Get Mystery Box with random crypto!

NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

የቴሌግራም ቻናል አርማ nisirbroadcasting — NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel) N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nisirbroadcasting — NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)
የሰርጥ አድራሻ: @nisirbroadcasting
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.71K
የሰርጥ መግለጫ

NISIR International Broadcasting Co. is an impartial and independent media agency operates as television; radio; social media & multimedia production.
Facebook: https://www.facebook.com/NISIR-International-Broadcasting-Corporation-105276671420707

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 241

2022-09-06 08:36:50
1.2K views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 07:11:01
በወለጋ የአማራ ህዝብ ላይ ቀጣይ ጥቃት ለማድረስ ኦነግም ቅስቀሳ እያደረገ ነው ።

ንሥር ብሮድካስ
ጳጉሜ 1/2014።

በወለጋ የአማራ ህዝብ ላይ ቀጣይ ጥቃት ለማድረስ ኦነግም ቅስቀሳ እያደረገ ነው ። ኦነግ ትላንት የሚከተለውን የጥፋት ጥሪ በOMN ሚዲያ አስተላልፏል ።

====የኦነግ የጥፋት ቅስቀሳ===

" የኦሮሞ ህዝብ የአለምአቀፍ ህግን በመፃረር እየተፈፀመበት ያለውን ጭፍጨፋ በጋራ እራሱን መከላከል እንዳለበት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አሳሰበ።

ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሁን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ ያለው ፋኖ አስቀድመው በሰፈራ መልክ ኦሮሚያ ውስጥ የነበሩትን ከለላ በማድረግ ከአማራ ክልል መምጣቱን ገልጿል።

ይህ በሰፈራ መልክ ኦሮሚያ ውስጥ በነበሩ ዜጎችና በመንግሥት ፀጥታ መዋቅር የሚደገፈው ቡድን ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አገምሳ ከተማን በመውረር በፈፀመው ጥቃት ከ65 በላይ ዜጎች መገደላቸውን ተናግሯል።

ከተገደሉት ውስጥ ሴቶችና አዛውንቶች ጭምር እንደሚገኙበት ኦነግ ገልፆ፣ ከግድያ ውጭም ፋኖ ዘረፋ መፈፀሙንም ገልጿል።

ይህ ቡድን አገምሳ ላይ ጭፍጨፋ ከፈፀመ ከጥቂት ቀናት በኋላም በሆሮ ቡሉቅ ወረዳ በፈፀመው ጥቃት 31 ንፁሃን መገደላቸውን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ ሌሎች ወንጀሎችንም መፈፀሙን ተናግሯል።

የሲቭል ልብስ የለበሱ የፌዴራል ሃይሎችም በቡድኑ ውስጥ እንደነበሩ መረጋገጡን ገልጿል።

ኦነግ በተለያዩ ቦታዎች የተፈፀሙ ተመሳሳይ አሰቃቂ ግድያዎችን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ተናግሮ፣ በግድያዎች ውስጥ የመንግሥት ሃይሎች እጅ ሊኖር እንደሚችል ያለውን ጥርጣሬ ገልጿል።

የኦሮሞን ህዝብ ከመሬቱ ለማፈናቀል የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሶ፣ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ ሲፈፀመ መንግሥት በዝምታ እያለፈ መሆኑን አስረድቷል።
የኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈፀም ጭፍጨፋ ከኢትዮጵያ ምስረታ ጀምሮ እስከዛሬ የዘለቀ መሆኑን ኦነግ ገልፆ፣ ይህ መቆም የሚችለው የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ተነስቶ ራሱን ከተከላካለ ነው ብሏል።

የኦሮሞ ህዝብም ይህን ተረድቶ እየተፈፀመበት ያለውን ጭፍጨፋ በአንድነት ተነስቶ ራሱን እንዲከላከል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አሳስቧል።

የአለምአቀፉ ማህበረሰብም በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ ለማስቆም የበኩሉን እንዲወጣ ኦነግ አሳስቧል።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
1.6K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 07:10:13
የፋኖ መሪዎች  ምሬ ወዳጆን እና ደምሌ አራጋውን ለመግደል በተደጋጋሚ ከኋላ እየተተኮሰባቸው ህይዎታቸው ተርፈዋል።
በጦር ሜዳላይስ መንግስት እንዴት ይታመን?

