Get Mystery Box with random crypto!

አናሲሞስ - Anasimos

የቴሌግራም ቻናል አርማ anasimos_tube — አናሲሞስ - Anasimos
የቴሌግራም ቻናል አርማ anasimos_tube — አናሲሞስ - Anasimos
የሰርጥ አድራሻ: @anasimos_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.69K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙሮች ግጥሞች ከነ ዜሞቻቸው ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
share ማድረግ እንዳይረሳ
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Youtube -https://youtu.be/hiPRAx332IY

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 21:51:38 ኢትዮጵያ እንደ ርብቃ በሆድዋ ያሉ ልጆችዋ እየተዋጉባት  "እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?" ብላ እየጮኸች ነው:: ለእናት ልጆችዋ ቢጋደሉላት ምን ይጠቅማታል? ሟቹም ልጅዋ ገዳዩም ልጅዋ ነውና ከመቁሰል በቀር ምንም አታገኝም:: ዳዊት ልጁ አቤሴሎም ሌላ ልጁን አምኖንን በገደለ ጊዜ ያለቀሰውን ለቅሶ ኢትዮጵያ ታለቅሳለች:: በዚህ መካከል ምስኪኑ ወገናችን ይረግፋል:: እጅ እጁን ሲቆርጥ ደስታና ፉከራ የለም:: ብንችል በዚህ ሰዓት በጸጸት እንጸልይ:: ካልቻልን ደግሞ ቢያንስ ዝም እንበል:: የሀገርን ሰላም የምትፈልጉ ሁላችሁ ከሩቅ በለው በለው ማለት ትታችሁ ማረን ማረን በሉ::

በሩቅ ሆነን አይነካንም ብለን እየፎከርን በምስኪኑ ላይ እሳት የምናነድ አንሁን:: በወገን ሞት ተደስተን እንደባዕድ ሀገር ጦርነት የድል ዜማ ብናዜም እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ይፈርድብናል::

ከራሳችን በላይ ሌላ ጠላት የለንምና ጌታ ሆይ ከራሳችን አድነን:: ኢትዮጵያ እጅዋን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ትታ ራስዋ ላይ ቃታ የሳበችበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ጌታ ሆይ በዓይነ ምሕረትህ ተመልክተህ እኛው ያነደድነውን እሳት አብርድልን:: በትግራይ በአማራ በኦሮሚያ ያሉ በዚህ እሳት ዙሪያ የሚማገዱ ወገኖቻችንን ከጥፋት ይጠብቅልን:: በግራም በቀኝም የተሰለፉት በድህነት የሚኖሩ አንድ ውኃ የጠጡ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው::  አባቶቻቸው ሳይለያዩ አብረው ከብዙ ጠላት ጋር ታግለው ባቆዩአት መሬት ላይ ወንድማማቾች ጦር እየተሳበቁ ነውና በቸርነትህ ልባቸውን አራራ:: ወንድምን ገድሎ እንደ ቃየን ከመቅበዝበዝ በቀር ትርፍ እንደሌለ አሳያቸው:: ጠግቦ በልቶ ሳያድር ተመስገን ማለትን ያልተወ ሕዝብህን ጌታ ሆይ በምሕረትህ አድነው::

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
93 viewsአናሲሞስ ፳፪, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 22:24:00
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
289 viewsአናሲሞስ ፳፪, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:22:18
የፍጥረት አለቆች አዳምና ሔዋን በፊቱ መቆም ያልቻሉትን የአዳምና የሔዋን ልጅ ድንግል ማርያም እንደምን ወሰነችው??? ሰማይና ምድር አይወስኑትም እኮ! ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በቅዳሴው እንደተናገረው ''ዓሣዎች የማይዋኙት ጥልቅ ነው፤ንስሮች የማይበሩት ምጡቅ ነው፤ ኪሩቤል የሚያዩት ረቂቅ ነው፤ ነፋሳት ሩጠው የማይደርሱበት ሰፊ ነው፤ እሳታውያኑ ኪሩቤል ሊነኩት የማይቻል እሳት ነው ፤ ከአርያም በላይ የሚገኝ ልዑል ፤ ከበርባኖስም በታች ያለ እረጅም ነው ...'' ከዚያም በላይ ነው ።ነገር ግን ለመለኮት ነውና ላይገርመን ይችላል መለኮት ሁሉን ይችላልና ። በጣም የሚገርመው በአንዲት የ15 ዓመት ብላቴና ማኅፀን ሲወሰን ከሚያንጸባርቀው ዙፋኑ ከሚወጣ ብርሃናዊ ክብሩ የተነሣ ፊቱን ለማየት ብርሃናውያኑ ፍጡራን ፊታቸውን በክንፎቻቸው የሚጋርዱለት እርሱን በማኅፀኗ ተሸከመችው ። ወዮዮዮዮዮ ድንቅ ነው።


