Get Mystery Box with random crypto!

BE INFORMED FIRST ️ ️

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuschristinheaven — BE INFORMED FIRST ️ ️ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuschristinheaven — BE INFORMED FIRST ️ ️
የሰርጥ አድራሻ: @jesuschristinheaven
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.28K
የሰርጥ መግለጫ

👉መልካም ለማጨድ መልካሙን ይዝሩ!
#Christian_songs
#መጽሐፍ_ቅዱስ_በድምፅ
#ጠቃሚ_ምክሮች
#Scholarships 💌

👉 #ዓላማችን
♥ ሰው ሁሉ ማህበራዊ ሚዲያን ለተቀደሰ ዓላማ እንዲጠቀሙ ማበረታታት፡፡

#For any suggestions 👇👇
@Bochu_Unclica

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:38:05
የቴሌቪዥን ተወዳጁ አደይ ድራማ ስንተኛው ክፍል ማግኘት ይፈልጋሉ?

https://t.me/AdeyDrama_TV/3
307 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:46:04 . የተሸከመህ ሸክም

ገና ከጫጩትነቱ ጀምሮ ብረር ብረር የሚለውና በፍጥነቱ ታዋቂ ለመሆን የሚመኝ ወፍ ነበረ ይባላል፣ ምንጩ የማይታወቅ አፈ-ታሪክ፡፡ እናቱ ከልምዷ በመነሳትና ለእርሱ በመጠንቀቅ ተረጋጋ ትለው ነበር፡፡ እርሱ ግን ፈጽሞ አይሰማትም ነበር፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ሄደና በእርግጥም እንደተመኘው ፈጣን በራሪ ሆነ፡፡

ይህ ወፍ በቃ መብረር ይወዳል፡፡ መብረር ከመውደዱ የተነሳ ማታ ሁሉም በጊዜ ወደጎጆው ሲመለስ አይኑ ለማየት የማይችልበት ደረጃ እስኪመሽ ድረስ ሲበር፣ ሲከንፍ ውሎ እያለከለከ ወደ ጎጆው ይገባል፡፡ ማለዳም ቢሆን ለመነሳት የሚቀድመው ወፍ የለም፡፡ ከእርሱ ዘግየት ብለው የወጡ አቻ ወፎቹን ካልተወዳደርን እያለ ስቃያቸውን ነው የሚያላቸው፡፡ ሁሉንም ግን ይቀድማቸው ነበር፡፡

ይህ ወፍ ሌሎቹን ወፎች ሁሉ የመቅደሙ ሁኔታ ስላላረካው አሁንም ከዚያ በበለጠ ሁኔታ ለመፍጠንና ከእርሱ የላቁ የወፍ ዝርያዎች ጋር ለመወዳደር ምኞት አደረበት፡፡ አንድ ቀን አንድ ሃሳብ ብልጭ ያለለት መሰለው፡፡ ብዙ ካሰበ በኋላ፣ “ችግሬ ክብደቴ ነው” ወደማለት ሃሳብ መጣ፡፡ ክብደቱን ለመቀነስ ሲል በየቀኑ አንድ ላባ ከክንፉ ላይ በመንቀል ፍጥነቱን መለካት ጀመረ፡፡ የተወሰኑ ላባዎች ሲነቅል እውነት ይሁን ወይም የስነ-ልቦና እይታ ያመጣው ምልከታ ይሁን ባይታወቅም ፍጥነቱ የጨመረ መሰለው፡፡

ይህ ተግባሩ እንደማያዛልቀው እናቱ በየቀኑ ብትመክረውም፣ “እንደናንተ ያለ ወደኋላ የቀረ አመለካከት ያለው ሰው ነው የጎተተኝ” በማለት አልሰማ አለ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ መብረር እስከሚያስቸግረው ድረስ አብዛኛዎቹን የክንፉን ላባዎች ነቀላቸው፡፡ ከዚያ የተከተለውን ውጤት መገመት ቀላል ነው፡፡ እውነታው የገባው በኋላ ነው፡፡

ለካ ሸክም ሆነብኝ ያለው ነገር እሱን የተሸከመው ነው . . . ሸክሜ ነው ያለው ነገር የመብረሪያ አቅሙ ነው . . . አዎ ሸክም ነው፣ ነገር ግን የጉልበት ምንጭ ነው . . . አዎ ሸክም ነው፣ ነገር ግን ወደከፍታ ለመብረር የተነሳበት መነሻና እንደገና የማረፊያ ምክንያት ነው፡፡

• ይህ የልጆች የሚመስል ታሪክ “ሸክም ሆናችሁብኛል” በማለት ቀድሞውኑ የጉልበት ምንጭ የሆኑትን ቤተቦቹን ነቅሎ የጣለውን ሰው አስታወሰኝ፡፡

• ታሪኩ ውጪ ለተከፈተለት የስኬትና የተቀባይነት እድል መነሻው ቤተሰቡ፣ ትዳሩ፣ ልጆቹና የቅርብ አጋሮቹ ሆነው ሳሉ፣ የሚደርስበትን የስኬት ከፍታ ሲያይ መነሻውን እንደሸክም በመቁጠር ጎድቶ የተነሳውን ሰው አስታወሰኝ፡፡

