Get Mystery Box with random crypto!

የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ne_siha_eslamik — የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ne_siha_eslamik — የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
የሰርጥ አድራሻ: @ne_siha_eslamik
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.26K
የሰርጥ መግለጫ

بسم الله الرحمن الرحيم
📮እንኳን ወደዚህ ቻናል ተቀላቀሉ‼️
በዚህ ቻናል ቂርአቶችን፣ ሙሐድራዎችን፣ዳዐዋዎችን እና ሌሎችንም ከአረብገንዳ መስጊድ በአሚሩ አማካኝነት በቀጥታ የምታገኙበት ቻናል ነው።
ሃሳብ አስተያዬት ካለ በዚህ ያድርሱን ⤵️
@ye_Arebgenda_mesgid_wetatoch_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-10-01 20:28:04 ☞የሠዉ ልጂ ሁለት ግዜ አሏህ ፊት ይቆማል

①) የመጀመርያዉ በዱንያ ላይ እያለህ የምትሰግደዉ ሶላት ነው።

②) የሁለተኛዉ የውመል ቂያማህ ነው።

▼☞ የሁለተኛዉ አሏህ ፊት አቋቋምህ ያማረ  እንዲሆን ከፈለክ የመጀመርያዉን ☞አቋቋምህ አሳምር።

ኢብኑል ቀ-ይ'ዩም

SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
442 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 22:44:04
70 views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:12:27 ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላል :-
" ዕውቀትን ፈልጉ (ተማሩ ) እሱን መማር አላህን መፍራት ነው
"እውቀትን መፈለግ ዒባዳ ነው
መማማሩ አላህን ማጥራት ነው
ብይኖችን ከእውቀት ፈልጎ ማውጣቱ ጂሃድ ነው
ለማያውቀው ማስተማሩ ሰደቃ ነው
ለባለቤቶቹ ማካፈሉ ወደ አላህ መቃረቢያ ነው
ብቸኛ ስትሆን አጫዋችህ ነው
በባዶ ቤት ስትሆን ጓደኛ ነው "
ጃሚዑ በያኒል ዒልሚ ወፈድሊሂ : ( 1/ 54

http://t.me//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
159 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 15:29:18 "يَا كَثِيرَ القَبَائِح ...
غَدًا تَنطِقُ الجَوَارِح "
አንተ የብዙ መጥፎ ሥራ ባለቤት ሆይ!
ነገ አካላቶቻችን እንደሚናገሩ እወቅ።
ابنُ الجَوزيِّ رَحِمَهُ اللّٰه

SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች
71 views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 15:38:33 Watch "ሱረቱ አል- ዙመር//31-40//" on YouTube


160 views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 10:13:37 ስለ ሰው ልጅ ክህደት የአላህ ፍጥረቶች ምን አሉ?
"
ምድር በየቀኑ እንዲህ በማለት ጌታዋን ትጣራለች፦ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን ልዋጠው ፍቀድልኝ እርሱኮ ያንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም»

ተራራም እንዲህ በማለት የጌታዋን ፍቃድ ትጠይቃለች፦ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን ላጣብቀው ፍቀድልኝ እርሱኮ ያንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም»

ባህርም በተራዋ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን እንዳሠምጠው ፍቀድልኝ ፣እርሱ ያንተን እርዚቅ እየበላ አያመሰግንህም» ትላለች

ሰማይም «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን አንዳች መቅሰፍት ላውርድበት ፍቀድልኝ እርሱ የአንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም» በማለት ትጣራለች።

#አሏህም « ፍጥረቶቼ ሆይ,,,, የሰው ልጅን የፈጠራችሁት እናንተ ናቹህን»? ይላቸዋል

«#ጌታችን #ሆይ አይደለም» ይላሉ ጥራት የተገባው አሏህም እንዲህ ይላል፦ እናንተ ብትፈጥሯቸው ታዝኑላቸው ነበር።

የነሱን ጉዳይ ተውልኝ እስኪ ከነሱ ወደኔ የተመለሰ (የተፀፀተ) እኔ ወዳጁ ነኝ። እኔኮ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለባሮቼ አዛኝ ነኝ። ከነሱ ወደኔ ተፀፅቶ የተመለሰ «አንተ ተውበት አድራጊ ሆይ
እንኳን ደህና መጣህ ብየ ከርቀት እቀበለዋለሁኝ ።

ወንጀል ሰርቶ ከኔ ለሚሸሸው ደግሞ፦ ወደርሱ ቀርቤ ፦ ባርያዬ ወዴት ነው የምትሄደው ከእኔ ውጭ ሌላ ጌታ አገኘህን፤ ከኔ ውጭስ ሌላ አዛኝ የሆነ ጌታ አገኘህን የምትሸሸኝ »በማለት እጠራዋለሁኝ።

ጌታዬ ሆይ ከርቀት የምትቀበለው ወዳንተ ተመላሽ ባርያ አድርገን።አሚን

SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
114 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 10:03:06
361 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 13:52:50 #ዑስማን #ኢብን #ዐፋን ( ረዲየሏሁ ዐነሁ) የዒባዳን ጥፍጥና በአራት (4 ) ነገሮች አግኘው አሉ :-

➊አላህ ያዘዘውን ግዴታ በመፈፀም ::

➋ #አላህ ከከለከለው ሐራም ካደረጋቸው ነገሮች
በመራቅ ::

➌ #አላህ በመልካም ያዘዘውን በመፈፀም ::

➍አላህ የሚጠላውን ነገር መሥራት የአላህን ቁጣ
ስሊሚያመጣ ፈርቶ በመተው ናቸው ::