እነርሱ ዙፋኑን እንኳን እንዳያዩ ነው'ኮ  የሚለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፊታቸውን ይሸፍናሉ አለ። እርሷ ግን ዙፋን ሆነችው ፤ ሶስት ክንድ ከስንዝር ሆና ሳለ የማይወሰነውን ወሰነችው ፤ ጠባብ ሆና ሳለ ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎች በማኅፀኗ ተዘረጉ የሚያስደነግጠውና የሚያስፈራው ኪሩቤል የሚሸከሙት ዙፋን በማኅፀኗ ተዘጋጀ።


ይደነቃል እንጂ ሊነገር አይችልም።

           [_ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መላክ_]
420 viewsአናሲሞስ ፳፪, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:57:17 ኦርቶዶክሳውያኑ ወንድማማቾች ድጋሚ እርስ በእርሳቸው እንዲጫረሱ ሁኔታዎችን አመቻችተው ጥሩምባውን ነፍተው የሞት ድግሱን ደግሰውላቸዋል።
የቅዱሳኑን አባቶቻችን አምላክ በቃችሁ ይበለን እንጂ ምድራዊ መፍትሔም ያለው አይመስልም።

#የእኔ_ምኞት፦ የአኵሱም ጽዮን ልጆች ከግሸን ማርያም ልጆች ጋር ስለ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታቸው ብለው መስማማት ቢጀምሩ፤ የደብረ ዳሞው ጻድቅ የአቡነ አረጋዊ ልጆች እና የቅዱስ ላሊበላ ልጆች የሚለያያቸውን ምድራዊ ርካሽ ፖለቲካ ወደጎን ብለው አንድ ስለሚያደርጋቸው ሰማያዊ መንግሥት ብለው ሰላምና እርቅ አውርደው እርስ በእርሳቸው የሚያባሏቸውን ደማቸውን በከንቱ የሚያፋስሱትንና በሞታቸው የሚነግዱባቸውን ወያኔንና ብአዴን/ብልግናን ከላያቸው ላይ አራግፈው ጥለው ሁለቱ ቁጭ ብለው ቢመክሩ ያንጊዜ 3 ሰዓታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሞት ነጋዴው ጩጬው ፓስተር ወደ ዐረብ ሀገር ይፈረጥጥ ነበር፤ ኦህዴድም ከኦነግ ወደ ኤርትራ በረሐ ይገባ ነበር።

ይህ ቢሆን የኢትዮጵያም ትንሣኤ ያንጊዜ ይመጣ ይመስለኛል። ነገር ግን በሰው ሰውኛ ካሰብነው ከንቱ ምኞት ነው። አምላከ ቅዱሳን የአኵሱሞችንና የጎንደሮችን ምሕላና ጸሎት ተቀብሎ ይታረቀን እንጂ ምድራዊ መፍትሔ የለውም። ሁለቱም ኦርቶዶክሳውያን ዛሬ በ"በለው" መፈክር ደንዝዘው ኦርቶዶክሳውያኑ እርስ በእርሳቸው ሲጫረሱ ሰሜን ላይ የሚነደውን እሳት ኦነጋውያን ከዳር ተቀምጠው ይሞቁታል። ከትናንቱ ስሕተታቸው መማር ያልፈለጉን እነዚህን ነው ለካ ሰውየው "ጅል፣ ጅላጅል እና ጅላንፎ" እያለ አስቀድሞ ልክ ልካቸውን የነገራቸው። የሞዐ

እመብርሃን እናቴ ቅድስት አገራችን በምልጃዋ ትርዳን

ሞዐ ተዋህዶ
521 viewsአናሲሞስ ፳፪, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:21:03 የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት

አምላኬ ሆይ ክፉ የማያስብ ምኞቶችም የማይጠጉት ንፁህ እና ቅን ልብን ፍጠርልኝ። ንፁህ ልብ መጥፎ ጨዋታን የማያውቅ ባልንጀራውን የማይነቅፍ ነው። ንፁህ ልብ ሁል ጊዜ በፍቅር የተሞላ እና ለእያንዳንዱ ሰው ደህንነትን እና ሰላምን የሚፈልግ ነው። ንፁህ ልብ መጾምን፣ መጸለይን፣ ማረፍን፣ አካልን ማዋረድን፣ ሁልጊዜ መሥራትና መድከምን ይወዳል::

አሜን...አቤቱ በምህረትህ ጨምርልን

@Anasimos_Tube
589 viewsአናሲሞስ ፳፪, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 14:46:56 ድንግል ሆይ !


