Get Mystery Box with random crypto!

NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

የቴሌግራም ቻናል አርማ nisirbroadcasting — NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel) N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nisirbroadcasting — NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)
የሰርጥ አድራሻ: @nisirbroadcasting
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.71K
የሰርጥ መግለጫ

NISIR International Broadcasting Co. is an impartial and independent media agency operates as television; radio; social media & multimedia production.
Facebook: https://www.facebook.com/NISIR-International-Broadcasting-Corporation-105276671420707

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 248

2022-08-30 09:38:18
የሐይቅ ከተማ አስተዳደርና የተሁለደሬ ወረዳ የጸጥታ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦

- የባለ 3 እግር ተሽከርካሪና አነስተኛና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

- የመጠጥ ግሮሰሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።

- ህግ ከሚያስከብሩ የጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በየጫት ቤቱና መቃሚያ ቤቶች በማንኛውም ሰዓት መሰባሰብ፤ በነዚህ አካባቢዎች መቃምና መገኘት ተከልክሏል።

- ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ በዘመቻ ሰበብ ከመንግስት እውቅና ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጥ አልባሳት፣ ትጥቅ፣ የጦር መሳሪያና የመሳሰሉትን በማንኛውም ሰዓት በከተማው ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- ተፈናቅይም ሆነ ሌሎች ወደከተማው የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት በሚያገኙበት ተቋም ራሳቸውን የመግለፅ እንዲሁም ተቋማቱም መጠየቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- በከተማው አሉባልታ መንዛት፣ ህዝቡን በማሸበር አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ፣ የግል ንብረት እና እቃ እንዲሰብሰብ ማነሳሳት በጥብቅ ተከልክሏል።

