2022-09-13 20:23:01
ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው።
አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው።
# እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ" አሉት።
"ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?"
# እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት
"ከሰው ሁሉ ሀብታመ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው።
# "ባለህ ነገር ተብቃቅተ አላህን አመስግን" አሉት
"ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ"አሉት።
"ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "በአላህ ተወከል"አሉት
"በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን
እፈልጋለው" ሲላቸው?
#"ዚክር አብዛ" አሉት።
"ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "ለሰው ጠቃሚ ሁን" አሉት።
"የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው
# "ችግርህን ለፍጡር አትንገር" አሉት።
"ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ እፈልጋለው?" ሲል
#"አንተም እነሱ የወደዱትን ውደድ" አሉት::
"ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህንመገናኘት እፈልጋለው" ሲል
# "ጀናባህን በደንብ ታጥበ እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ መተናነስ መታመም አለብህ" አሉት።
"ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸውም
#"አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው" አሉት።
"ኢማኔ እንዲ ሞላ እፈልጋለው" ሲል
# "ፀባይህን አሳምር" አሉት።
"እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል
# "ተዋዱዕ አዘውትር" አሉት።
"ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው
# "ሀራም አትብላ" አሉት::
"አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "ግዴታዎችህን ፈፅም" አሉት።
"በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው
# "መልካም ፀባይ መተናነስ እና በበላ ላይ ሰብር ማድረግ ነው" አሉት።
"በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው
# "መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው" አሉት
"በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው?
#"ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው" አሉት።
"የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ
እፈልጋለው?" ሲል
# "ሰውን አትበድል" አሉት
"የቂያማ እለት አላህ እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?"
# "ለአላህ ባርያዎች እዘን" አሉት።
"የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው
# "በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትህግስት መሰድረግ ነው" አሉት።
"የቂያማ እለት ነውሬ እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል
# "የወንድምህን አይብ ሸፍን" አሉት።
"የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን
እፈልጋለው?" ሲል
# "በአንድም ፍጡር አትቆጣ" አሉት።
*** አላህ ሱብሃን ወተአላህ ባወቅነው. በስማነው የምንስራ ያድርገን አሚን!!!!
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
1.1K views17:23