኛንም ከወደቅንበት ዓራተ ዝንጋኤ፣ ዓራተ ኃጢአት በንስሃ እንዲያነሳንና ዳግም ከመበደልም እንዲጠብቀን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን። አሜን

Яερ๑รтεδ ƒя๑๓ ☞ በቴዎድሮስ በለጠ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ·ም· በጣልያን ሮም የተፃፈ
1.3K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 10:27:37 "ዘሐይወ ኢያእመረ ዘአሕየዎ …የዳነው ያዳነውን አላወቀውም" (ዮሐ. ፭፥፲፫)

የነፍሳችንን ማሠሪያ እንዲፈታና ዓለሙን ከተያዘት የኃጢአት በሽታ እንዲያድን ለቤዛነት፤ እንዲሁም የመልካምና የበጎ ምግባራት ሁሉ አብነት ሆኖ በሥራና በቃል እንዲያስተምር ለአርአያነትም ወዳለንባት ምድር በሥጋ ቅድስት ድንግል ማርያም የወረደው እግዚአ ለሰንበት ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአራተኛው የአቢይ ጾም ሳምንት በመፃጉዕ እሑድ በ"ቤተሳይዳ" የፈጸመውን ተአምራት ቤተክርስቲያናችን ታሰባለች። በዕለቱም በዮሐንስ ወንጌል አምስተኛው ምዕራፍ የተቀመጠው ታሪክ በልዩ ልዩ ኅብረ ምሥጢር ተሰናስሎ በሊቃውንቱ ይነገራል።

መፃጉዕ ተብሎ የደረሰበት ድካመ ሥጋ ጽናት ከሕመም ከበሽታ ከደዌም በላይ መገለጫው የሆነ ሰው ለ፴፰ ዓመት በአልጋው ላይ ሆኖ ምሕረትን ሲጠባበቅባት የኖረባት ስፍራን "ቤተ ሳይዳ" ይላታል።

በቅዱስ መጽሐፍ የሥፍራዎችን ስያሜ ስንመረምር በይሁዳና በገሊላ ለሚገኙ ሁለት የተለያዩ ግዛቶች በተመሳሳይ አገባብ "ቤተ ሳይዳ" የሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸው እናገኛለን:: በሁለቱ አውራጃዎች (ይሁዳና በገሊላ) ሥር "ቤተ ሳይዳ" በሚል የተጠቀሱት ሥፍራዎች በትርጉም ፊደላቱ ያለአገባብ መሰደር ከወለዱት የሞክሼነት ስህተት (Metathetical Corruption) የተገኘ ክፍተት እንጂ ቦታዎቹስ በጥንታዊቷ የእስራኤል ግዛት ከመገኘታቸው ውጪ ምንም የሚያገናኛቸው መልክአ ምድራዊ ኩነት የለም "ጲላጦስ ጰንጤናዊ መልአከ ይሁዳ ወሄሮድስ ንጉሠ ገሊላ" (ሉቃ· ፫፥፩) እንዲል የግዛቶቹ አገረ ገዢዎችም እንዲሁ ለየቅል ነበሩ:: አገባቡን አካቶ ለመረዳት እንዲያመች የሁለቱንም መካናት ከተማና መንደር ለይቶ ማወቁ ተገቢ ነው::

በይሁዳ ግዛት ከሚገኙና እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ገቢረ ተአምራቱን ከፈጸመባቸው ሥፍራዎች ፦ ቤተሳይዳ(Bethesda) ፣ ቢታኒያ ፣ ቤተልሔም ፣ ቤተፋጌ ፣ ኢያሪኮ ፣ ጌቴሰማኒ ፣ ሊቶስጥሮስ(ገበታ) ፣ ኤማሁስ፣ ቀራንዮ(ጎልጎታ) ፣ ኢየሩሳሌም እና የደብረዘይት ተራራ የሚጠቀሱ ሲሆን፤