ነዋሪዎች ማንኛውም ጥቆማ ካላቸው በ 033 222 0481 ፣ 033 222 0955 ፣ 0333 222 0006 በመደወል መጠቆም ይችላሉ ተብሏል።
3.6K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:32:51 ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክርቤት በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!
እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በድልና በብቃት በብልሃት ና በጥበብ አሸባሪውን ትህነግ/ህወሐት እና ታሪካዊ ጠላቶቻችንን እያሸነፈች የምትሻገር እንጂ በፈተናዎች ብዛት ተደናቅፈን የምንወድቅ ኢትዮጵያውያን አይደለንም። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም የሚዘረጉ እጆች ያለን እንጂ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚመጣ ማንኛውም የሰማይም ይሁን የምድር ሃይል ሽንፈትና ውርደት ተከናንቦ የሚመልስ ታሪክ ያለን ህዝቦች መሆናችንን የአደባባይ ሚስጢር ነው ።
ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት የአሸናፊነት ምልክት በመሆኑ አሁናዊ የአሸባሪው ህወሃት ሦስተኛው የጦርነት ትንኮሳዎች የመጨረሻው የመሞቻው ጊዜ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የድልና የትንሳኤ ጊዜ ነው።
ስለዚህ ወራሪው ቡድን የተሰጠውን የሰላም አማራጮችን እያጨናገፈና እያፈረሰ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ተጣብቆ ደሙን እየመጠጠ እና በውር ድንብር ጉዞ ለመኖር አማራና አፋር ክልሎችን በመውረርና በማዋረድ ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚል ሰይጣናዊ ግቡ ለማሳካት በህዝባችን ያልፈነቀለው የሴራ ድንጋይ: ያልፈፀመው ደባ የለም።
ይሁን እንጂ መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን ወራሪ ቡድን ለአንዴና መጨረሻ እስከወዲያኛው እንዲያሸልብ ከወትሮው በተለየ ኢትዮጵያዊነታችንን አጠናክረን እንደ አንድ ሰው አስበን እንደ አንድ ቃል ተናግረን ለታሪካዊ ጠላቶቻችንን ውርደት አከናንበን በዲፕሎማሲው ተሰሚነቷ የገነነች በኢኮኖሚው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ መላው ህዝባችን ድካ የለሽ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ታሪካዊ ጥሪ ስናቀርብለት ትልቅ ኩራት ይሰማናል።
የተከበራችሁ የፀጥታ ጥምር ሃይሎች፣ የፖለቲካ አመራሮችና መላው ህዝባችን ዛሬም እንደትላንቱ የማያዳግም እርምጃ በአሸባሪው ህወሃት እና በታሪካዊ ጠላቶቻችን የመረረ ጥላቻ ይዘን የመረረ ምት አሳርፈንና አሳፍረን በሁለንተናዋ የተከበረችና የተፈራች ሀገር ለመገንባት ትግላችን ከውስጥ ባንዳ እስከ ውጭ ጠላት ያለውን ሀገር የማፍረስ ቅንጅት አፍርሰንና ደርምሰን በሁለንተናዊ የበለፀገች ኢትዬጲያ እውን ለማድረግ የሚከተሉትን ተግባራትን እንድንሰራ የፀጥታው
ምክርቤት ያቀረበው ጉዳይ:-
1.ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች ከመንግስት ተሽከርካሪወች ውጭ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጧቱ12:00 እስከ ምሽት 1:00 ብቻ እንዲሆን የወሰነ መሆኑ ታውቆ ይህን ተላልፎ የተገኘ የተሽከርካሪ ባለ ንብረትና አሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ የሚሰድ ይሆናል!!
2.መላው የዞናችን ህዝብ ከዚህ በፊት በተደራጀበት የመንግስት አደረጃጀት መሠረት አካባቢውን ከሰር-ጎገብና ከውስጥ ባንዳ ያላለሰለሰ ትግል በማካሄግድ ከጠላት አስተሳሰብና ተግባር የፀዳ ከባቢ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናቀርባለን!!
3.ማንኛውም ሀገሩን እንዳትፈርስና በጠላት እንዳት ወረር የሚፈልግ ሰው ሁሉ (ተቆርቋሪ) ፀጉረ-ልውጥ ሲያገኝ በፍጥነት በአካቢው ለተሰማራው የፀጥታ መዋቅር የመጠቆም:የመያዝ:ወደ ህግ አካላት እንዲያስረክቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን !!
4.በወረዳ የቀበሌ ከተሞችን ጨምሮ ባለሆቴሎች ባለ ምግብ ቤቶች ማንነቱ/አድራሻው/ ያልታወቀ ሲያጋጥም ለሚመለከተው የፀጥታ አካል እንድታስረክቡ
ከዚህ ውጭ በመሆን ማንነቱ ያልታወቀ፣ ያስጠጋ፣ ያሳደረ፣ ለጠላት ተባባሪ በሆነ አካል ላይ እርምጃ ይወሰዳል።
5.በተለይ በከተሞች አካባቢ ተከራይተውና አከራይተው የሚኖሩ ዜጎች በፍጥነት ተመዝግበው በአቅራቢያ ላለው የፀጥታ ተቋም ሪፖር እንድታደርጉ።
6.በዞናችን ጠላት የሚኖርባቸው አጎራባች ወይም አዋሳኝ ቦታዎች ቀይ መስመር መሆናቸውን ታውቆ በእነዚህ አካባቢ የእርሻና እርባታ ያላቹሁ አልሚዎቻችን ከጧቱ 12:00 እስከ ቀኑ 12:00 ብቻ እንቅስቃሴ የምታደርጉ መሆኑን እያሳሰብን ለጉልበት ስራ የምትወስዷቸውን አካላት ማንነት በማረጋገጥ ለሚለከተው የፀጥታ አካል አስመዝግባቹሁ የምታሰሩ ሆኖ ይህን የተላለፈ ባለ ሃብትም ይሁን ወኪል በህግ ይጠየቃል።
7.በዞናችን በሁሉም አካባቢዎች የሰው እንቅስቃሴ እስከ ምሸቱ 3:00 ብቻ መሆኑ ታውቆ እነዚህን ክልከላዎችን በሚተላለፍ አካል ላይ ህግ እንዲያስከብር ለጸጥታ መዋቅሩ ትዛዝ ተሰጥቷል።
8.በሁሉም የዞናችን አካባቢወች አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ተከልክሏል።
9.በዞናችን ውስጥ ያለ የታጠቀ ሃይል በሙሉ ካለበት ወረዳ ከተማና ቀበሌ አስፈላጊውን ወታደራዊ ዝግጅት አድርጎ እንዲጠብቅ ታዟል።
10.መላው የዞናችን ህዝብ ለፀጥታ ጥምር ሃይሎች የተለመደውን ደጀንነቱን በአስተማማኝነት እያጠናከረ እንዲሄድ ጥሪያችንን እናቀርባለን!
በመጨረሻም በጠላት ላይ የመረረ ጥላቻ በመያዝ እና በመዋጋት ክብራችንን እና ነፃነታችንን እንጂ ከቀያችን ሸሽተንና ተፈናቅለን ህልውናችንን አናረጋግጥም እና መታገልና መደራጀት ብቻ ነው አማራጫችን!!
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች!!
ነሐሴ23/2014 ዓ.ም
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
ሰቲት ሁመራ
3.3K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:32:40
2.9K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:39:58
#መረጃ
በምስራቅ ወለጋ ዞን በአሙሩ ወረዳና በኪረሙ ወረዳ ስር በሚገኙ የአጋምሳና በሐሮ አድስ አለም ቀበሌ መካከል የኦነግ ሸኔ አሸባሪ ዘራፊ ቡድን የመከላከያ ሠራዊት መውጣታቸውን ተከትሎ በኗሪዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰምቷል፣
ንሥር ብሮድካስት
ነሃሴ 24/2014

