Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox1 — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox1 — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
የሰርጥ አድራሻ: @orthodox1
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.52K
የሰርጥ መግለጫ

✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ፅሁፎች ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞
@orthodox1
ሁሉም እንዲያነበው share ያርጉ
ለማንኛውም መረጃዎች ለመጠየቅ @drshaye
ማናገር ይችላሉ
🇪🇹 ✝✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹
Join Us Today And Lets learn Together ✝✝✝
@orthodox1

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-15 16:07:41 «ተውኔተ ጵጵስና ☞ የጵጵስና ጨዋታ»
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥

የኩላዊት ቤተክርስቲያናችንን ትውፊት [παραδοσις] ትምህርት [διδασκαλια] እና እምነት [πιστις] ከመነሻው ስንመለከት በክርስቶስ የተሠጠ በሐዋርያት የተሰበከና በአበው የተጠበቀ መንገድ ነው። በዚህም ቤተክርስቲያን ተመሠረተች!【ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ】

በቀደመው ዘመንማ የገሃዱ ሢመት ቀርቶ የሕጻናቱ ተውኔት እንኳ ደርዝ ነበረው!

በክርስትና ማኅተም ያልከበርክ
እንዴት ለጵጵስና ተመረጥክ? 【አባ ጊዮርጊስ】

ዛሬ ግንቦት ፯ ቀን በሃይማኖት የተዋቀረ ፦ የማይናወጥ መሠረት፣ የማይፈርስ ግድግዳ ፣ የማያዘነብል ምሰሶ የተባለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፳ኛው የኢትዮጵያና የግብፅ ፓትርያርክ በ፬፻፸፬ ዓ.ም. ከሥጋ ድካም ያረፈበትን ቀን ቤተክርስቲያናችን ትዘክራለች። ይህ የምሥጢር ምንጭ የጉባኤ ኒቅያ አፈ ጉባኤ ደገኛው መምህር ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ለ፵፯ ዓመት በፕትርክና ሲቆይ ሢሦውን 【፲፭ ዓመት】በስደት ነበር ያሳለፈው።

ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያውን ጳጳስ ቅዱስ ፍሬምናጦስን【አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን】የሾመልን ባለውለታችንና በመንበረ ማርቆስ የተቀመጠ ፳ኛው ፓትርያርካችን ነው። («ወማርቆስ ወንጌላዊ ‘ወኮነ ሰባኬ ወመጥምቀ ወሠያሜ ካህናት’ በእስክንድርያ ወግብፅ ወኖባ ወምድረ ኢትዮጵያ እስከ ጽንፋ» እንዲል መጽሐፈ ግጽው ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፩ )

ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ክርስትናው የመጣበትና ለጵጵስና የበቃበት መንገድ እጅጉን የሚደንቅና አስተማሪ ነው። ስንክሳራችን በቀደመ ሕይወቱ ከአረማውያን ቤተሰብ የተገኘ አረማዊ እንደነበርና ለመጠራቱ ምክንያት ስለሆነች «የጵጵስና ጨዋታ» እንዲህ እያለ ይነግረናል

ውእቱ ይነብር ምስለ ሕፃናት እለ ይትሜህሩ ኀበ መምህር ርእዮሙ ለእሙንቱ ውሉደ ክርስቲያን እንዘ ይገብሩ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ወይትዋነዩ በበይናቲሆሙ ወይረስዩ እምኔሆሙ ዲያቆናተ ወኤጲስ ቆጶሳተ አደሞ ተላህዮቶሙ። ሰአሎሙ ዝንቱ አብ ለውሉደ ክርስቲያን ከመ ይሳተፍ ምስሌሆሙ በተላህዮቶሙ። ወከልእዎ ወይቤልዎ እስመ አንተ አረማዊ ኢንዴመር ምስሌከ ወይቤሎሙ ውእቱ አነ እከውን ክርስቲያናዌ ወተፈሥሑ ቦቱ።

【 እርሱም ከመምህር ከሚማሩ ሕፃናት ጋራ እያለ እርስ በርሳቸው በመጫወት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየሠሩ ከእነርሱ ውስጥ ዲያቆናትን ኤጲስ ቆጶሳትንም ሲያደርጉ እሊያን የክርስቲ ያንን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው ደስ ስለአለው ከእሳቸው ጋራ በጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው። እነርሱም አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም ብለው ከለከሉት እርሱም ክርስቲያን እሆናለሁ አላቸው እነርሱም ደስ ተሰኙበት።】

