2022-07-05 22:19:53
እርሱም ተፈወሰ።" (2ኛ ነገ. 20:7) " ከበለሱም ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንጀራ አልበላም ውኃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ ነፍሱ ወደ እርሱ ተመለሰች።" (1ኛ ሳሙ. 30:12) እና መጽ. ባሮክ
* በሕገ ወንጌል መድኅነ ዓለም ክርስቶስ የ"ሆሳዕና"ው ማግሥት በመንገድ ሲያልፍ ሊበላ ፍሬ ፈልጎ የተጠጋው ወደዚህችው የበለስ ተክል ነበር "በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።" (ማቴ. 21:19)
በነገረ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ምሳሌነቱ
"በለስ ዘይቤ ቤተ እስራኤል እሙንቱ" ባለው የምዕመንን ሰውነት በለስ ይለዋል ምግባር አልባ እንዳትሆን! በአንጻረ በለስ ኃጢዓት የተቆረጠላት ለገቢረ ጽድቅ ጉልበት እንዲኖራት ያደረጋት በለስ የሕይወታችን ምሳሌ ናት
የዘመናት መለወጥ የወቅቶች መፈራረቅ አስረጂ ምልክት ሰጪ ነው ! በዚህም ባህረ ሀሳቡን ቀምረው የአጽዋማቱን መውጫና መግቢያ ለይተው በማስተማር ለድኅነተ ነፍስ የሚያበቃ ምግባር አሠርተው ተዘክሮተ ሞት ከምዕመናን እንዳይታጣ የሚመክሩ አበው መምህራንን ይመስላል:: "ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤" (ማቴ. 24:32) "በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ።" (መኃ. 2:13)
ታግሠው ቢጠብቁት በሚገኝ በከበረ ፍሬው ምግብና ፈውስ ነው! ምግበ ነፍስ ቃለ እግዚአብሔርን ፈውሰ ነፍስ ንሰሐን ከምዕመናን ሕይወት የሚያደርሱ አበው ካህናቱን መምህራነ ነፍስ ሊቃውንቱን ይመስላል "በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።" (ምሳ. 27:18)
#ዕፀ_ወይን
"ወይቤልዎ ኩሎ ዕፀው ለወይን ንአ ንግሥ ለነ። ወይቤልዎ ወይን እኅድግኑ ወይንየ ወትፍሥሕትየ ዘበኀበ እግዚአብሔር ወዘኀበ እጓለ እመሕያው ወእሑር እንግሥ ለዕፀው … እንጨቶች ሁሉ ወይንን ና ንገሥልን አሉት፤ ወይንም ለእንጨቶች እነግሥ ዘንድ ለእግዚአብሔር መስዋእት ለሰው ትፍስሕት መሆኔን ልተውን አላቸው። "
ወይንም ዕለተ ፍጥረቱ ሠሉስ ነው! ቅባት የሚሰጥ ለመብልነት ለመብራትም የሚውል የወይራ ወገን ቢሆንም ከዕጸው ሁሉ እጅግ የተመረጠና የተወደደ ነው ! "አቤቱ ጌታዬ በዚህ ዓለም ካሉ ከታላላቁ ከታናናሾቹም እንጨቶች አንድ የወይን ሐረግን መረጥህ" (ዕዝ ሱቱ 3:23)
* በሕገ ልቡና:- ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ በሥራው ገበሬ ሆኖ የተከለው ወይን ነበር " ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። " (ዘፍ. 9:20) የልዑል እግዚአብሔር ካህን የክርስቶስ ምሳሌ መልከጼዴቅ ያስታኩት የነበረው በወይን ነው "የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።" (ዘፍ. 14:18)
* በሕገ ኦሪቱ እንደ ወይራ ሁሉ ከምድረ ርስት ከነአን ገጸ በረከት አንዱ ወይን ነው! "ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፥..." (ዘዳ. 8:8)
* በሕገ ወንጌል ክርስቶስ በከብካበ ቃና ዘገሊላ የለወጠው ውኃ ጠጅነቱ የወይን ነበር "ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ።" (ዮሐ. 4:46) ራሱንም መስሎ ያስተማረበት ነው (ዮሐ. 15:1-5)
በነገረ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ምሳሌነቱ
የምዕመናን ሕይወት በዐጽቀ ወይን አስገኚ ጌታቸውም በሐረገ ወይን እየተመሰለ ይነገራል "እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።" (ዮሐ. 15:5) "አብ ጉንደ ወይን ወልድ ጉንደ ወይን መንፈስ ቅዱስ ጉንደወይን" እንዲል ቅዳሴ ማርያም