በገሊላ አውራጃ ደግሞ ፦ ቤተሳይዳ(Bethsaida) ፣ ሄኖን ፣ ቃና፣ ቅፍርናሆም፣ ኮራዚ፣ ጌንሳሬጥ፣ ደብረታቦር፣ ናይን እና የገሊላ ባህር ተገልጸው እናገኛልን::
እነዚህኑ "ቤተ ሳይዳ" ዘይሁዳና "ቤተ ሳይዳ" ዘገሊላ አካባቢያዊ መገኛ ለይተው የሚያመለክቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም በይሁዳ ኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ ያለችዋን "ወቦ ውስተ ኢየሩሳሌም ምጥማቃት ዘጵሩጳጥቄ ቅልንብትራ (ዘውእቱ ቀላየ አባግዕ ብሂል) ወይቤልዋ ስማ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ወባቲ ኃምስቱ ሕዋራት" (ዮሐ ·፭፥፪) ብሎ የገለጠበትንና በገሊላ ስለምትገኘዋ ደግሞ "ወሖሩ እሙንቱሂ ኀበ ፊልጶስ ዘቤተ ሳይዳ ዘገሊላ" (ዮሐ ፲፪፥፳፩) የሚለው ማየት ይቻላል::

በሌላ መልኩ አንዳንዶች ደግሞ በሁለቱም ሥፍራዎች ክርስቶስ አምላካችን ለፈውስ ሥራ ያገኛቸውን ሰዎች አይተው ተመሳሳይ ቦታ ሲመስላቸው ይታያል ይህም "መጻጉዕ" እና "ዕውር" የነበሩትን ማዳኑ ነው:: ይኸውም "ወቦ ውስተ ኢየሩሳሌም ምጥማቃት ዘጵሩጳጥቄ ቅልንብትራ (ዘውእቱ ቀላየ አባግዕ ብሂል) ወይቤልዋ ስማ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ወባቲ ኃምስቱ ሕዋራት …በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። (ዮሐ ·፭፥፪) የተባለውና "ወበጽሑ ቤተ ሳይዳ ወአምጽኡ ኀቤሁ ዕውረ ወአስተብቁዕዎ ይግስሶ … ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ። ዕውርም አመጡለት፥ እንዲዳስሰውም ለመኑት።" (ማር· ፰፥፳፪) የሚለው ነው::


"ቤተ ሳይዳ" ዘገሊላ (Bethsaida) በትርጉም "የማጥመጃ ቤት" የሚል ፍቺ ያለው በተለይ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ አሳ አጥማጆቹ ወንድማማቾችና ቅዱስ ፊልጶስ የነበሩባት መንደር ናት " ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።" (ዮሐ·፩፡፵፭) እንዲል።
፨ "ቤተ ሳይዳ" ዘይሁዳ (Bethesda or Bethchasday) የመጠመቂያ ሥፍራ ስትሆን በግሪኩ ቤተ ዛታ ( Βηθζαθά) ወይም ቅልንብትራ (κολυμβήθρα) እንዲሁም በእብራይስጡና በአረማይኩ "ቤተ`ስዳ" (Beth hesda ( בית חסד /חסדא )) በማለት "ከማጥመጃ ቤት" ለይቶ "ቤተ ሣሕል / የምሕረት ቤት" የሚል ትርጉም ያለው መጠመቂያና መላለሻ መንገድ መሆንዋን ያመለክተናል። የግእዙ መጽሐፍ ቅዱሳችንም ለዚህ በመጨነቅ የቦታውን ስያሜ ከእብራይስጡ "የአንድዮሽ ትርጉም" ስያሜ (ቤተ ሳይዳ) ጋር በግሪኩ ያለውንም መጠሪያ ጭምር አካቶ ቅልንብትራ ( κολυμβήθρα / kolumbethra) ሲል እናገኘዋለን::

ቤተ ሳይዳ ዘይሁዳ ባለ አምስት በር መመላለሻ አምስት ዓይነት ድውያን ፈውስን ከማየ ጥምቀቱ ሲጠባበቁ የሚኖሩባት በአምስተኛው የዮሐንስ ወንጌል ተጽፎ ያለ የጌታችን ማዳን የተገለጠባት ሥፍራ ናት። "እስመ ኦሪት መንፈቀ ፍጻሜ ወኅዳጠ መክፈልት" እንዲላት መልአከ እግዚአብሔር ለቀድሶተ ማይ ወርዶ ውኃውን ሲያናውጥ ቀድሞ የገባ የሚነጻባት በዕለቱ ከአንድ በቀር ለሌላው ፈውስ የማይደገምባት ቦታ ናት ይህችው "ቤተ ሳይዳ" ።