#ኢብኑ #ዑመር የአላህ መልዕክተኛ :
( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) ትከሻዬን ያዝ በማድረግ " በዚህች ዓለም ስትኖር እንደ መንገደኛ ሁን " አሉኝ ማለቱ ተዘግቧል ::

#አራት #ነገሮች አሉ ላዩን ስናያቸው ምንዳ ያላቸው ውስጡን ስንመለከታቸው ግን ግዴታ መሥራት ማድረግ ያለብን ነገሮች ናቸው :: እነሱም :-
➊ከአላህ ሰዎች ጋር አብሮ መኖር

➋ #ቅዱስ #ቁርአንን መቅራት

➌ቀብርን መጎብኘትና

➍የታመመ ሰው መጠየቅ ናቸው ።

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
430 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 17:39:46 》መዉሊድ 《
በታላቁ ሸይኽ ዱክቱር ሷሊህ አል ፈውዛን من كتاب الخطب المنبرية لمعالي
الشيخ 1الدكتور صالح الفوزان/ج

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ሙውሊድ በብዙ አቅጣጫ ከንቱ እና ሀራም ነው።
①በዲን ላይ ፈጠራ ነው ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው ሙሊድን ማቆም የሚያዩ ሰወች ከሸሪአ ማስረጃን ሊያቆሙለት አይችሉም
②ሙሊድ ነሷራዎችን በኢሳ ልደት ላይ በማክበራቸው ላይ መመሳሰል ነው በነሷራዎች ከመመሳሰል ደግሞ በርግጥ ተከልክለናል
③በመውሊድ ዉስጥ በአብዘሃኛው ግዜ በተወገዙ  እና እርም በተደረጉ ነገሮች ላይ ይወድቃል እርም ከተደረጉ ነገሮች ትልቁ በአሏህ ማጋራት ነው ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለምን መጣራት በሳቸዉም እርዳታን መጠየቅ ሽርክ ያለባቸዉን ስንኞችን ነብዩን ማወደስ ላይ መግጠምን ይመስል ቡሩዳ የተሰኘው ስንኝ እና መሰሎቹ(መውሊድ ላይ ይከሰታል)
④በእስልምና ላይ ሁለት በዓል እንጂ የለም ¹ኢዱል_አድሃ እና የተባረከው ²ኢዱል_ፈጥር ሶስተኛ በዓልን የፈጠረ በርግጥም በእስልምና ከርሱ ያላደለን ፈጥሯል
አነስ ኢብኑ ማሊክ ከርሱ የተገኘውን አሏህ ይውደድለትና እንድህ አለ ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም መደመዲና ገቡ ለመዲና ሰወችም በነሱ ዉሰጥ የሚጫወቱባቸዉ ሁለት ቀን ነበራቸው ነብዩም እነዚህ ቀኖች ምንድን ናቸው አሉ እነሱም በጃሂልያ ግዜ እንጫወትባቸው ነበር አሉ ነብዩም እንድህ አሉ አሏህ ከነዚህ ቀኖች የተሻለ የሆነን ቀን ለውጦላቹሀል ¹የእርዱ ቀን እና ²የፈጥሩ ቀን
አቡ ዳውድ አህመድ ነሳኢይ ዘግበውታል ሰነዱ በሙስሊም ነስፈርት ነው

እናንተ የአሏህ ባሪያዎች ሆይ አሏህን ፍሩ ቢድአንና ተፃርኖን ተጠንቀቁ ሱናን ሙጭኝ አድርጋቹህ ያዙ ተከተሉ አትፍጠሩ
أعوذ بالله من الشيطان الرجيم
وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
بارك الله لي ولكم في القرآن العظيم
)من كتاب الخطب المنبرية، لمعالي الشيخ الدكتور صالح الفوزان/ج1)·
☞ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈዉዛን [አሏህ ይጠብቃቸዉ] እንዲህ አሉ ፦
[ልክ ወደ መልካም ተጣሪዎች እንዳሉት ሁሉ ፡ ወደ መጥፎ ተጣሪዎችም አሉ

☞ሰዎች ደግሞ ከመልካም ተጣሪዎች ይልቅ ወደ መጥፎ ተጣሪዎች የቀረቡ ናቸዉ ፡ ምክንያቱም ነፍሶች ወደ ፊትና እና ወደ ሹብሀ የተዘነበሉ ናቸዉ አሏህ ያዘነለት ሲቀር ]

ምንጭ ☞ሸርህ ኪታብ አል-ፊተን ወል ሀዋዲስ [83]
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
541 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 12:26:29 አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡

ወጣትነትህን     ከማርጀትህ በፊት
ጤንነትህን       ከመታመምህ በፊት
ሀብትህን         ከመደህየትህ በፊት
ትርፍ ጊዜህን    ከመጨናነቅህ በፊት
ህይወትህን         ከመሞትህ በፊት

የአሏህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)  ሲናገሩ " ሕዝቦች አምስት ነገሮችን በመውደድ ከአምስት ነገሮቺ ይዘናጋሉ"  ካሉ በኀላ ሲዘረዝሯቸው እንዲህ አሉ:

   ሕይወትን ያፈቅሩና - ሞትን ይረሳሉ:

ዱንያን ያፈቅሩና -አኼራን ይዘነጋሉ፡

  ህንፃ መገንባት ይወዱና - ቀብር  መኖሩን ይዘነጋሉ፡

  ገንዘብ ይወዱና - ከሒሳብ ( በቂያማ ግዜ መተሳሰቡን ) ይዘነጋሉ ፡

ፋጡራንን ያፈቅሩና - ፈጣሪን ይዘነጋሉ ፡፡
አሏህ ከዚህ ተግባር ይጠብቀን ኣሚን ፡፡

http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
527 views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