=====በጎበዜ ሲሳይ=======

ሰሞኑን በአንድ በቲዊተር ስፔስ ላይ በነበረኝ ውይይት አሁን በጦር አውድማ ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብን ስሜት አስመልክቶ የተለያዩ ነጥቦችን አስቀምጨ ነበር። ከዚያ ውስጥ Tplf ውይይቱን ቀድተው የሚፈልጉትን ብቻ መዘው እና ቀጣጥለው ተጠቅመውበት ተመለከትኩ ።

እውነታው:-
የአማራ ሕዝብ በተለይ ከትግራይ ክልል ጋር የሚዋሰነው ህዝብ ጦርነት ሰልችቶኛል ፣ መንግስት በይደር በሚተወው ጦርነት በየአመቱ እያገረሸ ለሞትና ለስደት ዳርጎኛል ። ጦርነት አንፈልግም ዝመቱም አትበሉን የሚል አርሶ አደር አለ።

በኦሮሚያ ክልል በአንድቀን አዳር  በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች ታርደው ሲያድሩ መንግስት ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንኳ ነፍጓቸዋል። ኦሮሚያ መሬታችሁ አይደለም ውጡ ስንባል፣  አዲስ አበባ ከተማችሁ  አይደለም አትገቡም እየተባልን መልሰው አገራችሁ ተወረረ ዝመቱ ይሉናል። ስለዚል  ብልፅግናም ይሁን ሕወሓት ለእኛ አንድ ናቸው ። ብሎ ያኮረፈ ሕዝብ አለ።

የአማራ ክልል ብልፅግና አንፃራዊ ሰላም አለ ብሎ ሲያስብ ደግሞ ራሱን ከጠላት ለመከላከል ወታደራዊ ስልጠና ሲወስድ የነበረን ወጣት   ኢ- መደበኛ የሚል ስም ሰጥቶ በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶችን እስር ቤት ወርውሮ  በእጁ ያልገቡትን ሲያሳድድ ቆይቷል።
አሁን በተከፈተው ጦርነት ውስጥም ሕወሓትን ፊት ለፊት እተዋጉ የሚገኙት የፋኖ መሪዎችን  ምሬ ወዳጆን እና ደምሌ አራጋውን ለመግደል በተደጋጋሚ ከኋላ እየተተኮሰባቸው ህይዎታቸው ተርፏል። በዚህ ሁኔታ እንደት መንግስትን ተማምኜ ጦርነት እገባለሁ የሚል ወጣትም አለ ።
መንግስት ይህንን ጦርነት መቋጨት ከፈለገ እነዚህን ችግሮች ተገንዝቦ ይቅርታ የሚጠይቀውን ጠይቆ  እና ችግሮቹን ተማምኖ እና ተማምሎ ሕወሓቶች  እንደመጡበት መንገድ ሕዝባዊ መዓበል ካላስነሳን እና ሕዝቡን ወደ አንድነት ካላመጣን በሰተቀር ጦርነቱ አይቋጭም  የሚል መሬት ላይ ያገኘሁትን መረጃዎች አሰባስቤ ነው ያስቀመጥኩት ። ለምን ጦርነት በቃኝ አላችሁ ? የሚል የብልፅግና ሰዎች እየጮኹ ነው።ይሁን እንጅ እውነታውም አላማውም  ይህ ነው።

ሃቁ ይህ ነው።

#ድልለፋኖ
#ድልለኢትዮጵያ


ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https:  https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
1.5K views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 21:22:33
"እኔን ለማሰር ክትትል እያደረጉብኝ  ነው "

=======ጋዜጠኛ ወግደረስ========

መረጃው ደርሶናል

የጎንደር ማዕከላዊ ዞን የፀጥታ መዋቅር ከኦህዴድ ብልፅግና ታዝዞ በብአዴን ተላላኪነት ከወልቃይት ጠገዴ ስመለስ ሊያሳስረኝ ሲቪል ደህንነቶቹን አሰማርቶ እየጠበቀኝ መሆኑን መረጃው ደርሶኛል።

ትናንት ምሽት አካባቢ "ለስራ" ነው በሚል ሁለት ተላላኪዎቹን ልኮ ለማስያዝ ሞክሩ ነበረ።ይሁን እንጅ ቀድመን በመንቃታችን ለማምለጥ ሞክረናል።

እኔን የሚያሳድዱኝ የአማራ፣የአዲስ አበባ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ጠላት ትህነግ ብቻ ሳይሆን የትህነግ የበኩር ልጅ የሆኑት አራት ኪሎ የተቀመጠው ኦህዴድ ብልፅግና እና ተላላኪው ብአዴን መሆናቸውን ለሰፊው ህዝብ በመግለፄ ነው።ዛሬም እውነታው ይህ።ብታስረኝም የሚለወጥ ነገር የለም።

እኛን ለማሳደድ የምታወጣውን በጀት እና የሰው ኃይል የተፈናቀሉ 12 ሚሊየን አማሮችን መግብበት።በወለጋ ሀሮ አዲስ ቀበሌ ተፈናቅለው ያለ እህል ውሃ ጎዳና ላይ የወደቁትን ቀልብበት።አማራውን 30 ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰውን የመሰረተ ልማት ውድመት ጠግንበት፣"አይ" ካልክ ግን ለወሰኪህ አድርገው።