ታዲያ ከእነዚህ መካከል ነበር ይህን ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል የድኅነት ተስፈኛ ሆኖ የኖረ መጻጉዕን በአልጋው ተኝቶ ሳለ ደዌው እንደጠናበት ፈውስ እንደዘገየበት አይቶ "መፈውስ ወማሕየዊ" ጌታችን ቀርቦ አዎን እንዲለው እያወቀ ብወዳችሁ አላዋቂ የሆነ የእናንተን ሥጋ ተዋሕጄ መጣሁላችሁ ሲለን ("አኮ ኢያእሚሮ ኅቡአተ አላ ከመ የሀብ መካነ ለጥንተ ትስብዕቱ ዘኢየአምር ኅቡአተ" እንዲል) ያንን በሽተኛ "ትፈቅድኑ ትሕየው? … ባድንህ ፈቃድህ ነውን?" አለው። የሚገርመው ቅዱስ ጳውሎስ በእብራውያን መልእክቱ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፪ ላይ "የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።" ብሎ የመሰከረለት ጌታችን ፈውስን በመጠባበቅ ከመዳን ውጪ ሌላ ዓላማ ያልነበረውን ይህን ሰው ዓይቶ ፈቃዱን እያወቀ ግን ፍቀድልኝና ላድንህ አለው። " ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? "(መክ ፮፥፲፪) እንዲል የሚያስፈልገንን ሳንነግረው የሚያውቅ የሚሰጠንም ከእርሱ ከፈጣሪው ውጪ በእውነት ማን አለ? መፃጉዕ ግን ኋላ የሚክድ ነውና "በሰንበት ላይ ያመጸ ፣ ራሱን ከአብ የሚያስተካክል ፣ ቤተመቅደሱን አፍርሱት ያለ መች አድነኝ ብየው ሳልፈቅድለት ያዳነኝና አልጋ ያሸከመኝ ነውኮ" ብሎ በዕለተ ዓርብ የሚከስበትን ሲያሳጣውና ለኋላ ጥፋቱ የገዛ ኅሊናው እንዲቀጣው ፈቃዱን ጠየቀው። "አልብየ ሰብእ" ሰው የሌለኝ ሆኖ እንጂ ያንንማ ማን ይጠላል በሚል ጉጉቱን ከወዳጅ አልባነቱ ጋር ድኅነትን ፈቅዶ ገለጠ። እስከ ሁከተ ማይ ሳያቆየው "ተንሥእ ንሣእ ዓራተከ ወሑር … ተንስና አልጋህን አንስተህ ሂድ" አለው ወዲያው አፈፍ ብሎ በፍጥነት ያን ሁሉ ዘመን የተሸከመች ጠንካራ አልጋ ተሸክሟት ሄደ።
1.2K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 10:27:37
1.2K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 02:26:15 + ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ +

"የዚህ ዓለም ኑሮ እንደ እንቅልፍ ነው:: በዚህ ሕይወት የሚሆኑት ሁሉ ሕልም ናቸው::
በሕልምህ ባለጸጋ ብትሆን ምን ጥቅም አለው? በእንቅልፍ ልብ ሆኖ በቅዠት የሚናገር ሰው ስለ ንግግሩ አይፈረድበትም:: እኛ ግን በዚህ የእንቅልፍ ዘመን የምንናገረው ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ሊያሳጣን ይችላል"



"በድህነት እና በረሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ናቸው:: ከድህነት የበለጠ ምን እሳት አለ? ከረሃብስ የሚበልጥ ምን ነበልባል አለ?
ሦስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል:: ለድሆች ምጽዋትን የሚሠጥ ሰው ደግሞ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዚአብሔር መልአክን ይመስለዋል"



"አንድ ሰው እኔ ክርስቲያን ነኝ ሲል በአንድ ቃል ዜግነቱንና ቤተሰቡን ሥራውን ጠቅልሎ ተናገረ ማለት ነው:: የሚያምን ሰው ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም በቀር ምድራዊ ከተማ የለውም"



በትንንሽ ነገሮች ማመስገንን ከለመድህ ትንንሽ ነገሮች ብዙ ስለሆኑ ሕይወትህ ምስጋና ይሆናል"
1.1K viewsDrshaye Akele, 23:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 08:12:51 + ተራ የማይደርሰው ተጠማቂ +

"ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው ሰውዬውም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡ ብሎ መለሰለት" ዮሐ.5:5-7

