Get Mystery Box with random crypto!

NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

የቴሌግራም ቻናል አርማ nisirbroadcasting — NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel) N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nisirbroadcasting — NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)
የሰርጥ አድራሻ: @nisirbroadcasting
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.71K
የሰርጥ መግለጫ

NISIR International Broadcasting Co. is an impartial and independent media agency operates as television; radio; social media & multimedia production.
Facebook: https://www.facebook.com/NISIR-International-Broadcasting-Corporation-105276671420707

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 243

2022-09-04 09:25:50

1.5K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 03:13:21 NiSiR International Broadcasting Co. pinned a photo
00:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 03:08:39
አስቸኳይ መረጃ _የደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ አስተዳደር በፋኖ ላይ ወከባ እየፈጠሩ ነው


የደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ አስተዳደር በፋኖ ካምፕ ላይ ጥቃት እፈፅማለሁ እያለ እየዛተ ነው አስቸኳይ እንዲቆም ፋኖወቹ ጠይቀዋል።

ንሥር እንግዳ
ነሃሴ 29/201

በደቡብ ወሎ የምስራቅ አማራ ብ/ጄ/አሳምነው ፅጌ ብርጌድ የቁስለኛ ማገገሚያ እና የሬሽን ካምፕ የሆነውን የደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ አስተዳደር ብትችሉ ዛሬ አለበለዚያ ነገውኑ ካለቀቃችሁ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ከኋላ ያለውን የፋኖ የደጀን ሀይል በማስፈራራት ላይ ነው። ተልኮውም ግልፅ አይደለም ተብሏል። አሁን ሀገር በገመድ ተወጥራ ባለችበት ሰዓት ፋኖ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ተሰልፎ ህይወቱን እየገበረ ባለበት ወቅት አሁንም መንግስት የተባለው አካል ችግር እየፈጠረ መሆኑን ህዝብ ይወቅ ሲሉ የምስራቅ አማራ ፋኖ የብ/ጀ/አሳምነው ፅጌ ብርጌድ የደጋው መብረቅ ፋኖወች ለንሥር ብሮድካስት አስቸኳይ መልክት ልከዋል። እኛም ህዝብ ጉዳዮን በትኩረት በመመልከት ለሃገርና ለወገን ሲሉ በግምባር እየተዋደቁ የሚገኙትን የፋኖወች ካምፖች በማስከበር ህዝብ እራሱ ጥበቃ እንዲያደርግ መልክታችን ነው።

በፋኖ ላይ በመንግስት ሃይሎችም ሆነ አስተዳደር ክፍሎች የሚፈፀሙ አላግባብ ወከባወች የአማራን ችግር ከማባባስና ለጠላት ምቾትን ከመፍጠር የዘለለ ሚና ስለማይኖራቸው የአማራ አመራሮች ለችግር መፍትሄ ፈላጊ እንጅ ችግር ፈጣሪ ባለመሆን የአማራው ህዝብ ወደ ሰላሙ እንዲመለስ እንዲሰሩ እንመክራለን።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
62 views00:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 23:57:19
#መረጃ _ወለጋ
ነሃሴ 29/2014
*****************************************
ይህን መልክት ልውውጥ በደንብ ተመልከቱ! ሶስት ባንኮችም ተዘርፈዋል።

ትናንት አማራን ሀሮ ቡሉቅ ወረዳ ላይ ሲጨፈጭፉ ዋሉና ጀግናው የኦሮሞ ስራዊት እያሉ ሲዘግቡ ዋሉ። በዚሁ ቀን ማለትም 27/12/2014 ከጧት ጀምሮ በነበረው ጭፍጨፋ 7 የተረጋገጡ አማራወችን የገደሉ ሲሆን በቀን 28/12/2014 ለቃቅመው በአማራው አማራ ጨፈጨፈ ብለው ማሰራጨት ጀመሩ። እየሆነ ያለው ጉድ ይህ ነው።
ጦጣ በልታ በልታ አፏን በሌላ ወገን አበሰች እንደሚባለው
እውነት የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ነኝ ካለ ይህን ያስቁም እንላለን።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
499 views20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 23:28:40
ንሥር ስሞታ

ነሐሴ 29/2022
*************

ምንም አይነት ህጋዊነት ማህተብ በሌለዉ ደብተር የሮንድ በጭስ በወር 100 ብር እያሉን ነው::
********

ቦታዉ ሰበታ ከተማ ነዉ:: አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ቦታዉ አለምገና ቀበሌ 02 የህግ አካል ነን የሚሉ ምንም አይነት ህጋዊነት ማህተብ በሌለዉ ደብተር ይዘው የሮንድ በጭስ በወር 100 ብር እያሉ ማህበረሰቡን መከራ እያሳዩ ይገኛሉ። ለበዓል መዋያም ይሁን አናቅም:: እባካችሁ የሚመለከተው አካል ምላሽ ይስጥ ብለዋል::