ወነሥእዎ አሜሃ ወረሰይዎ አምሳለ ሊቀ ጳጳሳት ወመትሕቲሁ አምሳለ መንበር። ወእኀዙ ይስግዱ ሎቱ ወበውእቱ ጊዜ ኀለፈ አባ እለእስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት። ወሶበ ርእዮሙ ለውሉደ ክርስቲያን እንዘ ይትዋነዩ ይቤሎሙ ለእለ ሀለዉ ምስሌሁ ወለዎ ለዝንቱ ሕፃን ይሠየም ሢመተ ክብርተ ወልዕልተ።
【ያን ጊዜም ወስደው በሊቀ ጳጳሳት አምሳል አደረጉት ከበታቹም ወንበር አድርገው ይሰግዱለት ጀመር። በዚያን ጊዜም ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ በዚያ አለፈ የክርስቲያን ልጆች ሲጫወቱ በአያቸው ጊዜ አብረውት ላሉ ይህ ሕፃን ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች ሹመትን ይሾም ዘንድ አለው አላቸው።】

ወንድማለም እንግዲህ ስማ መሾም ስለምትፈልግ ብቻ አትሾምም! እንኳን ሢመቱ ጭውውቱም ቢሆን ሥርዓት አለው። እንዳየኸው ጥንቱን የገሃዱ ሢመት ቀርቶ የሕጻናቱ ተውኔት እንኳ ደርዝ ነበረው! መጽሐፉም ቢሆን እንኳን ራስህን በቦታው ልታስቀምጥ በቦታው ተቀመጥ እንኳ ቢሉህ እምቢኝ በል ነው የሚል።
【"ኢመፍትው ለመኑሂ እምሰብእ ይምሥጥ ሢመተ ክህነት ለርእሱ አላ ለእመ ተውህበ እምእግዚአብሔር ☞ #የክህነትን_ሹመት ከእግዚአብሔር ካልተሠጠው በቀር ከሰው ወገን ማንም ለራሱ ይገባኛል ብሎ ቀምቶ እጅ አያድርጋት" መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ ፩፥፷፩】

ዛሬ የሕጻናቱን ያኽል ድፍረት አጥተን መሰል እምነት የሌለው ኢጥሙቅ ልብሰ ጵጵስና ለብሶ ሲተውን አይተን ዝም ከማለት አለፍንና በበር ያልገቡ «መስኮተኞች» አይደለም ጵጵስናው ፕትርክናውም ሳይቀር ይገባናል ሲሉ እየሰማን «ሃይ–ባይ» አለመገኘቱ በእጅጉ ያሳዝናል። «ኧረ ተዉ» የሚል መገስጽ ብቅ ሲል ተቆጪውን መቆጣት ከመንገድ ማጥፋት ሥራችን ሆኖ አረፍነው።

ኧረ ጉድ የዚያ ዘመን የእስክንድርያ ሕጻናት እንዴት አድርገው እንደሚበልጡን እዩልኝማ

«ሰአሎሙ ዝንቱ አብ ለውሉደ ክርስቲያን ከመ ይሳተፍ ምስሌሆሙ በተላህዮቶሙ። ወከልእዎ ወይቤልዎ እስመ አንተ አረማዊ ኢንዴመር ምስሌከ ☞ #እሊያን_የክርስቲያን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው ደስ ስለአለው ከእነርሱ ጋራ በጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው። እነርሱም አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም ብለው ከለከሉት »

እንዲህ ያለውን ጨዋታ ወዳጅ ፡ አልፎ ሂያጅ «ና ግባና ጰጵስ» ለሚሉ ድንበር አፍራሾች እንዲህ ባለው የሌባ መንገድ እንዳልመጣ የምናውቀው ራሱ ቅዱስ አትናቴዎስ በድርሳኑ "ንሕነሰ ኢንኌልቆ ምስለ ክርስቲያን አላ ምስለ አረሚ ወዐላውያን ☞ እኛ ግን እንዲህ ያለውን ከማያምኑና ከሚያምጹት እንጂ ከክርስቲያን ወገን እንኳ አንቆጥረውም!” እያለ ይዘልፋል 【ሃይ አበው ፳፱፥፲፭】