ይህንን ጥያቄና መልስ ሳይ በሽተኛውን ማናገር ያምረኝና እንዲህ በል ይለኛል :-

አንተ በሽተኛ ግድ የለህም የተጠየቅከውን መልስ:: እመነኝ ጠያቂህ ተራ ጠያቂ አይደለም::
የሚጠይቅህ ሲያደርቁህ እንደኖሩት አሰልቺ ጠያቂዎች አይደለም:: ጥያቄውም የሌሎችን ሰዎች ዓይነት ጥያቄ አይደለም:: ከፊትህ የቆመው የመጠመቂያውን ውኃ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሞላውን ውኃ የፈጠረ ነው::

"ወደ መጠመቂያው የሚያኖረኝ ሰው የለኝም" አልክን? የተጠየቅከውን መልስ እንጂ!
ወደ መጠመቂያው መግባት ትወድዳለህን? ብሎ ማን ጠየቀህ? ተው እንጂ! የጠየቀህ ማን እንደሆነ ባታውቅ እንኩዋን ጥያቄውን በደንብ ስማ::

ሰው የለኝም አትበለው : ስለመጠመቂያው ወረፋ አትንገረው : ስንት ሰው ቀድሞህ እንደዳነ አትቁጠርለት:: የጠየቀህ ግልፅ ጥያቄ ነው::
ልትድን ትወዳለህን?

እግዚአብሔር ፊት ስለ ችግርህ ክብደት ለምን ታወራለህ? ምን እንደሌለህማ እሱም ያውቃል:: አዎን እድን ዘንድ በለው:: ችግርህን ትተህ የምትፈልገውን ንገረው:: የችግርህ መወሳሰብና ሥር መስደድ ለእሱ የሚከብድ አይደለምና መዳን እንደምትሻ ብቻ በእምነት ንገረው የሚል ተግሣፅ በበሽተኛው በኩል ወደ እኛ ደረሰ::



መጻጉዕ (በሽተኛው) ቤተ ሳይዳ ከመጣ 38 ዓመት ሆነው:: ዳዊትና ሰሎሞን 40 40 ዓመት ነግሠው እንኳን ብዙ የምሬት ቅኔ ተቀኝተዋል:: ይህ ሰው አልጋ ላይ ሆኖ አርባ ዓመት ሊሞላው ሲል ምንኛ ተንገሽግሾ ይሆን?

ልብ በሉ ጌታችን በቤተልሔም ሲወለድ ይህ በሽተኛ በአልጋው ላይ ነበረ:: እረኞች ከብዙ መላእክት ጋር ሲዘምሩ እሱ የአንድን መልአክ መውረድና ውኃውን ማናወጥ እየጠበቀ ስድስተኛ ዓመቱን ደፍኖ ነበር:: ጌታችን የሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ደርሶ ወደ መጠመቂያው ሥፍራ ሲመጣም ይህ ሰው አልጋው ላይ ነው:: መጠመቂያዋን 38 ዓመት በተስፋ ሲጠብቅ ቆይቶ ሳይጠመቅባት ቀረ::

ጌታ ሆይ የማይደርሰኝን ወረፋ ከመጠበቅ አድነኝ:: እንድፈወስበት ባልፈቀድክበት ሥፍራ ዕድሜዬን እንዳልጨርስ ጠብቀኝ::

ወደ ሐዲስ ኪዳንዋ ቤተ ሳይዳ ወደ ቤተክርስቲያን ከመጣሁ ብዙ ዘመን አስቆጠርኩኝ:: ግን እስካሁንም ድረስ ከኃጢአት አልጋ ላይ አልወረድሁም:: መነሣት እፈልጋለሁ ግን አቃተኝ:: ልቤ እንጂ እግሬ ጸንቶ መቆም አልቻለም::

ፈረቃ የሌለብህን የሕይወት ውኃ አንተን ሊጠጡ ሲመጡ በዓይኔ እየተቀበልኩ ብዙዎች ጠጥተውህ ሲድኑ በዓይኔ እየሸኘሁ አልጋዬ ላይ ቀረሁ::

እኔ እንደተኛሁ ስንቱ ቀድሞኝ እንደዳነ ባየህልኝ:: ከእኔ በኁዋላ መጥተውስ ከእኔ በፊት ስንቶች ዳኑ?
ስንቱ ከኃጢአት አልጋ በንስሓ ተነሥቶ ያንተን ሥጋና ደም ተቀብሎ ተፈወሰ?