ሰማይ በጠቆረበት ፣ ምድር በኃጢአት የጋለ ናስ በሆነችበት ፣ ነቢያት ከተነሡ አራት መቶ ዓመታት ባለፈበት ፣ የነፍስ ገዥ ዲያብሎስ ፣ የሥጋ ገዥ ሮማውያን በሰለጠኑበት ፣ ሃይማኖት በአጥባቂ ፈሪሳውያን ፣ በለዘብተኛ ሰዱቃውያን ፣ በመናኝ ኤሴያውያን ቡድኖች በተከፈለበት ፣ ሊቀ ካህንነት መኰንን ፣ ካህን በገዛ ቤቱ ደመወዝተኛ በሆኑበት ፤ ዓለሙ በአንድ ልዕለ ኃያል አገር ሥር በወደቀበት ፣ የሰው ልጅ በጣዖት አምልኮ መንፈሱ ፣ በሄለናውያን የኑሮ ዘይቤ ኑሮው በተቃወሰበት ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ገመድ በሚጓተቱበት ፣ ፈራጆች በዝተው ሁሉም “እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ” እያለ እጁን በሚታጠብበት ፤ በዚያ ዘመነ ጽልመት ፣ ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔ ፣ የጌታን ዓመት በሚጠባበቁበት ፣ ዓመተ ሰብእ መቼ ያበቃ ይሆን ? ተብሎ በሚናፈቅበት በአስጨናቂው ወራት …..

ነቢይ ጠፍቶ ምክር ፣ ካህን ጠፍቶ ምሥጢር ጠባቂ ናዛዥ ፣ ንጉሥ ጠፍቶ መንጋ ሰብሳቢ ባልተገኘበት ፤ በዚያ የመርዶ ዘመን ጆሮዎችሽ የምሥራች ስለ ሰሙ ፣ ዓለሙ ሁሉ የሚሰማውን የምሥራች ያንቺ ጆሮዎች ሁሉን ወክለው ስለ ሰሙ ፣ ዓለሙ ሁሉ ወጥቶ ሊቀበለው የሚገባውን ጌታ በማኅፀንሽ ስለተቀበልሽው ፣ በአንቺ ድልድይነት ሰውና እግዚአብሔር ቤተ ዘመድ ስለሆኑ ፣ ዘላለማዊ አምላክ ደኃራዊ ሥጋን ተዋሕዶ አንቺ የወልድ መቅደሱ ፣ ማኅፀንሽ መንበረ ፀባዖት ፣ የንጉሡ የክብር ዙፋን ስለሆነ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ !

ሰማይ የሰማያት ሰማይ የማይወስኑት በማኅፀንሽ ስላደረ ፣ ከሰፊው ዓለም ይልቅ ያንቺን ጠባብ ማኅፀን ስለመረጠ ፣ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ አማኑኤል ስለተባለ አንቺን የመረጠ ቡሩክ ነውና ሰላም እለዋለሁ ! ኪሩቤል ቢሸከሙት አያዩትም ፣ አንቺ ግን በዓይኖችሽ ያየሽው ነሽና ከኪሩቤል ትበልጫለሽ ! ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ ! የዘላለም አምላክ በማኅፀንሽ የዕለት ፅንስ ሆነ ። ዘላለምና ዕለት በአንድ ላይ የተገናኙት ባንቺ ማኅፀን ነው ። ዘመን ካለ ዘላለም ፣ ዘላለም ካለ ዘመን የለም ። ሰውና እግዚአብሔር የታረቁብሽ የምሕረት አደባባይ ነሽ ። የልጅሽ ጌትነት የታየው ያንቺ ክብረት ይታየዋል ። ልጅሽን የሚወድ ይወድሻል ። ለምንና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎች የተገዙልሽ ፣ “በበረት እንድወልድ ለምን ወሰነ ?” ብለሽ ያላዘንሽ ፣ እንዴት ይሆናልን “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም” በሚል ቃለ አሚን የረታሽ አንቺ ነሽ ። እመ ኢየሱስ ፣ እኅተ ኢየሱስ ሁነሽ ባሕረ እሳት ሲከፈል “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች” ብለሽ የዘመርሽ ሐዲስ ማርያም ሰላምታ ይገባሻል !

