Get Mystery Box with random crypto!

የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ne_siha_eslamik — የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ne_siha_eslamik — የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች
የሰርጥ አድራሻ: @ne_siha_eslamik
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.26K
የሰርጥ መግለጫ

بسم الله الرحمن الرحيم
📮እንኳን ወደዚህ ቻናል ተቀላቀሉ‼️
በዚህ ቻናል ቂርአቶችን፣ ሙሐድራዎችን፣ዳዐዋዎችን እና ሌሎችንም ከአረብገንዳ መስጊድ በአሚሩ አማካኝነት በቀጥታ የምታገኙበት ቻናል ነው።
ሃሳብ አስተያዬት ካለ በዚህ ያድርሱን ⤵️
@ye_Arebgenda_mesgid_wetatoch_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-08-24 21:22:41 በሰብርና በሰላት መታገዝ

አልሐምዱሊላሂ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ


#ሰው ሲፈጠር ደካማ ሆኖ ተፈጠረ ፣በስሜቶችና ፍላጎቶችም የተሞላ ሆኖ እንዲሁ።
ታዲያ ችግሮቹን ለመቋቋምና ከእዝነቱም በመቅረብ ለመቋደስ ያስችለው ዘንድ በኢማን ላይ የተመሰረተ  ሁለት መሳሪያዎች ተሰጡት።የችግር መላቀቂያ መድሀኒት ቀረበለት።
ሰብርና ሰላት
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱسْتَعِينُوا۟ بِٱلصَّبْرِ وَٱلصَّلَوٰةِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡ በቀራ 2 :153


ታላቁ ሰሐባ ዐብደላህ ኢብኑ አባስ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና በመንገድ እየሄዱ  የልጃቸውን  ሞት መርዶይረዳሉ።እርሳቸውም ከመጓጓዣቸው ወርደው ሁለት ረከዓ ሰላት ሰገዱና አላህ  አላህ  በመታገስና በሰላት ተረዱ  ብሏል በማለት በልጃቸው ሞት  የተከሰተባቸውን  ሀዘን ለመቋቋም የአላህን እገዛ ፍለጋ ወዲያውኑ ወደ ቀደሩ ባለቤት የሆነው ፈጣሪያቸው ለመጠጋት ትዕዛዙን ፈፀሙ
ምንኛ  የተወደደ በቀልብ የገባ፣ የረጋ፣ በተግባር የተረጋገጠ ኢማን ።
አላህ  ሆይ ሰብርና በሰላትና ከሚጠቀሙ የኢማን ባለቤቶች አድርገን።

http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
523 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:00:25 አቂደቱል ዋሲጥያ
ሸይህ ዑመር አሊ
ክፍል-9-
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ
508 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:00:15 የሰሐቦች ታሪክ ተከታታይ

ሀያቱ ታቢዒን

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

  "የኡማው ኢማን በአንድ መዳፍ፤ የአቡበክር ኢማን ደግሞ በሌላ መዳፍ ሆኖ ቢመዘን የአቡበክር ኢማን ባመዘነ ነበር፡፡” ነብዩ (ﷺ)
   
               ክፍል ሁለት
     እኚህ ታላቅ ሰው “አስ-ሲዲቅ” የሚል የማዕረግ ስምም ነበራቸው:: እውነተኛ ማለት ነው ስያሜውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኙበት አጋጣሚ ረሱል (ﷺ) “በኢስራእና በሚዕራጅ” ወደ ሰማየሰማያት ላደረጉትን ጉዞ  መጀመሪያና ከሁሉም ቀድመው ፅኑ እምነታቸውን የገለፁት እርሳቸው በመሆናቸው
ነበር፡፡ እውነትን አምነው በመቀበላቸው እውነተኛ ተባሉ፡፡ “ኣስ-ሲዲቅ'