የቤተ ሳይዳው ሐኪም ሆይ ወደ አንጋፋው በሽተኛህ ወደ ጽኑዕ ሕመምተኛህ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ይሆን? ያን ሕመምተኛ "ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበረ" አውቀህ ያናገርከው ሆይ እኔን የምታናግረኝ መቼ ይሆን? እኔስ ብዙ ዘመን እንደሆነኝ አታውቅምን? ሰው የለኝም : ልብ የለኝም : ኃይል የለኝም : አቅም የለኝም ብዬ ብሶቴን የምነግርህ መቼ ይሆን?

"ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ" ዮሐ.5:8-9

አንተ ተነሥ ብለኸው የማይነሣ ማን ነው? እንኳንስ ከአልጋ ከመቃብርም ተነሥ ያልከው ይነሣ የለምን?
ግዴለህም እኔንም ተነሥ በለኝ:: ተነሥ ኃይልን ልበስ ያልከኝ እንደሆነ እንኳንስ "ሸክሜም ቀሊል ነው" ያልከው አንተ ያዘዝከኝ የራሴን ሸክም ቀርቶ የወንድሜን ሸክምም ተሸክሜ የአንተን ሕግ እፈጽማለሁ:: (ገላ. 6:2)



"ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ... ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፡ አለው" ይላል::

በሽተኛው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ እንደሔደ ሳነብ አንድ ነገር ልቤን አስጨነቀው:: ይህ ሰውዬ 38 ዓመት ሙሉ የኖረው በቤተ ሳይዳ ነው:: ክርስቶስ ድንገት ፈውሶት ሒድ ሲለው እሺ ብሎ ከዚያ መጠመቂያ ሥፍራ ከወጣ በኁዋላ ወዴት ሔደ?

የሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛው ሆይ እውነት ወዴት ሔድህ? ከመጠመቂያው መውጣትህን ሰምተን አድንቀናል:: ከዚያስ ወዴት ሔድክ? ዙሪያ ገባው አልተለወጠብህም? መንገድስ አልጠፋብህም?
ወደ ዘመዶች ቤት ሔድክ እንዳልል "ሰው የለኝም" ስትል ሰምቼሃለሁ::

አልጋህንስ የት አደረስካት? መቼም ሰባብረህ እንደማትጥላት የታወቀ ነው:: አልጋ ለታመመ ብቻ ሳይሆን ለጤነኛም ያስፈልጋልና አራት እግር እያላት ጥላህ ያልሔደችውን ዘመድህን መቼም በክብር ማስቀመጥህ አይቀርም::

ለማንኛውም እዚያው ምዕራፍ ላይ ኢየሱስ ይህንን በሽተኛ ዳግም በመቅደስ አገኘው ይላል:: ዮሐ. 5:14 ጌታ ከመጠመቂያ ቦታ አድኖ ያስነሣውን ሰው በመቅደስ ቆሞ አገኘው:: ይህ በሽተኛ እግሩ ሲጸናለት የሔደው ወደ ፈጣሪ ደጅ መሆኑ ያስመሰግነዋል::

ጌታ በመጠጥ ቤት ቢያገኘው ኖሮ ያሳዝን ነበር:: እግርህን ያጸናሁልህ ለዚህ ነው ወይ ብሎ ባዘነበት ነበር:: አሁን ግን ያዳነው ጌታ በመቅደስ አግኝቶት "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" አለው::

ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ክርስቶስ አንተንስ አላዳነህም? "ኸረ እኔ ሽባ ሆኜ አላውቅም:: ማንም እኔን ከአልጋ አላስነሣኝም ትለኝ እንደሆን እመነኝ ክርስቶስ እንደ አንተ ያዳነውስ የለም:: እርሱ እኔና አንተን ተነሡ ብሎ ያስነሣን ከ38 ሳይሆን ከዘላለም የሲኦልና የኃጢአት አልጋ ነው::

እኛን የፈወሰን አልጋችንን አሸክሞ ሳይሆን እሱ ራሱ እኛን ከነአልጋችን ተሸክሞን ነው:: ካላመንከኝ ነቢዩ ኢሳይያስን ጠይቀው "እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ" ሲልህ ትሰማዋለህ:: ኢሳ. 53:12 የእኛን በደል ተሸክሞ ጀርባው ምን ያህል እንደ ቆሰለ ባየህ:: ይህንስ ጀርባዬን ታያለህ የተባለውን ሙሴን ብትጠይቀው ሳይሻል አይቀርም::

ያዳነህ አምላክ አንተንስ የት ነው የሚያገኝህ? እንደዚህ ሰውዬ መቅደስ ያገኝህ ይሆን?