አባ ጊዮርጊስ የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታና የእግዚአብሔር ምርጫ የሆነውን ሹመት በራሱ ጳጳስ ነኝ ይገባኛል ለሚል ንሥጥሮሳዊ በላከው ተግሳጽ ይህን ይላል ፦

እፎ ተኀረይከ ለጵጵስና ?
ዘኢተቀደስከ በማኅተመ ክርስትና
እፎ ተኀረይከ ለተክህኖ ?
ዘኢተሠርጎከ በተአምኖ
【በክርስትና ማኅተም ያልከበርህ ለጵጵስና እንዴት ተመረጥህ፡ በመታመን ያልተሸለምህ ሆይ እንደ ምን ለክህነት አገልግሎት ተመረጥህ ?】
【መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፮】

«ወአንተሰ ተመሰልከ ተክለ ዘእንበለ ፍሬ: ወዖመ ዘእንበለ ቈጽል: ፈለገ ዘእንበለ ውሒዝ : ወዐዘቅተ ዘእንበለ ማይ፡ ንጉሠ ዘእንበለ ጌራ መንግሥት : ሐራዌ ዘእንበለ ንዋየ ሐቅል : ደመና ዘእንበለ ዝናም : ወሰዊተ ዘእንበለ መስበልት : አበ ዘእንበለ ሀብተ ሲሳይ : ወእመ ዘእንበለ አጥባት : ንድቀ ዘእንበለ ተድባብ : ወኆኅተ ዘእንበለ ማዕፆ : መርዓዌ ዘእንበለ አክሊል : ወመርዓተ ዘእንበለ ባዝግና : ካህነ ዘእንበለ ኤፉድ : ምሥዋዐ ዘእንበለ ቊርባን : ኖትያዌ ዘእንበለ ሥርዐተ ሐመር : ወምሥያጣዌ ዘእንበለ ንዋይ : ሠረገላዌ ዘእንበለ ድርዐ ሐጺን : ወፈረሳዌ ዘእንበለ ኲያንው! እፎ ተኀረይከ ለጵጵስና ? ዘኢተቀደስከ በማኅተመ ክርስትና ፣ እፎ ተኀረይከ ለተክህኖ ? ዘኢተሠርጎከ በተአምኖ »
1.0K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 16:05:45
1.0K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 10:38:26
https://t.me/joinchat/AAAAAEILHwyFiBuqHNVyRw
1.6K viewsDrshaye Akele, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 10:37:38 #መፆር_እምዕፀወ_ሊባኖስ (የሊባኖስ እንጨቶች ዙፋን ) ቅድስት ድንግል ማርያም!

በወንጌል "ዕፅ ሰናይ ፍሬ ሰናየ ይፈሪ" (ማቴ ፯፥፲፯) እንዳለው ከመልካም ዛፍ ቤተሰብ የተኘች ምግባረ መልካም ደምግባተ ቀና፣ የሊባኖሷ ብላቴና አማናዊት መፆር (ዙፋን) እግዝእትነ ማርያም ናት! እርሷ ፆረቶ በከርሳ ፣ፆረቶ ዲበ ዘባና ፆረቶ ዘኢይፀወር እያሉ ሊቃውንቱ የሚያወድሷት ለአምጻኤ ዓለማት መፆሩ ፣ ለመጋቤ ዓለማት አገሩ ፣ ለአኅላፌ ዓለማት መንበሩ ናት!

♧ በሰቆቃ ወድንግል "አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ። … ናዝሬት ሀገሩ አብሪ አብሪ ከዙፋኑ ማርያም ጋር ንጉስሽ ወዳንቺ ደርሷልና" ተብላለች፤

♧ በሰአታቱ ገነይነ ለኪ እና ኵሎሙ ዘእግዝእትነ ምስጋናው አፈ ሊቃውንት አባ ጊዮርጊስ
♢ "ሐዳስ መቅደስ መፆረ ንጉሥ። ወላዲቱ ለኢየሱስ።… አዲሲቷ መቅደስ የንጉስ ዙፋኑ ለኢየሱስ ወላዲቱ " ብሏታል፤
♢ "አንቲ ውእቱ ለንጉሠ ነገሥት መፆሩ ለአዳም ተድላ መንበሩ ብኪ ተመይጠ ኅበ ዘቀዳሚ ማኅደሩ።… ለነገሥታቱ ንጉሥ ዙፋኑ ፣ ለአዳም ወደቀደመ ማደሪያው መመለሻ የደስታው ማረፊያ አንቺ ነሽ" ሲል ይገልጣታል፤