• ይህ የወፉ ታሪክ ጡንቻ ሲያወጣ፣ አይኖቹ ሲገለጡ፣ ዙሪያውን መመልከት ሲጀምርና ለጋ አቋሙን የሚያደንቁለት ሲበዙ እዚያ ያደረሱትን ወላጆቹንና አሳዳጊዎቹን እንደሸክም የቆጠረውንና ከሕይወቱ ነቅሎ የጣላቸውን ወጣት አስታወሰኝ፡፡

• ይህ ቀላል የሚመስል ታሪክ ተሸክመውት ሳለ እርሱ ግን እንደሸክም የቆጠራቸውን ከእሱ ለየት የሚሉትን የሃገሩን ሰዎች ገንጥሎ ለመጣል የሚቃጣውን የህብረተሰብ ክፍል አስታወሰኝ፡፡

የተሸከመህን ሸክምህን አትጣል!

Dr.Dreyob Mamo
BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
336 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:13:31 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው

1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ ጊዜው ሲገፋ በዘፈቀደ የሚኖር ከንቱ ሰው እንደሆንክ ማሰብህ አይቀርም፤

2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤

3. በፈጣሪህ ታመን! ከዛ ልበ ሙሉነት ፀባይህ ይሆናል። ግን ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን!

@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
share"
275 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:23:42 . ወድቆ የማይቀር ማንነት!

ታላቅ ለመሆን ተፈጥረሀል! ደስተኛ ሆነህ ለመኖር ተፈጥረሀል! አሁን ያለህበትን አይተህ ራስህን ዝቅ አታርገው፤ ብርሀን ከጨለማ ጋር ምንም ህብረት የለውም፤ ያንተም ድክመት ወይ መሳሳት ጊዜያዊ ነው፤ ለምን ካልከኝ ጥሎ የማይጥል ፈጣሪና ወድቆ የማይቀር ማንነት ስላለህ!

Motivate ur mind

@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
share"
563 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:08:11 . የተወደድክ

ስትደክም የሚያዝንልህና የሚሳሳልህ ፀጋና ምህረትን እየሠጠ የሚደግፍህ አሸናፊ ሆነህ እንድትኖር የሚችለውን ሁሉ የሚያደርግ አባትህ እንጂ። ስትሳሳት ሊቀጣህ የተዘጋጀ ምህረት የማያውቅ በስህተትህ ሊራራልህ የማይችል ሁልጊዜ አንተን በመውቀስ ብቻ የሚኖር አባት የለህም!! ሁልጊዜም ልጄ አንተ ብርቱ ነህ ይልሀል። እኔ የሞትኩልህ አንተ በህይወት እንድትኖር ነው። የኔ አላማ አንተን ማዳን ነው እንጂ መግደል አይደለም። ሀጢያት አንተን ስለሚጎዳህ ልትሸሸው ይገባሀል በዚህ ጊዜ ደግሞ እኔ ያንተ ረዳት ነኝ። ከሀጢያት ጋር ተስማምተህ እንዳትኖር ምክንያቱም ያንተ ማንነት ፅድቅ እንጂ ሀጢያት አይደለም። አንተ የተፈጠርከው ለፅድቅ ነው። ስለዚህ እኔ ለ አንተ ጋሻህ ነኝ በዚህም ምክንያት አንተ አሸናፊ ነህ። በፍፁም ወደኔ ከመምጣት ተስፋ አትቁረጥ አንተን ማዳን የምችለው እኔ ብቻ ነኝ። የአምላክህ የልብ ንግግር ይሄን ይመስላል...አንተ የተወደድክ ነህ!

@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
985 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:24:00
2015 የአዲሱ ዓመት ዋዜማ ታሪካዊ ሀገር አቀፍ የንግድ ትርኢትና ባዛር በውቢቷ ከተማ ሀዋሳ መስቀል አደባባይ በደማቅ ስነስርዓት ታላላቅ እንግዶችና የንግድ ተቋማት ባሉበት የሀዋሳ ከተማ ክቡር ከንቲባ ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ በይፋ አስጀምረዋል።

የዘንድሮውን ባዛር ልዩ የሚያደርገው ሁሉ ሙሉ የተሟላ መሆኑ ሲሆን በተጨማሪም የሲዳማ ባህላዊ ምግብ አዘጋጅ አዚ ሆቴልና ጥራት ባለው ቡና እውቅናን ያተረፈው ፊላ ካፌ የባዛሩ ልዩ ድምቀት ሆነዋል።

ባዛሩ ለተከታታይ ቀናት ማለትም እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆይ ይሆናል።

ፊላ ካፌ እና አዚ ሆቴል

Bochu
Sponsored by FILA CAFE & Azy HOTEL
BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
962 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:50:49
እንኳን ደስ አላችሁ መልካም ወጣት ወደተለወጠው ህይወት በድል ተጠናቀቀ!!!!!