የትም ቢያገኝህ ግን ቃሉ አንድ ነው "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" ከሠላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት የሚብስ ምን ሊመጣ ነው? ካልክስ እሱን ከማየት ይሠውረኝ ብትል ይሻልሃል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 10 2014 ዓ.ም.
ባሕር ዳር ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
1.7K viewsDrshaye Akele, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 08:12:42
1.5K viewsDrshaye Akele, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 12:14:11 ፩. የዛሬዋ ምኩራብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፤

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትባት፤ ሰዎች ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚያገኙባት የሐዲስ ኪዳን ምኩራብ ናት። ጌታችን በቅፍርናሆም ምኩራብ የሕይወት እንጀራ እርሱ ስለመሆኑ ያስተማረበት በዚህ በሦስተኛው ሳምንት በሰፊው ይነገራል። በዘመናችንም ‹‹የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት ይሆናል።›› በሚል የድኾችና የምስኪኖች መጠጊያ እናት ተብላ የተነገረላት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በዘመናችን የንግድ ቤትና የወንበዴዎች ዋሻ ወደ መሆን የተሸጋገረች ትመስላለች። በርካታ ድሆች፣ አረጋውያንና መበለቶች፣ እናት አባት የሌላቸው ሕፃናት፣ ድውያንና አካል ጉዳተኞች በደጇ የወደቁ ቤተ ክርስቲያን የእነዚህን ድሆችና ምስኪኖች ጩኸትና ዋይታ አላየኹም አልሰማውም በሚል የንግድ ቤት ግንባታ ውድድር ውስጥ ገብታለች። በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምግባረ ሠናይ ድርጅትን በማጠናከር ረገድ እጅግ አነስተኛ ነው፤ ሌላው ቀርቶ በደጋጎቹ ነገሥታት የተቋቋሙ ምግባረ ሠናይ ድርጅቶች የሚከታተላቸው አካል በማጣታቸው የፈረሱ አሉ፤ በመፍረስ ላይ የሚገኙም አሉ፤ ለምሳሌ ከመቶ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ጥንታዊው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የአረጋውያንና የእጓለ ማውታ ድርጅት ‹‹አለ›› በማይባልበት ደረጃ እጅግ በመዳከም ላይ ይገኛል፤ ዛሬ የአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ታላላቅ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ገንብተዋል፤ የሚገርመው ሬስቶራንትና ሱፐር ማርኬት እንጂ ግን አንዳቸውም ላይ የምግባረ ሠናይ ተቋም አናገኝም። ይህ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መሄዳችንን ያሳያል፤ እውነቱን ለመናገር ከመቶ ዓመታት በፊት ያሉትን መሪዎችን እንኳን የመውቀስ ሆነ የማወደስም ሞራል የለንም፤ ምክንያቱም በዘረኝነት በነቀዘ በሙስና በቆሸሸ በእኛ አንደበት መወደሳቸው ለእነርሱ ውርደት እንጂ ክብር አይደለምና። እንደ ሕንድና እንደ ግብጽ ያሉ አኃት አብያተ ክርስቲያናትን ተሞክሮ ብንወስድ ለምሳሌ በሕንድ ከ፵፪ በላይ በቤተ ክህነት የሚተዳደሩ የምግባረ ሠናይ ድርጅቶች አሏቸው። በአሁኑ ጊዜ አረጋውያንን የሚጦር እጓለ ማውታ ሕፃናትን ተንከባክቦ የሚያሳድግ ምግባረ ሠናይ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ተጠናክሮ መቀጠል ሲገባው ያሉትን ከማዳከም በላይ ምን ግፍ አለ፤ በተለይ በአንዳንድ አህጉረ ስብከት ያሉ የመምሪያ ኀላፊዎች በሙስና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እየተመቻመቹ ቤተ ክርስቲያን ለምግባረ ሠናይ ብላ ይዛ ያቆየችው ሀብትና መሬት በሌሎች አካላት እንድትነጠቅ ከፍተኛ ደባ ተፈጽሞባታል። የቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ዓላማ መሆን የነበረበት ሕንጻ እየገነቡ ለሆቴልና ለሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ ማከራየት ሳይሆን በሃይማኖታቸው ምክንያት ከቤታቸው ለተገፉ፤ ሃይማኖታችሁን ካለወጣችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ እየተባሉ በገዛ ልጆቻቸው ዛቻ ለሚፈጸምባቸው ከቤታቸው ለተገፈተሩ ጧሪ ቀባሪ ላጡ አረጋውያን መርጃ እንዲሆን ማድረግ ነበር። (ምንጭ ‹‹ሰቆቃወ ቤተ ክርስቲያን›› ታኅሣሥ ፳፻፲፪ ዓም)