አንተ ታስረኛለህ ብየ ለዕውነት ከመቆም እና እውነትን ከመናገር ለአፍታ ወደ ኋላ አልልም።አበቃ።

ጋዜጠኛ ወግደረስ

#ድልለፋኖ
#ድለኢትዮጵያ

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https:  https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
1.4K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:11:17 ንሥር እለታዊ ዜና _ Sep 5/2022

1.8K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 14:34:27
1.3K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 14:34:26 አሸባሪው ሕወሓት የአማራን ሕዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ – ቀቢጸ ተስፋ
September 3, 2022 የዕለቱ ዜናዎች
ከአማራ ሕዝብ ሂሳብ አወራርዳለሁ ያለው የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ዛሬ ላይ ደግሞ የአማራን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ ቀቢጸ ተስፋ መሆኑን በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፖሊሲ ጥናት ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገለጹ።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አንተነህ መሉ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው ሕወሓት አማራ ክልል አካባቢ ያሉ የፖለቲካ ሁነቶችን በራሱ ዓላማ ለመጠምዘዝና ወደ ራሱ ሁኔታ ውስጥ ለመውሰድ የሚፈልግባቸው አማራጮችን እየሳየ ነው።

ቡድኑ ሕዝቡ ከእሱ ጋር እንዲሰለፍና በራሱ መንገድ እንዲሄድ የሚያደርጋቸውን ጥረቶችም እያሳየ ይገኛል። ይህ ቀቢጸ ተስፋና የትም የማያደርሰው ሴራ ነው።

እንደ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገለጻ፤ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በሕዝብ ላይ እያደረሰ የነበረው ግፍ የሚታወቅ ነው።

አሁንም ጦርነት እያካሄደ ባለባቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል። ለሕዝብ አዛኝ ያልሆነ ቡድን ሕዝብን የትግል አጋር ለማድረግ መሞከሩ ተስፋ የለሽ ያደርገዋል።

ከዚህ ቀደም ከአማራ ሕዝብ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን ባሉበት አንደበት ዛሬ ደግሞ ከአማራ ጋር ጸብ የለንም ሲሉ ይደመጣል።

ነገር ግን በተጨባጭ ከዚህ ቀደም በደረሱባቸው አማራና የአፋር አካባቢዎች ያደረሱት ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እጅግ ዘግናኝ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህ ቁስል ሳይሽር ሌላ ጥፋት ለመፈፀም ሦስተኛ ዙር ወረራ በመፈጸም ይህንኑ የግፍ ሥራቸውን ተያይዘውታል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ጸብ የለንም የሚለው ፕሮፓጋንዳ «ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ» ዓይነት ቀልድ ነው።

ሕወሓት ወደዓላማው የሚያሻግረውን መንገድ አሊያም አንድ ግብ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ዕድል የመጠቀም ሁኔታን በሰፊው የለመደ ነው፤ ገና በትጥቅ ትግል በነበረበት ወቅት እንኳን ለሰላማዊ ውይይት የጠራቸውን የሌሎች የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በጅምላ በመጨፍጨፍ ጭካኔውን በተግባር ያሳየ፣ በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን የመፍታት ልምድ የሌለው ቡድን ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ: የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ስዬ አብርሃ ስለ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ - ጽዮን ግርማ
አሁንም በዚህ ደረጃ መምጣቱ የሚጠበቅ ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ የሚደረጉ የሰላም ጥሪዎችን ሲያበላሽ የከረመና አሁንም ትግራይ ውስጥ ያለውን ቆይታ ለማራዘም በሕዝቡ ዘንድ የተጠላ መሆኑ እየታወቀ ሕዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ መሞከሩ ተስፋ መቁረጡን ያሳያል ብለዋል።

አሸባሪው ሕወሓት በማጭበርበር በኩል በመጥፎም ይሁን በጥሩ ይጠቅመኛል ያለውን ለመጠቀም መሞከሩ የተለመደ ባህሪው ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህ የራሱን ፍላጎት ሊያሳካለት የሚችለውን ማንኛውንም ቀዳዳ የመጠቀም ባህሪው ከበፊት ጀምሮ የመጣ እንደሆነ አመላክተዋል። ሆኖም ግን ይህ አካሄድ እንደማይሳካለት ተናግረዋል።

ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ዋስትና ሊሆን የሚችልና በአካባቢውም ሠላማዊ የሆነ መረጋጋትን ለማምጣት በተከታታይ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው አሁንም ተጨማሪ ጥፋቶችን እየፈጸመ የሚገኘው አሸባሪው ሕወሓት፤ አሁን እየተከተለ ያለው አካሄድም መላ የጠፋበት ስለመሆኑ እንደሚያሳይ ነው ረዳት ፕሮፌሰሩ ያብራሩት።