ዛሬም እንደ ጥንቱ ችግራችን አንቺ በሥጋ ከነበርሽበት ዘመን ጋር ተመሳስሏል ። የምልጃሽ በረከት አብሳሪ መልአክን ይላክልን ። ፍልሰትሽ ትንሣኤያችንን ፣ ዕርገትሽ የምእመናንን መነጠቅ ያስታውሳል ። የሆነልሽ ግን ከሆነልን በላይ ነውና ክብር ይገባሻል !

ድንግል ሆይ …..

ኖላዊ
@Anasimos_Tube
1.0K viewsአናሲሞስ ፳፪, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:46:43 ንጉሥ ሰሎሞን እናቱ ቤርሳቤህ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመጣች ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ‹‹ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም ፤ በዙፋኑም ተቀመጠ ፤ ለእናቱም ወንበር አስመጣላት በቀኙም ተቀመጠች፡፡ እርስዋም ፡- አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች፡፡ ንጉሡም ፡- እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ለምኚ አላት›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (1ነገሥ. 2፡19-20) ከዳዊት ሆድ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ሰሎሞን ይልቅ በዳዊትን ዙፋን ለዘለዓለሙ ይነግሣል የተባለለት ክርስቶስ ይበልጣል፡፡ ስለ ክርስቶስ ‹‹ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማቴ. 12፡42) ክርስቶስ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከሆነ የክርስቶስ እናትም ከሰሎሞን እናት ትበልጣለች፡፡ ሰሎሞን ለእናቱ ከሠጣት ክብርም በላይ ክርስቶስ ለእናቱ የሚሠጣት ክብር ይበልጣል፡፡ የሰሎሞን ቤተ መንግሥት በምድር ነው ፤ የክርስቶስ ቤተ መንግሥት ግን በሰማይ ነው፡፡ መድኃኔ ዓለም ወደ ሰማያዊው መንግሥቱ እናቱን በጠራት ጊዜ እንደምን ተቀብሏት ይሆን? እንደ ሰሎሞን እናት ወንበር አስመጣላት እንዳንል በሰማይ መቆም መቀመጥ የለም፡፡ ነገር ግን ‹‹የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› ተብሎ ድንግሊቱ ስለተሠጣት ክብር ተጽፎአል፡፡ ወርቅ መልበስዋ አነሳት የሚል ካለ ደግሞ ‹‹አሕዛብን በብረት በር የሚገዛቸውን ወንድ ልጅ የወለደችው›› ድንግል ‹‹ፀሐይን ተጎናጽፋ ፤ ጨረቃም ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ፣ ዐሥራ ሁለትም ከዋክብት አክሊል የሆኑላት አንዲት ሴት ነበረች›› ተብሎ ተጽፎላታል፡፡ (መዝ. 44፡9 ፣ ራእ. 12፡1)

ለእኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር አቀባበል በሕሊናችን ከማሰብ በቀር ምን የሚያውከን ነገር የለም፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ድንግልን ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? እዚህ ‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ› ብሎ ሰላምታ ያቀረበላት ይህ መልአክ ጸጋን የተሞላችው ወደ እርሱ ስትመጣ ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? ቅድስት ኤልሳቤጥስ አሁንም ‹ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?› ብላት ይሆን? መጥምቁስ ዳግም በሰማይ በደስታ ዘልሎ ይሆን? ነቢያቱ ድንግልን እንዴት ተቀበሏት? ኢሳይያስ ‹ትፀንሳለች› ያላትን ድንግል ሲያያት ምን ይል ይሆን? ሕዝቅኤልስ ‹የተዘጋችዋ ደጅ› ወደ እርሱ ስትመጣ ምን አለ? ጌዴዎን ጸምሩን ፣ ኤልሳዕ ማሰሮውን ፣ አሮን በትሩን ፣ ኖኅ መርከቡን ባየ ጊዜ ምን ብሎ ይሆን? ሙሴስ ያልተቃጠለችው ዛፍ ወደ እርሱ ስትመጣ ዳግም እንደ ሲና ተራራው ጊዜ ጫማውን አውልቆ ይሆን? አዳም የልጅ ልጁን ሲያይ ሔዋንስ ዳግሚት ሔዋንን ስታይ ምን ብላ ይሆን? ሁሉንም በሰማይ ለመረዳት ያብቃን!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 21 2010 ዓ ም ተጻፈ
1.2K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:46:43 የዳዊት መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር አገናኝተን እንድናስብ ያነሣሣን ምንድር ነው? ወደሚለው እንምጣ፡፡