ቤተ ክርስቲያን ዙሪያዋን በንግድ ቤትና በሱቆች ተንቆጥቁጣ በገንዘብ ባሕር ውስጥ እየዋኘች፣ ሀብትና ንብረቷ በአስመሳዮች፣ በወንበዴዎች፣ በሙሰኞችና በአጭበርባሪ ነጋዴዎች እየተዘረፈ ባለበት በዚህ ወቅት በደጇ ለወደቁ ድሆችና ምስኪኖች ምእመናኖቿ ከሚጥሉላቸው የሳንቲም ሽርፍራፊ የልብስ እራፊ በስተቀር ቤተ ክርስቲያኒቱ ለእነዚህ ድሆች ዘላቂነት ያለው ሥራ ከመሥራት ይልቅ የመቃብር ሥፍራ እንኳን ሁሉ ሳይቀር እያፈረሰች የንግድ ቤትና ሱቆችን እየገነባችና እያስፋፋች ትገኛለች። ለመሆኑ በከተማችን የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው ለአረጋውያን መጦሪያ፣ ለድኾች መርጃ የሚሆን ተቋም የገነባው። በጣት የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ለትውልድ ማፍሪያ የሚሆን የትምህርት ተቋማት መገንባታቸው እሙን ነው። እነዚህም ቢሆኑ በአብዛኛው በራቸው ክፍት የሚሆነው ኪሳቸው ዳጎስ ላሉት እንጂ ለድሆችና ረዳት ለሌላቸው አይደለም። ሆኖም ግን የቤተ ክርስቲያንን አጥር በንግድ ቤት ከሞሉት እነዚህኞቹ ሳይሻሉ አይቀርም፤ ቢያንስ ትውልድ እየቀረጹ ነውና።
በከተማይቱ እምብርት ባሉ አንዳንድ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የመዝናኛ ስፍራዎችና ጭፈራ ቤቶች እንኳን ለኻያ አራት ሰዓት የማይቋረጥ አገልግሎት በሚሰጡበት በዚህ ዘመን የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ግን እህል ውኃ የማያሰኝ ቆመጥና ነፍጥ ባነገቱ ዘበኞቿ በሯ ከምሽት ሰዓት በኋላ በትላልቅ ሰረገላና መሸጎሪያዎች ተቆልፈው ድሆች ከግቢዋ ተገፍትረው እየወጡ ለሌሊት ብርድና ቁር ተጋልጠው እንዲኖሩ ይፈረድባቸዋል። እናም እነዚህ ድኾችም በሺዎች በሚቆጠር ብር በሚከራዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የንግድ ማዕከላት በረንዳ ላይ ወድቀው ኑሮአቸውን በምሬት ይገፋሉ።
ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ የዘመነ ሐዲስ ምኩራብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላዘነው መጽናናትን ለተጨነቀው መረጋጋትን የምትሰጥ፤ ደስታን የምታስታጥቅ ኀዘንን የምታርቅ እንደሆነች ሲዘምርላት እንዲህ አለ ‹‹በከመ ይቤ እግዚእነ በነቢይ ጊሥዋ ለቤተ ክርስቲያን እስመ ኵሉ ዘጌሠ ኀቤሃ ተአሥዮ ፍሥሐ። ጌታችን በነቢዩ አድሮ እንደተናገረው ቤተ ክርስቲያንን ገሥግሡባት፤ ማልዱባት ወደ እርሷ የገሠገሠውን ደስታ ትሰጠዋለችና›› በማለት ዘወትር ማልደው ወደ እርሷ የሚሄዱ ምእመናን ተጽናንተው ኀይል አግኝተው ተደስተው እንደሚመለሱ ተናግሯል። (ደብረ ዘይት ዘሐሙስ)
ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ
275 viewsDrshaye Akele, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