የኦነግ ሸኔ ከጭፍጨፋው በተጨማሪ በአጋምሳ ቀበሌና በጃቦዶበን ቀበሌ ኗሪ የሆኑ ስምንት የአማራ ተወላጆችን በተለይም ሴትና ህጻናት፣ አግቶ በገንዘብና በመሳሪያ እየተደራደረባቸው መሆኑን የታጋች ቤተሰቦች ገልፀዋል።
በአከባቢው ከኪረሙ ወረዳ ጀምሮ እስከ አባይ ወንዝ ባለው አከባቢዎች ላይ የተለያዩ የሸኔ ማሰልጠኛዎች እና መጋዘኖች ያለበት በመሆኑ መንግስት በአስቸኳይ ለቀጠናው አስተማማኝ ሐይል እንድያስቀምጥልን ሲሉ ኗሪዎቹ በአጽንኦት አሳስበዋል።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
3.1K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:10:22
#ሰበር መረጃ
በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በአሙሩ ወረዳ፣በሀሮ ወረዳ፣ በጃርደጋ
ጃርቴ፣በኪረሙ፣በደንጎሮ እና በተለያዩ ወለጋ ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች እና
አጠቃላይ ወለጋ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች የይድረሱል ጥሪ እያሰሙ
ነው።
ንሥር ብሮድካስት
ነሃሴ 24/2014
መከላከያ ቦታውን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት አሸባሪው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ
ወለጋ ላይ ሰፊ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል። ሰኞ 23/12/2014 አገምሳ ወረዳ ላይ የሚኖሩ
አማራዎችን ጨፍጭፈዋል። እናም በአሙሩ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አማራዎች ላይ ከባድ ተኩስ ነው
የዋለው ብዙ አማራዎችም መሞታቸው ነዋሪወች ለንሥር ብሮድካስት አሳውቀዋል።
ስለሆነም በወለጋ የሚኖሩ አማራዎች እባካችሁ ህይወታችን ታደጉን ብለዋል። ጠባቂ አልባው የአማራ ህዝብ እያለቀ ነው።
ፍትህ ለወለጋ አማራዎች?
ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
3.4K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:51:47 ውድ ተመልካቾቻችን;

ስለ ጦርነቱ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ እንድንሰጣችሁ አንዳንዶች በውስጥ መስመር እየጠየቃችሁን ነው::

በጦርነቱ ዙሪያ መልካም ነገር የለም! ወያኔ አሁንም እየሾለከች ነው:: ይዞታዋን እያሰፍች መሆኑን ሁሉም አማራ በመረዳት ቆም ብሎ እንዲያስብና ጥያቄም እንዲጠይቅ እንመክራለን::

የሶሻል ሚዲያውን ፕሮፓጋንዳ እንቶወው!
የ2ኛውን ጦርነት ማስታወስ ለአሁኑም በቂ ነው::

እውነታው ሌላ ነው:: ችግሩም ከላይኞቹ ነው::

ይህ ጦርነት ፈጣን መፍትሄ ይሻል::
3.9K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:25:16 ከንሥርእንግዳ --ክብር ስለሚገባው ክብር እንሰጣለን
ነሐሴ 23/2014
-----~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ክብር ስለሚገባው ክብር እንሰጣለን ።

የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ግዳጅ አንድ እና አንድ ነው።
ዕርሱም #የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ!!

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
4.2K viewsedited  14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:25:12
3.9K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:37:53 በኢትዮጵያ ህዝብና በአማራ ህዝብ ላይ እንደቀለደው ቀልዱን ገብተን ከአውድማው ላይ እንተያያለን _ፋኖ አዛዥ ምሬ ወዳጆ

4.1K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:13:58
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ስንታዬሁ ቸኮል በዛሬው የፍርድ ቤት ቀጠሮአቸው በ10,000 ብር ዋሰ እንዲፈቱ ፍርድቤቱ መወሰኑ ታውቋል ነገር ግን ተፈፃሚነቱን የምንከታተል ይሆናል።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
3.9K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