♧ የተአምረ ማርያማችን መቅድም "አልቦ ዘፆረ እሳተ ወአልቦ ዘኢገብረ ኅጢአተ እንበለ እግዝእትነ ማርያም። … ከእመቤታችን በቀር ኀጢአትን ያልሠራ ለእሳት ዙፋን የሆነ የለም " ይለናል

♧ ውዳሴ ማርያም ከአንቀጸ ብርሃንና ከቅዳሴው ጋር በምስጢር እየተሳሰረ "ማዕጠንት ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት … የእሳተ መለኮት ዙፋን የወርቅ ማዕጠንት" ይላታል።

♧ የመልክአ ቁርባን ምስጋናም "ናዛዝትነ እምኃዘን ወኃይለ ውርዙትነ እምርስዓን በማኅፀንኪ ተፀውረ ብሉየ መዋዕል ሕፃን።… ከሃዘን የምታረጋጋ መጽናኛችነን፣ ከድካም የምታበረታን የወጣትነት ኃይላችን ፣ ዘመኑ ጥንት የሆነው ሕፃን ማኅፀንሽን ዙፋን አድርጎ አደረ" እንላታለን።

#መፆረ_ገብረ_ለርእሱ (ለራሱ ዙፋን ሰራ)

ይህንን በመሰለው ምሥጢር ውስጥ የተገለጡ ሁለት ፍሬ ነገሮችን እንመርምር

፩ ለራሱ ዙፋኑን የሠራት ራሱ ነው!

ይችን ወላዲተ ቃል መሠረተ ንጽሕ ድንግል
በዚህም በአባት ዘር ከሚመጣ ቁራኝነት በእናት ደም ከሚያርፍ የመርገም ጽነት ለይቶ እኩያት ፍትወታት ኀጣውእ ሳይደርሱባት ራሱ ሠራት ቅዱስ ያሬድ "ማርያምሰ ተሐቱ ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀዓዳ … ማርያምስ በአዳም ገላ ውስጥ እንደ ነጭ እንቁ ታበራ ነበር " እንዳላት
ቅድስናዋ የመመረጥ አንድም እንድትመረጥ ሆና በተገባ ለመገኘት ጽናት ያለበት ነውና! ሊቁ "አቀባ መንፈስ ቅዱስ እምከርሰ እማ" ያለውን እንዲህ አብራርቶታል "የበጎ ዕድል ፈንታ ጽዋ ተርታ የሚሆን እግዚአብሔር ብዙ ስጦታ ከብዞች መናፍስት የሚቀዳ አይደለም ካንድ መንፈስ ነው እንጂ የክፉ ዕድል ፈንታ ግን የሚገኝ ከሰይጣን ነው፡ እንዳትበድል ድንግልን ከናቷ ሆድ ጀምሮ የጠበቃት መንፈስ ቅዱስ እንዳትረክስም ያነጻት ለወልድ ዋህድም ማደሪያ ያደረጋት እርሱ ነው፡፡ አብ ወደዳት ወልድ ከርሷ ሥጋ ለበሰ መንፈስ ቅዱስ ጋረዳት፡፡ "

፪ ራሱ የሠራት ለራሱ ዙፋንነት ነው!

ይኽችን የንጉሥ ዙፋን የአብ ሙሽራ (መርዓቱ) ፣ የወልድ እናት (ወላዲቱ)፣ የመንፈስ ቅዱስ እልፍኝ (ጽርሐ ቤቱ) ከሰማይ ከወረደ ቃል በቀር ሌላ አድሮባል እንዳያሰኝ "ወትረ ድንግል ማርያም" ብለን እንድናምን እና ድንግሊቱ "ብቻ መውለድን ቀምሶ አቀመሰኝ" እንዳለች ከእርሱ ውጪ ሌላ ልጅ እንደሌላት "እምድኅረ ወለደት ኪያሁ ነበረት በድንግልና" ብለን እንድንመሰክር ዙፋኑን ለራሱ ሠራ ይላል።