   እናታቸውም ኡም አል-ኸይር ይባላሉ፡፡ ቢንት ሶኽርም ይባላሉ፡፡
በኢብን አቢአርቀም (ዳሩል አርቀም) ውስጥ እስልምና ከተቀበሉ
የመጀመሪያዎቹ ሶሓቢዎች ተርታ ይመደባሉ፡፡ አባታቸው አቡ ቁሀፋ
ግን ኢስላምን የተቀበሉት ዘግይተው ነበር፡፡ እስልምናን የተቀበሉት
(የሰለሙት) በእድሜያቸው መጨረሻ፣ መካ በድል በተከፈተች ጊዜ ነው፡፡ የኣቡበከር (ረ.ዐ) አባት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አስ-ሲዲቅ ባረፉ በስድስተኛ ወር ነበር፡፡ ሲሞቱም የዘጠና ስድስት ዓመት አዛውንት ነበሩ፡፡

            የአስ-ሲዲቅ የዘር ግንድ
አቡበክር የበኒ ተይም ጎሳ አባል ሲሆኑ በኒ ተይም ደግሞ ከቁረይሽ ጎሳዎች ውስጥ ዋንኛው ነው፡፡ ከነብዩ (ﷺ) ጋር በስድስተኛ አያታቸው በሙራ ቢን ከዕብ አማካኝነትም ይዛመዳሉ፡፡ ጎሳዎቻቸው በኒ ተሚሞች ለማስፈጸም አስቸጋሪ የነበረውን “አል-መጋሪም” እና “አል-ዲያት” (መቀጮ እና የደም ካሳ) የተባለውን ማህበራዊ ክንውን ያስፈጽሙ ነበር፡፡ ሰይድ አቡበክር (ረ.ዐ) ከእስልምና በፊት ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ከሚያስፈጽሙ አስር ሰዎች ውስጥ ዋነኛው ነበሩ።

             ውልደት
አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) የተወለዱት ከ "ዓመልፊል”(የዝሆን ዓመት) ሁለት ዓመት ከሰባት ወር በኋላ ነበር፡፡ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በሁለት ዓመታት ያንሳሉ፡፡ ነብዩ (ﷺ) ለነብይነት ማዕረግ ሲበቁ አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) የሰላሳ ስምንት ዓመት ወጣት ነበሩ፡፡

   አንድ ወሳኝ የሆነ ነገር ልጠቁማችሁ፡፡ የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) የታላቅነት ሰብዕና በዋናነት የሚጀምረው በሰላሳ ስምንት ዓመታቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ ሁኔታ አንድ ቁም ነገር መቅሰም እንችላለን፡፡ ይኸውም በተለይ ወጣቶች ወደ ጎልማሳነት እድሜ ተጠግቻለሁ ብለው ጊዜዬ አልፏል በሚል ብሂል ቁርኣንንና የሸሪዓ ትምህርትን ከመማር ተስፋ መቁረጥ እንደማይኖርባቸው ነው፡፡ የአቡበክር (ረ.ዐ) ታላቅነት ሀ ብሎ የጀመረው በዚሁ የእድሜ ክልል ገደማ መሆኑን ልብ ማለት ያሻል።

   ነብዩ (ﷺ) መካ ውስጥ ለአስራ ሶስት ዓመታት የዳዕዋ ቆይታ ካደረጉ በኋላ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ወደ መዲና ለመሰደድ ሲወጡ አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ተከትለዋቸው ተሰደዋል፡፡ ያኔ ነብዩ (ﷺ) የሃምሳ ሦስት፣ ሰይድ አቡበክር ደግሞ የሀምሳ አንድ ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ነበሩ።

   ሰይድ አቡበክር (ረ.ዐ) ነብዩን (ﷺ) በመተካት አመራሩን
ሲቀበሉ (ኸሊፋ ሲሆኑ) የስልሳ አንድ ዓመት ሰው ነበሩ፡፡ ከሁለት
ዓመት በላይም ሙስሊሞችን በመምራት ኸሊፋ ሆነው ቆይተዋል።
ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩም ልክ እንደ አሽረፈል ኸልቅ ሁሉ የስልሳ
ሦስት ዓመት አዛውንት ነበሩ፡፡ ህይወታቸው ያለፈችውም ልክ እንደ
ረሱል (ﷺ) ሁሉ ሰኞ እለት ነበር፡፡ ነገሩ አጋጣሚ ነው ልንል
ብንችልም ነብዩን (ﷺ) እግር በእግር ስንዝር በስንዝር ሲከተሉ
በመኖራቸው ሞታቸውም ሆነ እድሜያቸው ከረሱል (ﷺ) እኩል እንዲሆን በማድረግ ቸሩ አምላካችን አላህ (ሱ.ወ) ጸጋውን
አጎናፅፏቸዋል፡፡ ረዲየላሁ ዓንሁ!

             ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው
    አስ-ሰ.ዲቅ በጃሒሊያው ዘመን (ከኢስላም በፊት) ሁለት ሚስቶችን በየተራ ያገቡ ሲሆን ከስለሙ በኋላም እንዲሁ ሁለት ሚስቶችን በየተራ አግብተዋል፡፡

  በዘመነ-ጃሒሊያ ያገቧት የመጀመሪያ ሚስታቸው ቁተይላ ቢንት
ዓብዱል ዑዛ ትባላለች፡፡ እስልምናን ተቀብላለች አልተቀበለችም በሚለውጉዳይ ላይ የታሪክ ምሁራን ተወዛግበዋል፡፡ በክህደት ላይ በመጽናቷ ፈትተዋታል የሚል ዘገባም አለ፡፡ ይህም ሆኖ በትዳር ሕይወታቸው ወቅት አብደላህ ቢን አቡበክር የሚባል ልጅ ወልዳላቸዋለች፡፡ አብደላህ የሰይድ አቡበክር (ረ.ዐ) የበኩር ልጅ መሆናቸው ነው፡፡

  ረሱል (ﷺ) እና አቡበክር (ረ.ዐ) ወደ መዲና ሲሰደዱ "ሰውር" የተባለው ዋሻ ውስጥ ተሸሽገው በነበሩበት ወቅት የቁረይሾችን እንቅስቃሴ እየሰለሉ ዋሻው ድረስ በመሄድ ወሬ ያቀብሏቸው የነበሩት እኚሁ የበኩር ልጅ አብደላህ ነበሩ፡፡ አብደላህ የሰለሙት በመጀመሪያው የዳዕዋ (ተልዕኮ) ወቅት ነበር፡፡

  አብደላህ ብዙ ዘመቻዎችን ከነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ጋር በመሆን ዘምተዋል፡፡ ታግለዋልም፡፡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባታቸው ኸሊፋ በነበሩበት ወቅት ነበር፡፡ የተቀበሩት አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) በተገኙበት ነው፡፡ የኸሊፋው ልጅ በሞቱበት ወቅት በእጃቸው የነበረው ኃብት ንብረት ስድስት ዲርሃም ብቻ ነበር፡፡

    አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) በጃሒሊያው ዘመን ያገቧት ሁለተኛ ሚስት ደግሞ ኡሙሩማን ትባላለች፡፡ እስልምናን የተቀበለቸው ቀድማ ነበር፡፡ ወደ መዲና በመሰደድም ለነብዩ (ﷺ) ቃል-ኪዳን (ሙባየዓ) ገብታለች፡፡ አላህን (ሱ.ወ) በጽኑ የምትታዘዝ ባልቴት ነበረች፡፡

   ኡሙ ሩማን ለሰይድ አቡበክር (ረ.ዐ) ሁለት ልጆችን
አፍርታላቸዋለች። የመጀመሪያው አብዱራህማን ሲሆን ሁለተኛዋ ደግሞ የምዕመናን እናት የሆኑት እሜቴ ዓኢሻን (ረ.ዐ) ነው፡፡ አብዱራህማን እስልምናን የተቀበሉት በጣም ዘግይተው ነበር፡፡ እንደውም በበድርና ኡሑድ ዘመቻዎች ከሙሽሪኮች (ከከሐዲያን) ጋር ወግነው ከአባታቸው አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ)
በተቃራኒ ተሰልፈው ሙስሊሞችን ተዋግተዋል፡፡ እስልምናን ከተቀበሉና በእስልምና ውስጥ መኖር ከጀመሩ በኋላ ከታላቁ ሶሃቢና የጦር ጀኔራል ኻሊድ ቢን አልወሊድ (ረ.ዐ) ጋር በመሰለፍ ሻምና ኢራቅን ባቀናው የአል-የማማ ዘመቻ ላይ በግንባር ቀደምትነት ተሳትፈዋል፡፡