ጌታችን ሥጋውን በኅብስት እነደሰጠ ለማጠየቅ ሲሻ ራሱን በኅጠተ ሥርናይ (በስንዴ ቅንጣት) ይመስላል እንዲሁም ደሙን በወይን እንደሰጠ ሲያመላክተን ራሱን በሐረገ ወይን የመስልል! በእርሱ አምነው ሥራ የሚሰሩ በትምህርቱ አምነው ጸንተው የሚኖሩ በልተውት ጠጥተውት የሚከብሩ ምዕመናንም በዚሁ ተመስለዋል "ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" (መኃ.2:15)
#ዕፀ_ራምኖን (አስታ ወይም ዶግ ወይም እሾህ )
"ወይቤልዋ ዕጸው ለራምኖን ንዒ አንቲ ንግሢ ለነ ወትቤሎሙ ዕጸ ራምኖን ለዕጸው እመ በአማን ታነግሡኒ ...በጽድቅ ላዕሌክሙ ንዑ ታጽለሉ ታሕተ ጽላሎትየ እመ ኢወጽአት እሳት እምራምኖን ወትበልዖ ለአርዘ ሊባኖስ ... ዛፎችም ሁሉ እሾህን፦ መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት።እሾሁም ዛፎችን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ታነግሡኝ እንደ ሆነ ኑ ከጥላዬ በታች ተጠጉ። እንዲሁም ባይሆን እሳት ከእሾህ ይውጣ፥ የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል አላቸው።"
ፍሬ አልባ ቅጠሉም የማያጠላ ሌላውም እንዳያፈራ አንቆ የሚይዝ ካፈራውም ተጠግቶ ወግቶ የሚያደማ ክፉ ተክል እሾህ ነው! የአዳም የበደሉ ርግማን መገለጫ መሆኑ ተገልጿል "እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።" (ዘፍ. 3: 18) በዚህ ምርገም ጥላ ሥር ያሉትን ልጆቹን ሁሉ እሾህ ይላቸዋል ከንጽሕት እመ አምላክ ድንግል ማርያም በቀር እርሷን "በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ" ይላታል (መኃ. 2:2) የታካቾች ፍኖት መገለጫ ሆኖም ተነግሯል "የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።" (ምሳ. 15:19)
የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል የያዛቸው በእሾሆች የታነቁ ይባላሉ ለነዚህም እሾሁ ብዕል ሰፋጢት (አታላይ ባልጠግነት) ሐልዮ መንበርት (ቦታን ማሰብ ሥልጣንን መናፈቅ) ትካዘ ዓለም (ሥለ ሥጋ ማሰብ) ፍቅረ ብእሲትና ፍቅረ ውሉድ እያታለላቸው በመንፈሳዊ ሕይወት እንዳይጎለብቱ ማነቆ ይሆንባቸዋል! ትሩፋት አፍአዊን ሠርቶ ትሩፋት ውሳጣዊ የቀረችበት እሾኻማ ይባላል!
"ሁሉም ለገንዘብ ይገዛል።" እንደተባለ (መክ. 10:19) እመጸውተዋለሁ እያሉ ገንዘብ የሚሰበስቡ አሉ እኒህን መጽሐፍ "ኢትኩን መፍቀሬ ነዋይ በእንተ ፍቅረ ነዳያን" ይልባቸዋል::
ፍሬ ከሌላቸው ፍሬ አልባ ከሚያደርጉ እሾሆች መራቅ ደግሞ እጅጉን ይገባል:: ገንዘብ እየሰጡ እጅ መንሻ እያመጡ ሹሙን ሸልሙን ከሚሉ እሾሆች መሸሽ ይገባል "እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል።" እንዳለን የጥበብ ወዳጇ (ምሳ 22:5) "ሥልጣንን በመውደድ አስኬማቸውን ቀንድ" አድርገው መልሰው ቤተክርስቲያንን ከሚወጉ የምሕረት አምላክ ይጠብቀን::
እንደ ማጠቃለያ
ሁሉን እንዳሰቡት እንደሚጠብቁትም አለማግኘት ደስታን የሚያጓድል ኃዘንን የሚያመጣ ይመስላል:: ይሁንና ግን እግዚአብሔር እንደወደደ ነገር ሁሉ መደረጉን ለምናምን "የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ" (ነህ 8:10)እንዳለው በነገር ሁሉ እያመሰገንን በተለይ ባለንባት ዘመን እንዲህ እያልን ልንኖር የገባል “ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ ... እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል" (ዕን. 3:17)
4.3K viewsተεพ๑δr๑ร (አግናጥዮስ)𝕿𝖊𝖜𝖔𝖉𝖗𝖔𝖘 𝕭𝖊𝖑𝖊𝖙𝖊 𝕸𝖊𝖓𝖌𝖎𝖘𝖙𝖚 Ignatius Theophoros (Ἰγνάτιος Θεοφόρος), 19:19