2022-07-19 21:01:18
የሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር አሳዛኝ ታሪክ
================================
ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር ረዲየልሏሁ ዐንሁ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት፣
በመካ ሰዎች ዘንድ እጅጉን የተከበረ፣ ተክለ ቁመናው የሚያምር፣ የባለ ሀብት ልጅ ነበር።
ከመቀማጠሉ የተነሳ አንዳንዶች እንደሚሉት፣
በመንገድ ላይ ሲኬድ ዝም ብሎ ሽቶ ከሸተተ፤
በቃ፥ በዚህ መንገድ ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር አልፏል ይሉ ነበር።
ሙስዐብ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዳሩል አርቀም በነበሩበት ጊዜ መጣ፣ የሚያስተምሩትን አዳመጣቸው።
በትምህርታቸው ተማርኮ እስልምናን ተቀበለ።
ነገር ግን በተለይም እናቱን ስለፈራ እስልምናውን ደበቀ።
በኋላ ግን ሲሰግድ ታይቶ ታወቀበት።ወደ እስልምና ከገቡ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች ውስጥ አንዱ ነው።
መገለልና እንግልት ደረሰበት፣ ብዙ ስቃዮችን አሳለፈ።
የመጀመሪያው ወደ ሐበሻ ስደት ጊዜ ሲሰደዱ እርሱም ነበረበት።
በኋላ ደግሞ ወደ መዲና ተሰደተ።
ለመጀመሪያ ጊዜ መዲና ላይ ጁሙዐን የሰገደ ነውም ይባላል።
*
የሙስዐብ ባለቤት የረሱልሏህ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት የሆነችው የዘይነብ ቢንት ጀህሽ እህት ነበረች።
ሙስዐብ አንድ ሴት ልጅ ብቻ ነበረችው።
የበድርና የኡሑድን ዘመቻዎች ተሳትፏል።
በኡሑድ ጦርነት ጊዜ አንድ ኢብኑ ቀምኣህ የሚባል ግለሰብ፣ መጀመሪያ እቃ የያዘውን እጁን በሰይፍ ቆረጠው፣ ከዚያም እቃውን በግራው ሲይዝ ግራ እጁንም ቆረጠው፣ በደረቱ ጨምዶ ሲይዝ ደግሞ፥ ደረቱን ወግቶ ገደለው።
ሙስዐብም ሸሂድ ሆነ።
ረሱልሏህ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስዐብን መሞት ሲያዩ፤
ይህን የአላህ ቃል አነበቡ፦
" مِنَ الْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَاهَدُوا اللَّهَ عَلَيْهِ فَمِنْهُمْ مَنْ قَضَى نَحْبَهُ وَمِنْهُمْ مَنْ يَنْتَظِرُ وَمَا بَدَّلُوا تَبْدِيلًا"
"ከአማኞች በርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ።
ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለኃይማኖቱ የተገደለ) አልለ፤ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አለ።
(የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም።"
[አል አሕዛብ፥ 23]
||
ሙስዐብ ተገድሎ የተገኘ ጊዜ ሶሐቦች ለመከፈን ፈለጉ።
ነገር ግን ሙስዐብ ለእስልምና ብሎ የቅንጦት ህይወቱን ትቶ ስለተሰደተ፣
ከባለብትነት ወደ ደሃነት ተቀይሯል።
የለበሳት አንድ ነጠላ ብቻ ነበረች።
በዚህች ነጠላ ለመከፈን ሲፈልጉ ከማነሷ የተነሳ፣
ራሱን ሲያለብሱት እግሩ ይገለጥባቸውዋል፤
እግሩን ሲያለብሱት (ሲሸፍኑት) ጭንቅላቱ ይገለጥባቸዋል።
أرادوا تكفينه بها، فكانوا إذا غطوا رأسه بدت رجلاه، وإذا غطوا رجليه بدا رأسه!
በመጨረሻም ለረሱልሏህ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ምን እናድርግ?" ብለው ሲያማክሯቸው፣
ጭንቅላቱን አልብሱትና፣ እግሩ ላይ ቅጠል (ሳር) ጣል አድርጉበት (አልብሱት) አሏቸው።
فقال النبي محمد: «غطوا رأسه، واجعلوا على رجليه من الإذخر»،
ሶሐቦችም በተባለው መሰረት ከፍነው ቀበሩት።
ረዲየልሏሁ ዐንሁ ወአርዷህ
ያ ዝነኛ ቅምጥል ሶሐባ ነው እኮ እንዲህ የሆነው
የሚሄድበት መንገድ እንኳ ሳይቀር ሽቶ ሽቶ እንዳልሸተተ ሁሉ፣
ሲሞት የሚከፈንበት አንድ በቂ ነጠላ እንኳ አጥቶ በቅጠል (ሳር) ተጨምሮ ተከፈነ።
ሀከዘ ዱኒያ ያ አኺ ወ ያ ኡኽቲ
ይህን ያክል ክብራቸውንና ዱኒያቸውን ጥለው የተሰውለትን ዲን ነው እኔና እናንተ ዛሬ የያዝነው።
እኛስ ምን ሰርተን ይሆን
በነርሱ ፈለግ ላይ ነን
ራሳችንን እንጠይቅ!!
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
390 views18:01