   ሰይድ አቡበክር አስ-ሲዲቅ(ረ.ዐ) እስልምናን ከተቀበሉ በኋላ ያገቧትና ሶስተኛ ሚስታቸው ደግሞ አስማእ ቢንት ዑመይስ ትባላለች፡፡ "ሙሐመድ ቢን አቡበክር የሚባል ወንድ ልጅ ወልዳላቸዋለች፡፡ አስማእ በርካታ ሶሃባዎችን በየተራ አግብተው እንደነበር ይነገራል፡፡ ከነዚህም አንዱ ጃዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ ናቸው፡፡ ከጃዕፈር ሶስት ልጆችን ወልደዋል። አስ-ሲዲቅን (ረ.ዐ) ያገቧት ጃዕፈር ቢን አቢጧሊብ (ረ.ዐ) ከተሰዋ በኋላ ነበር። መሐመድ ቢን አቡበክርን የወለዱትም ከዚህ በኋላ ነው። ስይድ አቡበክር (ረ.ዐ) ከሞቱ በኋላ አስክሬናቸውን እንድታጥብ
የተናዘዙት ለዚህችው ባለቤታቸው ነበር፡፡ በእስልምና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሏን አስክሬን ያጠቡት ሴት አስማእ ቢንት ዑመይስ ናቸው፡፡

   አኚሁ ሶሃቢት ከሰይድ አቡበክር (ረ.ዐ) ሕልፈት በኋላ፤ ከታላቁ
ኸሊፋ ከሰይድ ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረ.ዐ) ጋር በጋብቻ ኖረዋል፡፡

   ▻▻ኢንሻአላህ ይቀጥላል◅◅
ለሌሎችም ሼር ያድርጉ

http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
በኢስላምእንኖራለን...በሰለፎችፋና
485 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:32:03
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ


#ቁርኣን
594 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:31:56 ቁራአንን ስትቀራ  ወይም ስታዳምጥ ከልብህ ይሁን

   በተረጋጋ መንፈስ ይሁን ስታነበው ቁራአንን  አዳምጡት በብዙ ልባችሁ ይረጋጋ ዘንድ !!!
http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ

 
554 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:42:46 Watch "ሸይህ ሙሀመድ ጧሂር//ፅናት በኢስላም//" on YouTube


477 views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:42:39 አቂደቱል ዋሲጥያ
ሸይህ ዑመር አሊ
ክፋል-8-
537 views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:42:33 የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

  "የኡማው ኢማን በአንድ መዳፍ፤ የአቡበክር ኢማን ደግሞ በሌላ መዳፍ ሆኖ ቢመዘን የአቡበክር ኢማን ባመዘነ ነበር፡፡” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)
        
           ክፍል አንድ

   ምስጋና ለኃያሉ ጌታ አላህ (ሱ.ወ) የተገባ ነው፡፡ እናመሰግነዋለን፡፡ እገዛውንም እንሻለን፡፡ ምህረቱን እንጠይቃለን፡፡ ቀጥተኛውን ጎዳና እንዲመራንም እንማጸነዋለን፡፡ እርሱ ወደ ቀጥተኛው ጎዳና የመራውን የሚያጠመው እንደሌለ ሁሉ እርሱ ያጠመመውንም የሚያቀናው የለም፡፡

   ስለ ታላቁ ኸሊፋ አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ማራኪ ታሪክ ከማውጋታችን በፊት አንድ ጥያቄን ፡ዕናስቀድም ?ለመሆኑ የእስልምና ተዓምር ምንድን ነው? እንደሚታወቀው ሁሉ በምድራችን ላይ ተነስተው የነበሩ ነብያት ሁሉ ዳዕዋቸውን ሲያካሂዱ የነበረው በተዓምራት(ሙዕጂዛ) እየታገዙ ነበር፡፡

   ሁሉም ነብያት ይዘው የተነሱትን ዳዕዋ ያግዝ ዘንድ ያሳዩ የነበርው ተዓምር በዘመኑ በነበሩ ሕዝቦች አቅም በተግባር ሊውል የማይችልና ከሰብዓዊ ፍጡር ችሎታ በላይ የሆነ ነገር ነበር፡፡ በዓረብኛ “ኻሪቁን ሊልዓዳ” ይባላል።