ዳዊት ስለ ታቦቱ የተናገረውን እኛ ስለ ድንግል ማርያም ሆኖ እንዲሰማን ያደረገው ራሱ ዳዊት ነው፡፡ ዳዊትን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እርሱ ስትመጣ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?›› ሲል አልሰማነውምን? (2ሳሙ. 6፡9) ይህን ንግግርስ ኤልሳቤጥ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› ብላ ለድንግል ማርያም አልደገመችውምን? (ሉቃ. 1፡43) ዳዊት የፈራው ታቦት ወደ እርሱ ሲቀርብ ከዙፋኑ ተነሥቶ በታቦቱ ፊት እየዘመረ ሚስቱ ሜልኮል እስክትንቀው አልዘለለምን? (2ሳሙ. 6፡16) በኤልሳቤጥ ማኅፀን የነበረው ዮሐንስስ የድንግልን ‹‹የሰላምታዋን ድምፅ በሰማ ጊዜ› እናቱ እስክታደንቀው ‹ፅንሱ በደስታ ዘለለ›› አልተባለምን? (ሉቃ. 1፡44) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የድንግል ማርያምና የልጅዋ ክብር ላልገባቸው ሰዎች ‹‹እንደ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ መዝለል ቢያቅታችሁ ምነው ነፍስ ካወቃችሁ በኋላ እንኳን ለእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ ዳዊት በምስጋና ብትዘሉ?›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ እኛ ምን እናድርግ የእግዚአብሔር ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች እንደተባለ ‹‹ማርያምም በዘካርያስ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች›› ተብሎ ተጽፎ አነበብን፡፡ (2ሳሙ. 6፡11 ፤ ሉቃ. 1፡56) ታዲያ የድንግል ማርያም ታሪክ ከእግዚአብሔር ማደሪያ ከታቦቱ ታሪክ ጋር አንድ ሆኖ ስናገኘው ዳዊት ስለ ታቦት የተናገረውን ስለ ድንግል ማርያም እንደምን አንጠቅስ? የነገረ ማርያምን ታሪክ እንጥቀስ ካልንማ ታቦቱ በወርቅ እንደተለበጠ በንጽሕና ያጌጠችውን ፣ ታቦቱ በመቅደስ እንደኖረ በመቅደስ ያደገችውን ፣ ታቦቱን በትሩ አብባ የተገኘች አሮን እንደ ጠበቃት በትሩ ያበበች ዮሴፍ የጠበቃትን፣ ታቦቱን የነካ ዖዛ እንደተቀሠፈ (2ሳሙ. 6፡7) የድንግልን ሥጋ ነክቶ የተቀሠፈውን ታውፋንያ ታሪክ እንጠቅስ ነበር፡፡

‹የመቅደስህ ታቦት› ማለት መቅደስ የተባለው የሰውነትህ ማደሪያ እናት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ሰውነቱን ‹ይህን መቅደስ አፍርሱት› አላለምን? ‹በጉ መቅደስዋ ነው› ተብሎ አልተጻፈምን? ስለዚህ ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ማለት ጳውሎስ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ እንዳለው ‹‹ጌታ ሆይ ‹ዕረፍትህ› ወደተባለ ወደ ሰማያት አንተ ብቻ ተነሥተህ አትቅር የመቅደስ ሰውነትህ ማደሪያ እናትህንም ይዘህ ተነሥ›› ማለት ነው፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤ ብዙዎችን ማከራከሩ እንዴት ያሳዝናል? ክርስቶስ ‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ› ብሏል፡፡ እውነት ትንሣኤን ለወለደች እናት መነሣትዋ ትልቅ ነገር ነው? የሕይወት እናት ሕያው ሆነች ቢባል ያስቆጣልን? ሞትን የሞተው በልጅዋ አይደለምን? የሕይወትን እናት ሞት ይዞ አስቀራት ማለት ደስታ የሚሠጠው ለሞት አበጋዞች ነው፡፡ ‹‹አምላክ ያደረባት የምትናገር ታቦት ፈርሳ ቀርታለች ማለት ፣ ታቦተ ጽዮን ድንግል በሞት ፍልስጤም ተማርካ ቀርታለች›› ማለት የሚያስደስተው በማኅፀንዋ ፍሬ የተፈረካከሰው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚደንቀን መሞትዋ እንጂ መነሣትዋ አይደለም፡፡

ቅዱስ ያሬድ ‹‹የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል›› እንዳለው ሕይወትን ያስገኘች ድንግል ፣ አምላክን የታቀፉ ክንዶች ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆኑ ጉልበቶች በሞት መሸነፋቸው ያስደንቀናል፡፡ መነሣትዋ ግን የምንጠብቀው ነው፡፡ አልዓዛርን ‹አልዓዛር አልዓዛር› ብሎ ያስነሣ ጌታ ፣ በዕለተ ዓርብ በሞቱ ብዙ ሙታንን ያስነሣ ጌታ እናቱን አስነሣ ሲባል የሚቆጡ እንዴት ያሉ ናቸው?

