2022-09-01 16:49:04
"ጦርነቱ የአማራ እና የትግራይ ህዝብ ጦርነት አይደለም ። በጦርነቱ የአማራ ልዩ ሀይል፤ ፋኖ እና ሚሊሻ ኢላማ ያደረገ ውግያ ላለማድረግ እና በሂደቱ የተማረኩ ካሉ ወድያው ለመልቀቅ ወስነናል።"
የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ)
ንሥር ብሮድካስት
ነሃሴ 26/2014 ዓ.ም
በትግራይ ህዝብ ላይ የተከፈተው ጦርነት የአማራ እና የትግራይ ህዝብ ጦርነት ባለመሆኑ በጦርነቱ የአማራ ልዩ ሀይል፤ ፋኖ እና ሚሊሻ ኢላማ ያደረገ ውግያ ላለማድረግ እና በሂደቱ የተማረኩ ካሉ ወድያው ለመልቀቅ መወሰኑን የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) ገለፁ።
የትግራይ ሰራዊት ዋና ኣዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ በወቅታዊ ጉዳይ ዙርያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት የትግራይ እና የአማራ ህዝብ ጦርነት አለመሆኑን ገልፃል። የትግራይ ሰራዊት ለህዝቡ ህልውና ሲለ ተገዶ እንጂ የአማራ መሬት የጦርነት አውድማ የማድረግ ፍላጎት የለውም። የሁለቱም ህዝቦች ጦርነት ባለመሆኑም የአማራ ልዮ ሃይል፣ፋኖ እና ሚሊሻ ኢላማ ያደረገ ጦርነት ላለማካሄድ ወስነናል ብሏል።
በደቡባዊ ግንባር የነበረው ጦርነት 5000 ሺህ የጠላት ሰራዊት ተሟርካል። ከዚህ መሃል የአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ ወይ ሚሊሻ ስለመኖራቸው ሲጠየቁ ቀድሞ በያዙት የተሳሳተ የትግራይ ሰራዊት ለይቶ ይመታል የሚል ትርክት ራሰቸውን ያልገለፁ ይኖራሉ። 8 ራሳቸው የገለፁ ግን ወዲያው ተለቀዋል ብሏል። አሁንም ካሉ እንለቃለን፣ ሲማረኩም ወደ ጦር ምርኮ ሳይገቡ ወዲያው እንዲለቀቁ ተወስኗል። በመሆኑም የአማራ ታጣቂዎች ጥምር ሃይል ከተባለው አደረጃጀቱ ራሳቸውን ሊያርቁ ይገባል ብሏል።
የአማራ ህዝብ እየተፈናቀለ ይገኛል። ይህ ያሰዝናል ፣ ህዝቡ ቀየው የሚለቅበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። በመሆኑም በቤቱ ሊቀመጥ ይገባል። የትግራይ እና አማራ ህዝብ ተጎራብቶ መኖሩ ስለማይቀር የተፈጠረው ቀውስ ለማከም ሁሉም ሊሰራ ይገባል ብሏል ታጋይ ታደሰ ወረደ ።
የአማራ ሊህቃን ብስለት ሮቆባቸዋል ያለው ታጋይ ታደሰ ወረደ ከዚህ በፊት የሆነው ሆኗል። ከዚህ ብኋላ ግን ሌላ ቁስል መፍጠር ሊያበቃ ይገባል። በመሰረቱ የትግራይ ህዝብ ጠላት የአማራ ህዝብም ጠላት ነው ብለዋል።
የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ ለዓፋር ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት የትግራይ እና የዓፋር ህዝብ የማይነጣጠሉ ናቸው። በጠላቶች ተፈጥሮ የነበረው ችግርም ህዝቡ እየተነጋገረ ወደ ቀድሞ ሰላም እየተመለሰ ነው ብሏል።
ለሱማሌ ህዝብም ጥያቄዎቻቹሁ እንረዳለን፣ የሶማሌ ልዩ ሃይል ከዚህ ቀደም ላደረከው ነገር እናመሰግናለን አሁንም በትግራይ ጦርነት ላለመሳተፍ እያሳየሀው ያለው ተቃውሞ አጠናክረህ ልትቀጥልበት ይገባል ብሏል።
ሰፊ የኦሮሞ ሃይል በትግራይ ጦርነት ለማሳተፍ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም እየከሸፈ ይገኛል። ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እና ሌሎች ታጋዮች ጋር ያለንን ትብብር እናጠናክራለን ያለው ወዲ ወረደ የኦሮሞ ህዝብ እያደረገው ላለው ትግል ምስጋናውን አቅርቧል።
ከመከላከያ ሰራዊት አባላትም ከባእድ ጋር ሆናችሁ የትግራይ ህዝብን በመውጋት ተገፍቶ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ እያደረጋቹ ትገኛላቹ። የአሁኑ ጥቃትም የመጨረሻ ሊሆን ይችላል፣ በዚህም የታሪክ ተጠያቂዎች ናቹ ብሏል።
ነሃሴ 26/2014 ዓ/ም
ድምፂ ወያነ ትግራይ
ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
1.5K views13:49