የአማራና የትግራይ ሕዝብ ካላቸው ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ ግንኙነት አንጻር የሕወሓት አካሄድ ጠቀሜታ የሌለው ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ፤ አካሄዱ ሁሉ የዜሮ ድምር የጥፋት አካሄድ ነው። ይህም ቡድኑን የትም አያደርሰውም ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ በሁለቱም ሕዝቦች ዘንድ በወጣቶችና ሕፃናት ላይ የሚያደርሰው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ፤ እንደ አገርም ሆነ ለሕዝብ ቢያስብ ኖሮ ብዙ የሰላም አማራጮችና መንገዶች ይከትል እንደነበር ጠቅሰዋል፤ በሰጥቶ መቀበል መርህም ሆነ በሠላማዊ መልኩ የተጀመሩ የድርድር ጥረቶችን ተቀብሎ ገፍቶ መሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ከፍተኛ እንደነበርም ጠቁመዋል። ነገር ግን ሕወሓት ለአገርና ለሕዝብ ደንታ የሌለው ድርጅት መሆኑን የሚፈጽማቸው ግፎች ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ሕወሓት እያደረገ ያለው ሕዝባዊ ማዕበል የውጊያ ስልት ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል። ሕፃናትን በአጠቃላይ ትግራይ ውስጥ ያለውን ወጣት ሲያሰለጥንና ሲያስታጠቅ ነው የከረመው። ይህ አገር ተረካቢ ትውልድ እያሳጣ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ: Being evil has a price
ገና በአፍላ ዕድሜ የሚገኙ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ በርካታ ሥራዎችን መሥራት የሚችሉ ትውልዶችን በእንዲህ ዓይነት የሕዝባዊ ማዕበል ጦርነት ማሳተፍ አስነዋሪና ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም የተኮነነ ድርጊት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ ነገር እንዲወገዝና ተጽዕኖ ማሳደር እንደሚገባም ተናግረዋል። በዚህ ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ አገር ቤት ባሉ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ዘንድ ተገቢ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢፕድ @Zehabesha
1.3K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:46:45
#ሰበር መረጃ_ ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን

ሆሮ ቡሉቅ( ሰቀላ) ቦኔ አቡና ቀበሌ ላይ 3 አማራ መቸ እንደታገቱ ሳይታወቅ አንድ ኦሮሞ ቤት ውስጥ ተገለው ተገኙ

ንሥር ብሮድካስት
ነሐሴ 30/2014


ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ቅዳሜ በቀን 28/12/2014 ሆሮ ቡሉቅ( ሰቀላ) ቦኔ አቡና ቀበሌ ላይ 3 አማራ ወገኖቻችን መቸ እንደታገቱ ሳይታወቅ አንድ ኦሮሞ ቤት ውስጥ የፊጢኝ ታስረው ተገለው መገኘታቸውን የንሥር ብሮድካስት ወለጋ ዘጋቢአችን አረጋግጧል::

ይህ ቦታ ማለትም ቦኔ አቡና የምትባል ኬላ ከዞን ወደ ጃርደጋ ጃርቴና ወደ አሙሩ ወረዳ መተላለፊ ቦታ እንደመሆኑ በተከታታይ ለረጅም ጊዜ አማሮችን ከመኪና እያስወረዱ በማገት መጨፍጨፊያቸው የታወቀ ቦታ ነውም ተብሏል:: ቢሆንም የዛሬው ግን የስቃዩን ልክ በአይን ብሌናችን ስላየነው በጣም ይዘገንናል ብለዋል በአካል ተገነተው ያዩት ሀገር ጠባቂ ሚሊሾች::

የሚገረመው ደሞ ይላሉ ይሀን ሁሉ ግፍ በንፁሃን (አባቶች እናቶች ህፃናት አዛውንት) ወገኖቻችን ላይ የሚፈፅሙት አካላትን አማራን በጨፈጨፉ ቁጥር" ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊታችን " እያሉ ይዘግባሉ።

ቆይተው ደግሞ ሞታችንን ቀምተው እንደነ OMN ባሉት ሚድያወቻቸው ፅንፈኛው የአማራ ፋኖ ወለጋ ላይ ንፁሃን ዜጎችን ጨፈጨፈ ይላሉ

ከሞትንም ቡሃላ እስራት አለ ወይ???" ሲሉ የወለጋ አማራወች ይጠይቃሉ

የማያበባራው የወለጋ አማራ ብሶት!


ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
2.1K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:01:30 ንሥር የረፋድ ዜናወች _Sep 5/2022

2.0K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 09:23:19 አማራ ከብአዴን በላይ ጠላት የለውም! _ከንሥር እንግዳ _ Sep 4/2022

2.3K viewsedited  06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