ሁለቱ የሊባኖስ እፀው ቅድስት ሀናና ቅዱስ ኢያቄም መሰላቸውን ሳይተኩ በመቆየታቸው ያዘኑት ሐዘን ማንም የማይተካትን የዓለም ሁሉ መክበሪያ አስገኘ! ይህስ ሐዘን የፍጥረት ሁሉ ሐዘን ነበር ዳግሚት ሰማይ ዳግሚት ምድር በመውለድ ደስታቸውን ወደ መካፈል አሳደጉን ከዚቁ ይህን ብለን የዛሬውን በዛሬ እንቋጭ፦

" አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ
ረከቡ ወለተ ዘታሥተሰሪ ጌጋየ
ለወንጌላውያን ኩልነ ዘኮነተነ ምጉያየ
ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ
ምስራቀ ምስራቃት ሙፃዕ ፀሐይ
እግዝእትየ ዘመና ሙዳይ
ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ "
አረጋውያኑ ― በእጅጉ ቢያለቅሱ፣
በደል በምታርቅ ― በሴት ልጅ ተካሱ፤
ለወንጌልም ልጆች ― መሸሻቸው ካለም ፣
ሰማይን ወለዱ ― ሃናና ኢያቄም ፣
ሰማይዋም (ሰማዯም) ፀሐይን ― አውጥታለች ለዓለም፤
የምሥራቃት ምሥራቅ ― መውጫዋ ለፀሐይ ፣
የፍጥረት እመቤት ― የመናዋ ሙዳይ ፣
ዛሬ ተወለደች ― ዳግማዊቷ ሰማይ ።

⊙✧⇥ ይቆየን !

ከቴዎድሮስ በለጠ ( ክፍለሥላሴ)
Яερ๑รтεδ ƒя๑๓፦ ግንቦት ፩ ቀን ፳፻፲ ዓ·ም ከደብረ እንቊ ልደታ ለማርያም
1.5K viewsDrshaye Akele, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 04:56:21

++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?!  እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ኝ የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦  አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/joinchat/AAAAAEILHwyFiBuqHNVyRw
2.3K viewsDrshaye Akele, 01:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:58:40
+++ ጣዖት ምንድን ነው? +++ [እግር ኳስ ጣዖት ነው ወይስ አይደለም?] «ጣዖት» ለአንድ ነው። ለብዙ ሲሆን «ጣዖታት» ይሆናል። በዕብራውያን ቋንቋ «ጣዑት» ይሉታል። «ጣዖት» ማለት ስሕተት የሆነ ሥራ፣ በቊሙ ግልፎ፥ ስብኮ፣ የጥጃ፥ የእንቦሳ፥ የሰው፥ የእንስሳ ምስል፣ ስሑታን ሰዎች የሚያመልኩት ተብሎ ይተረጒማል። (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ሐዲስ) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትም «ጣዖት…
781 viewsDrshaye Akele, edited  18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:58:11 +++ ጣዖት ምንድን ነው? +++
[እግር ኳስ ጣዖት ነው ወይስ አይደለም?]

«ጣዖት» ለአንድ ነው። ለብዙ ሲሆን «ጣዖታት» ይሆናል። በዕብራውያን ቋንቋ «ጣዑት» ይሉታል። «ጣዖት» ማለት ስሕተት የሆነ ሥራ፣ በቊሙ ግልፎ፥ ስብኮ፣ የጥጃ፥ የእንቦሳ፥ የሰው፥ የእንስሳ ምስል፣ ስሑታን ሰዎች የሚያመልኩት ተብሎ ይተረጒማል። (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ሐዲስ)

የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትም «ጣዖት ማለት ከዕንጨትና ከቀለጡ ማዕድናት የተሠራ፣ የማምለኪያ ምስል...» እያለ ይተረጒምና ምእመናን ከጣዖት መራቅ እንዳለባቸው ገልጦ «እግዚአብሔር ከሰጠን ውጭ ሌላ ነገር እንዲኖረን መመኘት ጣዖት ነው» በማለት ደምድሞ አስቀምጦታል።