የሞተ ሰው ነፍስ ዘርቶ እንዲነሳ ማድረግ ነብዩላህ ዒሳ (ዐ.ሰ) የተሰጣችው ተዓምር ነበር። ነብዩ ዒሳ (ዐ.ሰ) በመዳበስ ብቻ ዓይነ ስውርን ያበሩ፣ ለምጻምን ይፈውሱ ነበር፡፡ ግዙፉን ቀይ ባህር ለሁለት የሰነጠቀውና ወደ እባብነት ይቀይር የነበረው በትር ደግሞ ለነብዩሏህ ሙሳ (ዐ.ሰ) የተቸረ ተዓምር ነበር።

ለመሆኑ የእስልምና ተዓምርስ ምንድን ነው?

የእስልምና ሃይማኖት ዋነኛ ተዓምር ቁርኣን እንደሆነ ነው ከልጅነታችን ጀምሮ የምናውቀው፡፡ ኧረ ለመሆኑ የቁርኣን ተዓምር ምንድን ነው?

በእርግጥ እጅግ በጣም አስደማሚና መሳጭ የሥነጹሑፍና የአገላለጽ ውበት ቅዱስ ቁርኣን መላበሱ እውነት ነው፡፡ ቁርኣን ሌሉችም በርካታ ዘለዓለማዊ ተዓምራትን በውስጡ አጭቆ ይዟል፡፡ ይኸውም፣ አንድ ሰው ቁርኣንን ለመንገዱ ብርሃን፣ ለሕይወቱ መመሪያ አድርጎ መያዝ ከቻለ በዚህ ዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ ሰዎች ውስጥ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከቅዱስ ቁርኣን ኅያው ተዓምራት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ማንኛውም ተራ ሰው የሕይወት መንገዱን ቁርኣን ካደረገ ከዓለማችን ዕንቁ መሪዎች ውስጥ አንዱ ይሆናል፡፡ ይህ በታላቁ ቁርኣን ካዝና ከተከማቹ ምስጢራት ውስጥ አንዱ ነው... በየትኛውም ጊዜና ቦታ ያለ ሰው ቁርኣንን ለመንገዱ ብርሃን ካደረገ ከታላላቅ ስብዕናዎች አንዱ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡

   ይህ ዘለዓለማዊ ተዓምር የተሰጠው የነብያት ሁሉ ማክተሚያና መደምደሚያ ለሆኑት ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ነው፡፡ የርሳቸው ተልዕኮ ደግሞ የትኛውንም ዘመንና ጊዜን የሚያጥለቀልቅ ብርሃን ነው፡፡ የቁርኣን ተዓምር በየትኛውም ዘመንና ቦታ ሕያው ሊሆን የሚችለውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡

...እኛ የሰው ልጆች ይህንኑ ህያውና ዘለዓለማዊ ተዓምር መሠረት ከነበሩ ምርጥ መሪዎች ውስጥ አንዱ መሆን የማንችልበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።

    ተራ ሰው የነበሩት ታላቁ ሶሓቢ ሰዕድ ቢን አቢወቃስ(ረ.ዐ) ከታላላቅ መሪዎች ተርታ ለመሰለፍ ጊዜ ያልወሰደባቸው ቁርኣንን ለሕይወታቸው መመሪያ፣ ለመንገዳቸው ብርሃን በማድረጋቸው ብቻ ነበር፡፡ ሌላ ምስጢር የለውም፡፡ ሶሓባው ተራ ሰው ነበሩ፡፡ የቁርኣንን ተዓምር በቀኝ እጃቸው ሲያነግቡ ግን ታሪክ በክብር መዝገቡ ያሰፈራቸው ታላቅ የጦር መሪ ለመሆን በቁ፡፡ በአል-ቃዲሲያ ዘመቻ ግዙፍ ጦር ሠራዊትን ከጀርባቸው በማስከተል ታላቂቱንና አይበገሬዋን ፋርስ ተቆጣጠሯት፡፡ የጣዖታት መናኸሪያ የነበረችውን ፋርስ ወደ ሰፊ የኢስላም ማሳነት ለወጧት። ተራ ሰው የነበሩት ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ!(ረድየሏሁ ዐንሁ)

   የእስልምና ተዓምር  እጅግ ተራና መሐይም የነበሩትን ