Get Mystery Box with random crypto!

#አንብቤው_ከተመቸኝ_ላካፍላችሁ! #ክፍል_ሁለት ሀዘን እና ትካዜ ወደ ኋላ ጣላቸው! ኢብኑ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

#አንብቤው_ከተመቸኝ_ላካፍላችሁ!
#ክፍል_ሁለት

ሀዘን እና ትካዜ ወደ ኋላ ጣላቸው!


ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት እንዲህ ይላል፦
"ሀዘን ቁርኣን ውስጥ በክልከላ መልኩ ወይም በማራቅ መልኩ ቢኾን እንጂ አልተጠቀሰም
ልክ አላህ እንዳለው

{ وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا }
{አትስነፉ አትዘኑም}


{ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ }
{ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም}"

የዚህ ሁሉ ሚስጥሩ
ሸይጣን ከሚያስደስተው ነገር ሁሉ ትልቁ ሙዕሚን የኾነ ሰው አዝኖ ማየቱ ነው። ከዚያም ከመንገዱና ከጉዞው ሊገታው።

በእርግጥም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሐዘን ተጠብቀዋል
"اللهم إني أعوذ بك من الهم والحزن"
[አላህ ሆይ እኔ ከሀዘንና ከጭንቀት በአንተ እጠበቃለሁ] በማለት


ኢብኑል ቀይም በድጋሚ እንዲህ ይላል፦
"ሀዘን ብሎ ማለት
ቀልብን ያደክማል፣ ቆራጥነትን ያከሽፋል፣ ፍላጎትን ይጎዳል፣ ወደ ሸይጣንም ምንም ተወዳጅ ነገር የለም ሙዕሚን አዝኖ እንደ ማየት"


ስለኾነም፦
ሀዘንን ራቁ!
   መልካምን ከጅሉ!
      በአላህ ላይ መልካም ግምት ይኑራችሁ!
       አላህ ዘንድ ባለው ተማመኑ
          በአላህም ላይ ተመኩ
              በአላህ ፍቃድ በሁሉም ሁኔታ ደስተኞች ትኾናላችሁ


ብትመለከት፦
አላህ ብዙ ነገራቶች ሳትጠይቀው ሰጥቶሃል። ስለዚህ አላህ የምትፈልገውን ነገር እንደ ማይከለክልህ እርግጠኛ ሁን። ምን አልባት ግን አለ መሰጠትህ የተሻለልህ ካልኾነ በስተቀር።


ምን አልባት፦
አንተ ተኝተህ ሳለህ የሰማይ በሮች ላንተ ዱዐ በሚያደርጉልህ ሰዎች እየተንኳኩልህ ይኾናል።

ድሃ ኾኖ የረዳኸው፣
  አዝኖ ያስደሰትከው፣
    የተጣበበ ኾኖ ያቃለልክለት፣
       እያለፈ ብቻ ፈገግ ያልክለት

እጁን ዘርግቶ እየለመነልህ ሊኾን ይችላል።

መልካምን ከመስራት መቼም አትቆጠብ


ከቀደምቶች አንዱ እንዲህ ይላል፦
"አላህ የኾነ ነገር እጠይቀዋለሁ, ያንን ነገር ከሰጠኝ አንዴ እደሰታለሁ፤  ያንን ነገር ካልሰጠኝ ግን አስር ጊዜ እደሰታለሁ፤ ምክንያቱም መሰጠቴ የእኔ ፍላጎት ነበር አለመሰጠቴ ደግሞ የአላህ ፍላጎት ነው።"


ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይላል፦
"ህይወት አጭር ናት።
      በሀዘን፣
         በጭንቀትና
            በጥበት
                አታሳጥራት"

በያላችሁበት የአላህ እዝነትና ጥበቃ አይለያችሁ
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