ተመልካቾቻን ይህን መልክት ለአካባቢው አስተዳደር እንድታደርሱ እንላለን::

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
609 views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:29:39 ንሥር እለታዊ ዜና _ Sep 3/2022

1.7K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:27:16
ከወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ!!
የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የሰዓት እላፊ ገደብ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ በማስፈለጉ የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
1. ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በከተማችን በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡
2. ከተፈቀደላቸው የመንግስት የፀጥታ አባላት ውጭ የሰራዊቱን አልባሳትን መልበስ የተከለከለ ነው፡፡
3. ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የከተማውን ማህበረሰብ የሚያውኩ አሉባልታዎችን በሚዲያዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ማዋከብ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
4. በከተማችን የሚገኙ የራያና ቆቦ ከተማ ተፈናቃዮች ውጭ ሌላው አካል ወደ መጣበት አካባቢ እንዲመለስ በጥብቅ እናሳስባለን
5. በከተማችን የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ የንግድ ተቋማት እና የመሳሰሉትን መዝጋት ፍጹም የተከለከለ ነው፡፡
6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ለፀጥታ ስራ ትብብር ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት። ነገር ግን ተሸከርካሪን የሚሸሽግ፣ የሚያሸሽ፣ ሆን ብሎ ተበላሸ በሚል ላለመተባበር ጥረት የሚያደርግ ግለሰብ እና ድርጅት ተጠያቂ ይሆናል።
7. የመኖሪያ ቤትና የመኝታ አልጋ የሚያከራይ ግለሰብ የተከራዮቻችሁን ማንነት የመለየትና የታደሰ መታወቂያ ስለመያዛቸው የማረጋገጥ ግዴታ ሲኖርባችሁ አጠራጣሪ ጉዳይ ሲኖር ለጸጥታ አካል ሪፖርት የማድረግ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ በግልፅ እናሳስባለን
8. ፀጉረ ልውጥ ሰው የሚያገኝ ግለሰብ በቅርቡ ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል
9. ከነሀሴ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን።
10. ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ አካባቢውን በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት
11. አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት መፍጠር፣ በሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት፣ በማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘት በህግ ያስጠይቃል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ ያለበት መሆኑንና ይህን ውሳኔ የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ በአጽእኖት እናሳውቃለን፡፡
ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም.
ወልድያ#
ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
1.7K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 13:00:28
በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሊረዳን አልቻለም ብለዋል:: መኖሪያ የሌለን ከ300,000 እስከ 500,000 ብር ክፈሉ እየተባልን ህገወጥ በሆነ መልኩ በየቦታው እየታደን ነው:: ህጉ የሚጠይቀውን ለመፈፀም እንድንችል የኢትዮጽያ ኢምባሲ እየረዳን አይደለም:: ችግሩ በግልፅ ሰፍቶ ማደን; እስት ቤት መወርወርና መግደል ተግባራቸው መኖአል::

እባካችሁ ትኩረት ሱዳን ካርቱም ለምንገኝ መንግስት ይድረስልን ብለዋል::
**********

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
1.6K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:25:11 ንሥር እረፋድ ዜናዎች _Sep 3/2014

1.7K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 10:33:29 በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን የማይናወጥ አቋም በየጊዜው ስትገልፅና ይህንኑ አቋሟን በተግባር ስታረጋግጥ መቆየቷ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡

ሆኖም ስለሰላም የተዘረጉትን እጆች አሻፈረኝ በማለት ለ3ኛ ዙር በሃገራችን ላይ የጥፋት በትሩን የዘረጋው አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ተገደን ለመመከት ወደመከላከል መግባታችን ይታወቃል፡፡

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጰያውያን ላይ ተነግረው የማያልቁ እልፍ አዕላፍ መከራና ሰቆቃ ሲፈፅም የኖረ እኩይ እና ፀረ ህዝብ ቡድን በመሆኑ የጭካኔ በደሉ በበረታባቸው ኢትዮጵያውያን የጋራ ክንድ ከስልጣን የተወገደው ይህ የአሸባሪ ስብስብ አሁንም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብሮ አገራችንን የማፈራረስ ግብ አንግቦ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ሆኖም በጀግናው የመከላከያ ሰራዊቻችንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አኩሪ ተጋድሎ የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ላንቃ እየተዘጋና ወረራውን በብቃት እየተመከተ ይገኛል፤ ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልቅ ክብርና አድናቆት አለው፡፡

ምንጊዜም ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን መሆናችንን በተግባር እያረጋገጥን ሃላፊነታችንን በብቃት እንወጣለን፡፡