ይህች ዓለም ጣዖትን ያመለኩ በርካታ ነጋሽ እና አንጋሾችን አፍርታለች። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክም ይሁን በገድላትና በድርሳናት እንደምናነበው «ሃይማኖታችሁን ካዱ፥ ለጣዖት ስገዱ» በማለት እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ደጋግ አባቶችን ሲያሳርዱ የነበሩ ክፉ ጣዖታሞች ነበሩ። አሉ። ለወደፊቱም ይኖራሉ።

እነዚህ ልበ ደንዳኖች ምስል ቀርጸው፣ ጣዖት አቊመው፣ ዕጣን አጢሰው፣ ለምስሉ ሲሰግዱና ሲያሰግዱ በመኖራቸው እንደ ክፋታቸው መጠን በየጊዜው ዋጋቸውን አግኝተዋል። ለወደፊት እነሣለሁ የሚሉም ዋጋቸውን ያገኛሉ።

ጣዖት የምንለው የተቀረጸ ምስል ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር የማይከብርበት ከንቱ ሥራ ሁሉ ጣዖት ነው። አንዲት ሴት መልክና ደም ግባቷን በመስታውት እያዬች ዘወትር የምትኮፈስ ከሆነ መልኳ ደምግባቷ ለእሷ ጣዖት ሆኖባታል። አንድ ሰው የዝሙት ልምድ ካለውና ያንን ክፉ ሥራ መልቀቅ ካልሻተ ዝሙቱ ጣዖት ነው። «ወዘመዉ በጣዖቶሙ» እንዲል (መዝ ፻፮፥፴፰)

ወዳጄ በየቤቱ ብዙ ጣዖት ያቆመ አለ። ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥበት ራሱ ያቋቋመው ቀኖና ጣዖት ሆኖበት የሚያስቸግረው ስንቱ ነው? ጫቱ፣ ሲጋራው፣ መጠጡ ጣዖት የሆነበት ስንቱ ነው? ዝሙቱ፣ መዳራቱ፣ ውንብድናው፣ ፍቅረ ነዋዩ፣ ጣዖት የሆነበት ስንቱ ነው?

ለዚህ አይደል ሐዋርያው «የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።» (፩ኛ ቆሮ ፲፥፳፩) ብሎ የዘጋው። ቅዱስ ጳውሎስ አድበስብሶ አላለፈም። ይልቊንም «ወዳጆቼ ሆይ፥ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ።» (፩ኛ ቆሮ ፲፥፲፬) ሲል ቊርጥ ያለ ቃል አስቀምጧል። ወልደ ነጐድጓድ ዮሐንስም በመልእክቱ «ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።» ሲል ያስጠነቅቃል። (፩ኛ ዮሐ ፭፥፳፩)

ከዚህ አንጻር እግር ኳስ ጣዖት ነው አይደለም ብሎ የሚጠይቅ ሰው ካለ ምን ያሕል ሞኝ መሆኑን እንመን። ወዳጄ አንተነትህን ለማያውቅህ ለአውሮጳ ኳስ ተጫዋች ጨርቅህን ጥለህ ስታብድለት እየዋልህ ጣዖትነቱን እንዴት ዘነጋኸው? በቴሌቪዥን ስክሪን አፍጥጠህ ስታይ እያመሸህና አጋንንት እንደተቆጣጠረው ድውይ ልብህ እስኪወልቅ ስትጮህ እያደርህ ጣዖት መሆኑ እንዴት ተረሳህ?

ልብ በል እንጅ! «እግዚአብሔር ከሰጠን ውጭ ሌላ [ባዕድ] ነገር እንዲኖረን መመኘት ጣዖት ነው» ተባልህ'ኮ። ደግሞስ የኳስ ጥቅሙ ምንድን ነው? የሚረባህንና የሚጠቅምህን ሳትይዝ ስለ አውሮጳ እግር ኳስ ልብህ እስኪወልቅ መደገፍ ምን ይሉታል?

አንተ ከድጋፍ (በሌላው ከመደ'ገፍ) ሳትወጣ የአውርጳን ኳስ ትደግፋለህ አይደል? አንተ ከሰው ጫንቃ ሳትወር የሌላው ደጋፊ መሆንህ አይገርምም? እስኪ ወደራሳችን እንመለስ? ሀገር እንዲህ በሰላም እጦት ተወጥራ ከኳስ ጋር ልናብድ ይገባል? መንፈሳውያን ነን የሚሉ ሰዎች ብሰው ሳይ አዝናለሁ።

«ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።» (፩ኛ ቆሮ ፲፥፳፫)

ቀሲስ ጌትነት ዐይተነው (ክንፈ ገብርኤል)
ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም
815 viewsDrshaye Akele, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:09:58
1.9K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:09:58 ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ [Paschal troparion & Greeting] #የፋሲካ_አመላለስና_ሠላምታ
᳀͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͞ ͟͞ ̸ ͟͞ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ✙ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᳀

(ለትንሣኤ የተቆነጠረ ሐሳብ)

ሀገርኛው የዘውትር ሰላምታችን ሰላም ላንተ ይኹን ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ! በሚል መነሻ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚታከልበት ምኞት መግለጫና ምስጋና ማቅረቢያ ነው!

የሰላምታው መንገድ ደግሞ በሦስት ሂደት (በቃል በእጅና በአንገት) የሚከወን ነው።


መጨባበጥ (ተራክቦተ እድ ፣ ፅብጠት፣ ተጻብሖ) ☞ በእጅ የሚፈጸም ፦ በመጨባበጥ [handshake] በመተቃቀፍ [hugging] አልያም በጉንጭ በመሳሳም [cheek kissing] ይፈጸም የነበረውን በቀደሙቱ ዘንድ “አምኃ ቅድሳት” [holy kiss & kiss of peace ⇨ ἐν ἁγίω φιλήματι, και φιλί της ειρήνης ] እየተባለ የሚጠራው መንገድ ነው!

በዚኽ አጋጣሚ በወቅቱ ጉዳይ መጨባበጥ መተቃቀፍና መሳሳም ለወረርሽቹ በፍጥነት መዛመት ምክንያት መሆናቸውን አውቀን #አካላዊ_ፈቀቅታ|ን በመጠበቅ በበሽታው የምናልፍ ሳንሆን በሽታውን የምናሳልፍ ነገንም የምናይ እንድንሆን በተከታዮቹ መንገዶች ሰላምታ የምንለዋወጥ ይሁን!


"እጅ መነሳሳት" (እማኄ) ☞ ባንገት፣ በወገብና በጕልበት የሚፈጸም ነው።


የሰላምታ ቃል መለዋወጥ (በቃለ ተአምኆ) ሰላምታ በንግግር በመለዋወጥ የሚፈጸም ዋናዎቹ ናቸው!

ወደተቆነጠረው ሐሳብ እንለፍ ተዝካረ ትንሣኤው በሚታሰብበት ዐባይ ፋሲካ ፶ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚፈጸም የተለየ ሰላምታና የዜማ ድጋም አመላለስ አለ።

የጌታችን ተዝካረ ትንሣኤ በቤተክርስቲያናችን ሰፊ ቦታና ትርጉም ያለው በመሆኑ የዓመት ሢሦው (⅓) ነገረ ፋሲካን የሚያስታውስ ነው (የፋሲካ ጾም ⁵⁵ እና ዘመነ ትንሣኤ⁵⁰)

በቅዳሴው መግቢያ መስዋእቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ከትንሳኤው እስከ በዓለ ፶ ጊዜው የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ "እመቦ ብእሲ… " በሚለው መግቢያ ፈንታ "ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪነ ⇨ ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት፡፡" የሚል መልእክት በዜማ ይደርሳል!

ከዚኽ ውጪ ምሕዛል ዘትንሣኤ ወይም «የፋሲካ አመላለስ» ያልነው [Paschal troparion] እና ቃለ ባሕ ዘትንሣኤ «የፋሲካ ሰላምታ» ያልነው [Paschal Greeting] ከወትሮው በተለየ መንገድ ይፈጸማል። ሁለቱም በልሳነ ጽርእ (ግሪክ) #ክሪስቶስ_አኔስቲ / Χριστὸς ἀνέστη እየተባለ ይጠራል።

① #ምሕዛል_ዘትንሣኤ [Paschal troparion] የፋሲካ አመላለስ

በእርግጥ ምሕዛል አልያም ምስትሕዛል የሚባለው በድጓው ሊቃውንቱ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም ሲሆን መነሻውን ድጓ ያደረገው በቅዳሴው ክፍል የምናገኘው ይኽ የተዝካረ ትንሣኤ ምስትሕዛል
«ህየንተ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት እምትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ » በሚል የገባ ሦስት ጊዜ ደጋግመን በመቀባበል የምናደርሰው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ "

በሌሎች ምሥራቃውያን (Eastern ) እና ጽባሓውያን (Orientals) ዘንድም በእጅጉ የተለመደ ነው!

