ከደሴ ከተማ አስተዳደር የተላለፈ ውሳኔ
ንሥር ብሮድካስ
ነሃሴ 30/2014
ከደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ተጨማሪ ውሳኔ ።
ደሴ - ነሀሴ 29/2014 ዓ.ም ( ደሴ ኮሚኒዩኬሽን )
የደሴ ከተማ አስተዳደር ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በከተማው ልዩ ልዩ ክልከላዎችን በማስቀመጥ የተቀመጡ ህጎችን እያስተገበረ ይገኛል።
እነዚህ ህጎች እንደተጠበቁ ሆነው በተጨማሪ ከነሀሴ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተጨማሪ ክልከላዎችን ያስቀመጥን መሆኑ ታውቆ ህዝቡ ተባባሪ እንድሆን እንጠይቃለን።
1ኛ- የመከላከያ አባል ሳይሆን የመከላከያን የደንብ ልብስ መልበስ ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሳይሆን የልዩ ኃይሉን የደንብ ልብስ ለብሶ በከተማው ውስጥ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ። የመከላከያም ሆነ የአማራ ልዩ ሀይል አባል ሳይሆን የደንብ ልብሱን ለብሶ ሲንቀሳቀስ የተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል ።
2ኛ - ከደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅር ውጭ ተፈናቃይ በመሆን የመጥታችሁ በከተማው በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው ፡፡
3ኛ- ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የጥምር ጦሩን ስም ማጠልሸት ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ይህን ተላልፎ የተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል ።
ለዚህም የከተማው ማህበረሰብ አሉባልታዎችን በተለያዩ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገጥ ወይም ጥላቻ ለማሳደር የሚሰሩ ኃይሎችን ለፀጥታ ሀይሉ ጥቆማ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
4ኛ- ፀጉረ ልውጥ የሆነ ሰው በምናገኝበት ሰአት ማህበረሰባችን በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል ።
5ኛ- በከተማችን የሚገኝ ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ በመንግስት አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ።
6ኛ- ማንኛውም አካል ከመንግስት አደረጃጀት ውጭ ለጦርነቱ በሚል ገንዘብ መሰብሰብ ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ አካል ሊኖር አይገባም ። ሆኖም መንግስት ወጣቱንም ፣ ባለሀብቱን ፣ መንግስት ሰራተኞችና አመራሮችን ወዘተ በማሳተፍ የራሱን የመንግስት አደረጃጀት ተጠቅሞ ለጥምር ጦሩ የሎጅስቲክ ድጋፍ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ በህጋዊ ደረሰኝ ከህዝቡ እየሰበሰበ ጥምር ጦሩ ውስጥ እየተሳተፈ ለሚገኝ ማንኛውም ኃይል ይጠቀምበት ዘንድ ያስረክባል ።
7ኛ- በማንኛውም ሰዓት ታርጋ ቁጥር የሌለው ተሽከርካሪ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር ውሎ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ።
የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
ነሐሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም.
ደሴ
ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1