በተመሳሳይ ዛሬም እንደ ትናንቱ በጦርነቱ ግንባር የአማራና የአፋር ንፁሃን ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ተግባራዊ በማድረግ እንቀጥላለን፡፡

ይህ እኩይ ቡድኑና ተላላኪዎቹ አልሆነላቸውም እንጂ በተደጋጋሚ አዲስ አበባንም ለማተራመስ የሽብርና የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ ለመክተት የማያባራ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ይህንኑ ቅዠታቸውን ለመፈፀም ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡

በተለይም በሃሰት ፕሮፖጋንዳ፤ ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጩና አንድነታችንን የሚበትኑ የተፈበረኩ መረጃዎችን በማሰራጨት ፤ በከተማዋ ውስጥ የሽብር ቡድኖቹ የህወሓትና የኦነግ ሸኔን የተለያዩ የፅንፍ አስተሳሰብ የሚረጩ አባላትን በማስረግና የጥፋት ሴሎችን በማደራጀት ፤ ሰላማችንን ለማወክ፤ የጸጥታ ስጋት ለመፍጠርና የእኩይ እቅዳቸውን ለማሳካት በግልጽ እንቅስቃሴ እያካሄዱ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለረጅም ዘመናት በዘረጋው የሌብነትና የዝርፊያ አደረጃጀቶችና አሰርጎ ባስገባቸው ተላላኪዎች ተጠቅሞ በተለያዩ ወንጀሎችና የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈፀም፤ ህብረተሰቡን በማማረር መንግስት ላይ ጫና ማሳደር በሚለው ያረጀ ስልት ለመጠቀም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ስልቶችም መካከል፤ በየቦታው ህገ ወጥነትን ማስፋፋትና የመሬት ወረራ እንዲካሄድ በማድረግ፤ የፖለቲካ ግብ ያላቸው የደረቅ ወንጀሎች እንዲስፋፉ በማድረግ፤ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲባባስና ህዝቡ አንዲማረር ለማድረግ የቀን ቅዠታቸውን ለማሳካት ግብ ያደረጉ እንቅስቃሴዎቻቸው በየአካባቢው መታየት ጀምረዋል፡፡

ይህ ከህዝብ ልብ ተተፍቶ የወጣ ሃይል ፤ በህዝብ ውስጥ ሊሸሸግ የሚስችለው አንዳችም እድል እንደሌለው የታወቀ ቢሆንም በማናቸውም ሁኔታ የዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ ሆነው ያገኘናቸው አካላትም ሆኑ ሰዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡

የከተማችን ነዋሪዎችም ወቅታዊ የኑሮ ጫናን ለማቃለል ለበዓል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የከተማ አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲቀርብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን በማወቅ ፤ ለህገወጦች እቅድ ተጋላጭ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ እንወዳለን!

በተለይም ቀጣዮቹ ሳምንታት በርካታ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት በመሆኑ እነዚህ በአላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የከተማችን ነዋሪ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አካባቢውን ብሎም ከተማውን በንቃት ተደራጅቶ እንዲጠብቅ ፤ ከፀጥታ ሃይሉ እና ከሰላም ሰራዊቱ አደረጃጀት ጋር በመተባበር እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በየአካባቢው በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩ፤ ፀጉረ ልውጦችን፤ የሽብር ወሬ የሚነዙና የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም የተለያዩ ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎቶች እንዲስተጓጎሉ የሚያደርጉ አካላትን ለፀጥታ ሃይሉ በመጠቆም እንዲሁም በማጋለጥ አገራዊ ሃላፊነታችንን እንድንወጣም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም የከተማችን ህዝብና አስተዳደር ከግንባር እስከ ደጀን ለሰራዊታችን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን እያረጋገጥን ፤ ሁላችንም በየተሰማራንበት ውጤታማ በመሆን የእኩይ ሴራዎችን እያከሸፍን ፤የመዲናችንን ሰላም ዘላቂነት በማረጋገጥና ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ በተደራጀና በተቀናጀ አመራርና ከህዝባችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን መስራትን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡

እውነትና ሃቅ ከኢትዮጵያ ጎን ነው፡፡ ኢትዮጵያ የያዘቸውን ምንጊዜም የማይናወጥ የፍትሃዊነትና ፤የሰላማዊነት አቋም የአሸናፊነት ጋሻዎቻችን ናቸው፡፡

ከሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እስከ ቅርብ ባንዳዎች ድረስ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ፣ የሞከሩት ሁሉ አሸንፈን መልሰናቸዋል። ዛሬም እንመልስላቸዋለን!!

አዲስ አበባ በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብርና አንድነት ሃላፊነቷን በብቃት ትወጣለች!!

ኢትዮጵያ ድል እያደረገች ትቀጥላለች!!

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2.1K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