ሁለቱ ምስክሮች የተባሉ ሄኖክና ኤልያስ ወደ ምድር መጥተው አስተምረው ከተገደሉ ‹‹ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ… በሰማይም ፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ ወጡ›› ይላል፡፡ (ራእ. 11፡4-12) ሄኖክና ኤልያስን ከምጽአቱ በፊት ዳግም ላይሞቱ ከሞት አስነሥቷቸው በጠላቶቻቸው ፊት ወደ ሰማይ የሚያሳርጋቸው አምላክ እናቱን በወዳጆችዋ ፊት አስነሥቶ አሳርጓታል ሲባል በቁጣ መቃወም ምን ይባላል?

እንደልጅዋ በራስዋ ዐረገች (Ascension) በማለትና ልጅዋ ወደ ራሱ ነጥቆ ወሰዳት (Assumption) በማለት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከቻልን የእመቤታችን ማረግ ምኑ ያከራክራል? ዝናምን ከከለከለው ኤልያስ ንጹሑን ዝናም ያስገኘችው ድንግል አትበልጥምን ፣ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረገው ሄኖክስ ይልቅ ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው እመ አምላክ አትበልጥምን?

እኛ ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹‹በሞትዋ ምድር መራራ ኀዘን ስታዝን በሰማይ ደስታ ሆነ እንዳለ›› እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገርም ሆነ ፣ በልጅዋ ሥልጣን ተነሥታ ስታርግ በሰማይ የሚኖረውን ደስታ በእምነት እናስተውላለን፡፡ ያ ደሃ አልዓዛር እንኳን ሲሞት መላእክት ነፍሱን ወደ አብርሃም አጅበው ወስደውት ነበር ፣ ኤልያስም ሲያርግ መላእክት በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረሶች ነጥቀውት ነበር፡፡ የአምላክን እናት ዕርገት ስናስብ ከዚህ በላይ ዝማሬ ይታየናል ፤ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደጻፈው ቅዱስ ያሬድም ‹በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ› እንዳለው አባትዋ ዳዊት ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› እያለ እየዘመረ ወላዲተ አምላክ ወደዚያኛው ዓለም ተሸጋግራለች፡፡ ኤልያስ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ መጎናጸፊያውን ለበረከት እንዲሆነው ለደቀ መዝሙሩ ኤልሳዕ እንደሠጠው እመቤታችንም በልጅዋ ሥልጣን ወደ ሰማይ ስታርግ መግነዝዋን (መታጠቂያዋን) ለቶማስ በመሥጠትዋ ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት አሁንም ድረስ ተከፋፍለው በታላቅ ፍቅር በረከትዋን ይቀበሉበታል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ስለ እመቤታችን መነሣት ስናስብ የምንጠይቀው ‹ተነሣች ወይስ አልተነሣችም ፤ ወደ ሰማይ ዐረገች ወይንስ ዐላረገችም› ሳይሆን ‹በሰማይ የተደረገላት አቀባበል ምን ይመስል ይሆን?› ብለን ነው፡፡ ደሃው አልዓዛር በሞተ ጊዜ መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ከተባለ የአምላክን እናት ምን ያህል አጅበዋት ይሆን? ወደ ሰማይ ማረግ ለእርስዋ ቁምነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰማይን በእጆቹ የሚይዘውን አምላክ በእጆችዋ የያዘች ሁለተኛ ሰማይ ናት፡፡ እርስዋ ወደ ሰማይ በማረግዋም ዕድለኛዋ እርስዋ ሳትሆን ሰማዩ ነው፡፡ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ከእናትና ከዙፋን እናት ትበልጣለች፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አልወለደውም ፣ አላሳደገውም ፣ አላጠባውም ድንግል ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ ስለዚህ ወደ ሰማይ ማረግዋ ክብሩ ለሰማዩ እንጂ ለእርስዋ አይደለም፡፡

እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ በእርግጥ አቀባበሉ እንዴት ይሆን? እኛ የሰው ልጆች እናታችንን ማክበርም መጦርም የምንችለው በምድር እስካለችና እኛም እስካለን ድረስ ነው፡፡ ‹እናትና አባትህን አክብር› ያለን ፈጣሪ ግን እናቱን ማክበር የሚችለው በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ነው፡፡ እናቱ ወደ እርሱ ስትመጣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንዴት ተቀብሏት ይሆን?
799 viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:46:42 + የድንግል ማርያም - ፍልሰታ - ትንሣኤ - ዕርገት +