መልካም ወጣት ተሳታፊ የነበራችሁ የተሰማችሁን በComment ግለፁልን #share
Be informed first
@Jesuschristinheaven
838 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:00:08 ከነህልማቹ መሞት የለባችሁም

ማንም ሰው ህልሙን የመኖር ፍላጎት አለው፤ ውስጡንም ብትፈትሹት አንድ መሆን የሚፈልገው ነገር ይኖረዋል ነገር ግን ምንም ያህል አለምን የሚቀይር ህልምና አላማ ቢኖረውም አላማውን አካል እስካላለበሰ ድረስ ዋጋ የለውም፤ እግዚአብሔር በየ ዘመኑ አለም የሚቀይሩ ብዙ ሀሳቦችን ለትውልዱ ይሰጣል፤ አውቀውትና ገብቷቸው ሀሳቡን አካል የሚያሲዙት ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ሌሎች ግን በስንፍናቸው ምክንያት ከነ ህልማቸው ይሞታሉ ፤ እናንተስ ውስጣቹን ምን ያህል ሰምታቹታል፤ የእውነት እግዚአብሔር ትልቅን ነገር በውስጣቹ እንዳስቀመጠ አምናለሁ፤ ይህንን ሀብት ደግሞ በስንፍናቹ ምክንያት ማጣት የለባቹም ስለዚህ በእናንተ ውስጥ ያለውን አቅም አውጡትና ተጠቀሙበት።

Ermias
BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
854 views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, edited  18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:11:02 አንዳንዴ በህይወትህ ውስጥ በብዙ ፈተናዎችና ጭንቀቶች ልትከበብ ትችላለህ ...

ያኔ አንተ ልትፈታው በምትችለው ነገር ላይ ብቻ አተኩርና ቀሪውን ለመፍትሄዎች ሁሉ ባለቤት ለፈጣሪህ ተወው:: መውጫ መፍትሄ አንተ ጋ እንጂ ፈጣሪህ ዘንድ አይጠፋም ደግሞም አስታውስ ሁሌም ትላልቅ ጭንቀቶች አሉብኝ ብለህ ለጭንቆች እውቅና ከመስጠትህ ይልቅ የትላልቅ ጭንቀቶች አለቃ የሆነው ጌታ አለኝ እያልክ ጭንቀቶችህን አቅልላቸው። በፈጣሪህ ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ!

እንደዚህ ሆነ ከለታት በአንድ ወቅት ጫካ ውስጥ መውለጃዋ የቀረበ አንዲት ሚዳቆ ነበረች ። መውለጃ ሰዐቷ ደርሶ ትግል ላይ ሳለች ድንገት አከባቢዋን ስትቃኝ ከፊት ለፊቷ ወንዝ ፣ ከኋላዋ ቀስት ያነጣጠረባትን አዳኝ፣ ወደ ጎን ስትዞር የተራበ አንበሳ አሰፍስፎባት ትመለከታለች።

ይህም ሳይበቃት በተጨማሪ ከፍተኛ ነጎድጓድና መብረቅ ያጀበው ደመና መጥቶ ሰማዩን ያጨልመዋል። መብረቁም ከፍተኛ ነበርና ደኑን ይመታና ከፍተኛ ቃጠሎን ያስነሳባታል። ወደ ፊት ሮጣ እንዳታመልጥ ጥልቅ ወንዝ ተደቀነባት ከኋላዋ አዳኙ ከጎኗ ደግሞ አንበሳው ወደ ጫካ ገብታ እንኳ እንዳትደበቅ ከፍተኛ ቃጠሎ ላይ ነው በዚያ ላይ የውልደት ህመም ነፍስ ውጪ ግቢ እያስባላት ነው ሚዳቆዋ በዚህ ውጥረት ውስጥ ሆና ትኩረቷን መፈፀም ወደ ምትችለው ነገር ላይ ብቻ በማድረግ ቀሪውን ለፈጣሪ በመተው በመወለድ ላይ ስላለው ልጇ ብቻ ማሰብ ጀመረች። አዳኙ ቀስቱን አነጣጥሮ ሊለቅ ባለበት ጊዜ ድንገት የመብረቁ ብልጭታ አይኑን ብዥ ያደርግበትና ቀስቱ አምልጦት ወደ ተራበው አንበሳ ይሄድና አንበሳውን ይገለዋል። አጎብድዶ የነበረው ደመናውም መዝነብ ይጀምርና የደኑን ቃጠሎ በቅፅበት አጠፋው።
በጭንቅ ታጅባ የነበረችው ሚዳቆም በሰላም ተገላገለች።

እኛ ግን ነገሮች ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንደሚሆኑ እናውቃለን

#share #share &"Join us
BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
1.1K views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:49:50 የ 12ኛ ክፍል ፈተና በ2 ዙር ይሰጣል።

1ኛ ዙር---Social Science ከ መስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3

2ኛ ዙር ---Natural Science ከ ጥቅምት 8 እስከ 11 ይሆናል።

. ቁጥራዊ መረጃ
በዚህ አመት 984,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፈል ፈተናን ይወስዳሉ።

Social Science 622,739 ሲሆኑ

Natural Science 361,279 ናቸው።

#SHARE# SHARE & JOIN US
BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
1.8K views𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