በግሪክ ፓስካል ትሮፓርዮን አልያም [χριστος ανεστη] የሚባል በዜማ የሚደርስና የዘመነ ሐዋርያት ጭምር ጥንታዊ መገለጫ አለው ተብሎ የሚታመን ነው።

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,

θανάτῳ θάνατον πατήσας,

καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,

ζωὴν χαρισάμενος!

የንባባዊ ፍቺው አማርኛ ትየባ (transliteration) ደግሞ ይኽን ይመስላል!

ክርስቶስ አኔስቲ ኤክ ኔክሮኒ ፣ ታናቶ ታናቶን ፓቲሳስ፣ ኬቲስ ኤን ቲስ ሚ’መሲ፣ ዞይን ካሪዛሜኖስ

በትርጉሙም የእኛው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ " ካለው ጋር አቻ ፍቺ አለው።

Christ is risen from the dead, Trampling down death by death, And upon those in the tombs, Bestowing life!

② #ቃለ_ባሕ_ዘትንሣኤ [Paschal Greeting] «የፋሲካ ሰላምታ»

በሓ ወይም ባሕ የሚባለው የሰላምታ የቡራኬ ቃል ፍሥሓ ሰላም የሚለውን የሚገልጥ ነው!

በቤተክርስቲያናችን አበው መምህራንም ቅድመ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ድኅረ ቃለ ቡራኬ ለ፶ው ዕለት ከምእመናን ጋር የሚለዋወጡት ሰላምታ ነው! ከዚያም አልፎ ምእመናንም ከምእመናን ጋር የትንሳኤውን የምሥራች ለማብሰርና መልካም ምኞት ለመግለጥ ያውሉታል።

አቀራረቡ በአመላለስ አገባብ የሚከወን ሲሆን ሰላምታ ሰጪና ሰላምታ ተቀባይ ይኽን ይለዋወጣሉ፤

በኢትዮጵያዊቷ የተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችም ከ6ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን መረጃዎች ይገልጣሉ። በቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ (ዘመወድስ) ውስጥ በፍታሕ ሊተ ሥር በመሪና ተመሪ የሚቀርብ ዛሬ ለፋሲካ ሰላምታ የምንገለገልበት የትንሣኤው ምስክርነት ቃል አለ። እንዲህ ይላል ፦

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፣ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን ፣ አሠሮ ለሰይጣን ፣ አግዓዞ ለአዳም ፣ ሰላም ፣ እምይእዜሰ ፣ ይኩን ፣ ሰላም!
[ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ፣ ሰይጣንን አሠረው፣ አዳምን ነጻ አወጣው ፣ ሰላም፣ ከዛሬ ጀምሮ ፣ ይሁሁን ፣ ሰላም]

በመቀባበል እንዲህ ተጽፏል

☞ Christ is risen from the dead!
☜ By the highest power and authority!
☞ He chained Satan!
☜ Freed Adam!
☞ Peace!
☜ Henceforth!
☞ Is!
☜ Joy and Peace!

☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው፤ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ!

በውጪው ግን ሰጥቶ መቀበል እንጂ አመላለስ የሌለው ባለ አጭር ይዘት ሆኖ በተለያየ ስያሜ የሚጠራ ነው The Paschal Greeting / the Easter Acclamation / The Paschal troparion / Christos anesti…

የበዙቱ የቀደመ መነሻውን ከግሪኩ ተውሰው ሰላምታውንም በሰጣዊ ተሰጣዊ (ሰጪና ተቀባይ) ቃል ልውውጥ ይከውኑታል እንዲህ ሲሉ

#ሰጣዊ ☞ ክሪስቶስ አኔስቲ Χριστός ἀνέστη! Christ is Risen! ✧ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን

#ተሰጣዊ ☜ አሊቶስ አኔስቲ "Ἀληθῶς ἀνέστη! " - "Truly He is Risen!" or "He Has Risen Indeed!" ✧ (አሜን) በአማን ተንሥአ

በአረማይኩ ግን ጥቂት የተሰጣዊ ምላሽ ልዩነት ያለው ሆኖ ይነገራል
1.7K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:09:58
1.5K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