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ ፈቃድ ከሞት መነሣት ኦርቶዶክውያን አባቶች ሲያስተምሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት በመዝ. 131፡8 ላይ ያለውን ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን ቃል ነው፡፡ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ትንሣኤ ጋር አያይዞ መጥቀስ አሁን የተጀመረ ነገር ሳይሆን ብዙ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነገር ነው፡፡

ሠላሳ ሦስተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ቀድመው የተነሡ አበው ያስተላለፉለትን የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ ታሪክ የዛሬ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በጻፈው ድርሳን ላይ ፣ በነገረ ማርያም ሊቃውንት ዘንድ Doctor of Dormition በመባል የሚታወቀው ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ ፣ ሐዋርያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በድርሳኖቻቸው ላይ ስለ ድንግል ማርያም ትንሣኤ ባነሡና በዓለ ዕርገትዋን ባከበሩ ቁጥር የሚያነቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ቃል ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? ‹ማርያም ተነሣች› የሚል ነገር አለውን? የሚለውን ጥያቄ በዚህች አጭር ጽሑፍ እንመለከታለን፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ግን አንድ ቁምነገርን እናስቀድም፡፡

በሐዲስ ኪዳን ለምናምን ፣ በወንጌል ለምንመራ ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ምን ያደርጉልናል? የሙሴ ሕግጋት ፣ የነቢያት መጻሕፍት ፣ የዳዊት መዝሙራት ለክርስቲያኖች ምን ይጠቅሙናል? ብለን ከመጠየቅ እንጀምር፡፡

የዚህ ጥያቄ መልሱ ጌታችን ‹‹በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ሊፈጸም ይገባል›› እንዳለው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ በምሥጢር የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ስለሆነ ነው፡፡ (ሉቃ. 24፡44) ‹ከሙሴና ከነቢያት ጀምሮ ስለ እርሱ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ተብሎ የተነገረላቸው የኤማሁስ መንገደኞች ‹በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትን ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?› ብለው እንደተናገሩ ብሉይ ኪዳን በእርግጥ ስለ ክርስቶስ እንደሚናገር በሚገባ ትርጉሙን ከተረዳን ልባችን በጥልቅ ተመሥጦ ይቃጠላል፡፡ ይህንን የአባቶችን ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መነፅር በዓይናችን ካጠለቅን ብሉይ ኪዳንን እያነበብን በሐዲስ ኪዳን ባሕር ውስጥ መዋኘት እንችላለን፡፡ በኅብረ አምሳል (Typology) አስቀድሞ የተነገረበትን ምክንያት (Primary application) እና ፍጻሜውን (Ultimate fulfillment) ስንረዳ በታሪክና ትንቢት ሁሉ ውስጥ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን እያገኘነው ስንደነቅ እንኖራለን፡፡

በገነት መካከል ተኝቶ ከጎኑ የሁላችንን እናት ሔዋንን ያስገኘውን አዳም ታሪክ ስናነብ በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ በመስቀል ላይ አንቀላፍቶ ከጎኑ በፈሰሰው የጥምቀት ውኃ የሁላችን እናት ቤተ ክርስቲያንን ያስገኘውን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ዕርቃኑን የወደቀውንና ካም ሲዘብትበት ፣ ሴምና ያፌት ዕርቃኑን የሸፈኑለትን የኖኅን ታሪክ ስናነብ የሞትን ጽዋ ጠጥቶ በሰው ልጅ ፍቅር ሰክሮ ዕርቃኑን የተሰቀለውንና አይሁድ ሲዘብቱበት ፀሐይና ጨረቃ ዕርቃኑን የሸፈኑለትን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡

አብርሃም የሚወደውን ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ መፍቀዱንና በግ የመሠዋቱን ታሪክ ስናነብ አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን የወደደውን እግዚአብሔር አብንና እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ ልጁን ንጹሑን በግ ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ዳዊት ጎልያድን ድል አድርጎ እስራኤልን ነጻ ሲያወጣ ስናይ ክርስቶስ ዲያቢሎስን ድል አድርጎ የሰው ልጅን ነጻ ሲያወጣ ይታየናል፡፡ እስራኤል በበረሃ ተጉዘው በበትር ከተመታው ከዓለት ውኃ ፈልቆላቸው ሲጠጡ ስናይ በዕለተ ዓርብ ጎኑን በጦር ተወግቶ በደሙ ጥማችንን ያረካልን መድኃኔ ዓለም ይታየንና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ‹ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ› እንላለን፡፡

ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተን ደብተራ ኦሪትን ብንጎበኝ እንኳን ክርስትናችን አይለቀንም፡፡ በመሠዊያ ላይ የሚሠዋውን በግ ስናይ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕሊናችን ይመጣብናል፡፡ ወደ ድንኳኑ ዘልቀን በመቅረዙ ላይ መብራት ሲበራ ስናይ እውነተኛው ብርሃን ክርስቶስ ፣ ዕጣን ስናይ የኃጢአት ሽታችንን ያራቀልን ክርስቶስ ፣ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ስናይ በመለኮቱ መለወጥ የሌለበትን ክርስቶስ ፣ መናውን ስናይ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ እየታየን እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ‹‹ልባችን እየተቃጠለ ለካስ ኦሪትና ነቢያት ሁሉ የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ነበረ?›› እንላለን፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ከሆንን ደግሞ ጌታን ባገኘንበት ሥፍራ ሁሉ እመቤታችንን ፍለጋ ማማተራችን አይቀርም፡፡ አዳምን የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ስናየው አዳምን ያለ አባት ያስገኘችዋ መሬት ያለ ወንድ ዘር የወለደችውን ድንግል ሆና ትታየናለች፡፡ አብርሃም የሠዋውን ከዱር ቀንዱ እንደታሰረ የወጣ በግ ስናይ የድንግልናዋ ማኅተም ሳይፈታ የወለደችው የበጉ እናት ትታየናለች፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተንም አናርፍም ፣ እርሱ መብራት ሆኖ ሲታየን እርስዋ መቅረዝ ትሆንልናለች፡፡ እርሱ ዕጣን ሲሆን እርስዋ ማዕጠንት ትሆናለች ፣ እርሱ ታቦት ሲሆን እርስዋ ታቦቱ ያለበት ቅድስተ ቅዱሳን ትሆናለች ፣ እርሱ ጽላት ሲሆን እርስዋ የጽላቱ ማደሪያ ታቦት ትሆናለች ፣ እርሱ በጽላት ላይ የተጻፈው ቃል ሲሆን እርስዋ ጽላት ትሆናለች ፣ እርሱ የተሰወረ መና ሲሆን እርስዋ የመናው መሶበ ወርቅ ትሆናለች፡፡ ለሰብአ ሰገል ‹ሕጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት› እንደተባለላቸው እኛም በሔድንበት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ የጌታችንን ምሳሌ ባነበብንበት ሥፍራ ሁሉ እናቱንም እናያታለን፡፡

እውነቱን ለመናገር ለመመርመር ትዕግሥት ላለው ሰው ስለ ክርስቶስ በሚናገሩት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንኳን ድንግል ማርያምን ቀርቶ ከሐዲው ይሁዳንም ማግኘት ይቻላል፡፡ ዮሴፍ የክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ዮሴፍ በሃያ ብር እንዲሸጥ ሃሳብ ያቀረበው ወንድሙ ይሁዳ የአስቆሮቱ ይሁዳ ምሳሌ አይደለምን?

ፍልስጤማውያንን ድል ያደረገው ናዝራዊው ሶምሶን የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ሶምሶንን እየሳመች አሳልፋ የሠጠችው ደሊላ ስሞ የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ አይደለችምን? አባቱን ለመግደል ሲያሴር ኖሮ መጨረሻ በዛፍ ላይ ተሰቅሎ የሞተው አቤሴሎምስ ጌታውን አሳልፎ ሠጥቶ ተሰቅሎ የሞተው የይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ‹የታመንሁበት የሰላሜ ሰው እንጀራዬን የበላ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ› ተብሎ የተነገረው ስለ ይሁዳ አይደለምን? ብሉይ ኪዳን እንኳን አምላክን ስለወለደችው ቅድስት ድንግል ቀርቶ አምላኩን ስለሸጠው ይሁዳም ትንቢት ተናግሯል፡፡

አሁን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ! ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ብሎ ዳዊት ስለ ቤተ መቅደስ መሠራትና ታቦቱም ወደ ቤተ መቅደሱ ስለመግባቱ የዘመረው መዝሙር ፣ ልጁ ሰሎሞንም መቅደሱ ተሠርቶ ሲያልቅ ደግሞ የዘመረው ይህ መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? (2ዜና 6፡41) ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ከጥንት ጀምሮ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ጋር የሚጠቅሱት ዳዊት ስለ መቅደሱ መሠራትና ስለ ታቦቱ መግባት የተናገረ መሆኑ ጠፍቷቸው ነው? ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› የሚለውን
694 viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 18:13:56 ፆመ ፍልሰታ
(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ለማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሀሴ 1እስከ15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው

ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች

የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን

@ANASIMOS_TUBE
899 viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