2022-09-04 12:39:06
ከንሥር እንግዳ-የውጭ ባንኮች
ነሐሴ 29/2014
****************
መንግስት ሊበራል ነኝ ለማለት እየሄደበት ያለው ውሳኔ በፍፁም ኢኮኖሚውን ሊያሳድገው አይችልም።
በመሰረታዊነት የሃገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ተወስነው የሚገኙት አንድ ቦታ ላይ ብቻ መሆኑ የፋይናንስ ተደራሺነቱን ኢፍትሃዊ አድርጎታል።
በመሆኑም የውጭ ባንኮች በዚህ ደረጃ ሃገር ውስጥ ገብተው እንድሰሩ ፍቃድ ከመስጠት ይልቅ የሃገር ውስጥ ባንኮችን በስርዓቱ መደገፍ እና ከፓለቲካ እና ከ ባለ አክሲዮኖች ጣልቃ ገብነት እንዲወጡ በማድረግ በሙያቸው አስተማማኝ የዕውቀት ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ጠቃሚ ነበር።
ነገር ግን መንግስት ከዶላር እጥረት እና ከውጭ እዳ ስረዛ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ተፅዕኖ ስላሳደሩ ብቻ ይህንን ውሳኔ መስጠት በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።
ስለሆነም የፋይናንስ ተቋማት ችግራችን መነሻው አብዛኛው ማህበረሰባችን በቂ ግንዛቤ የሌለው መሆኑ እና አሁንም ቢሆን የቁጠባ ሁኔታዎች በባህላዊ መንገድ እየተመሩ በመሆኑ ነው።
ይህንን ሁኔታ በጥልቀት ማስገንዘብ የፋይናንስ ተቋማት ድርሻ ቢሆንም አንዳንድ የፋይናንስ ሴክተር አዋቂዎችም መዋቅራቸውን ዘር እና ሃይማኖት እየሆነ መምጣቱ የፋይናንስ ተቋማቱን ወጥ ዕድገት የሚቀለብሰው ሆኗል።
ስለሆነም የሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ ጊዚያዊ ችግርችን ከመቅረፍ አኳያ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን ኢኮኖሚውን ከማሳደግ አንፃር ተጨማሪ ስጋት ነው።
የውጭ ባንኮችን ጫና በተመለከተ ኬንያን፣ኮንጎን፣ማሊን እንደ ምሳሌ መወሰድ ይቻላል።
በፈረንሳይ ባንኮች ኢኮኖሚዋን እየተዘረፈች ያለችው ኮንጎ አሁንም ዕጅግ ድሃ ማህበረሰብን ይዛለች።
በዚህም የውስጥ ፓለቲካዋ ሳይቀር በፈረንሳይ ባለሀብቶች ጫና ውስጥ ትገኛለች።
ኬንያም በእንግሊዝ ካምፓኒዎች እና ባንኮች የሃገር ውስጥ ጫና እየተደረገባት ነው።
የአሜሪካ ጣልቃ ገብነትም እንድሁ የኬንያን የሃገር ውስጥ ኢኮኖሚ እና የውስጥ ደህንነት እየተፈታተናት ነው።
ስለዚህ ኢትዮጵያም ማህበራዊ ተግዳሮቷን ለመፍታት ከመሰል እንቅስቃሴዎች ብትቆጠብ ጥሩ ነው።
ውሳኔዋንም ከፕራይቬታዜሺን አንፃር ቢሆንም ከህዝቧ ሰላም እና ከውስጥ ደህንነቷ አንፃር ራሷን ብትመረምር አዋጭ ሃሳብ ነው የሚል ግምት አለኝ።
የውጭ ተቋማት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሚኖሩባት ሃገር ውስጥ ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነታቸው እና ከውጭ ድፕሎማሲያቸው አንፃር ጠቃሚ አይደለም።
በመሰረታዊነት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አለማደግ እና የሰላም እጦት ዋነኛ ምክንያት የውጭ ተቋማት እና የምዕራባውያን ፓለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነው።
በምስራቅ አፍሪካ የተሻለ ጅኦ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ያላትን ሃገር ድሃ እና ዜጎቿ እርስ በዕርሳቸው እንድታኮሱ ያደረጉ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል የውጭ ባንኮች እንድገቡ መፍቀድ የምዕራባውያንን ሃሳብ እና የውስጥ ጣልቃ ገብነታቸውን በቀጥታ ይሁንታ መስጠት ነው።
መንግስት በጊዚያዊ ችግሮች እየተሺመደመደ የውስጥ ሰላሙን እና የሃገሪቱን አንድነት ለመብተን ከሚሰሩ ሃይሎች ያልተናነሰ ውሳኔውን አሳርፏል።
የኢኮኖሚስት ባለሙያዎች ጊዚያዊ ችግሩን ሳይሆን የውስጥ ጣልቃገብነቱን ጫና ጭምር ቢያጤኑት መልካም ነው እላለሁ።
2.8K views09:39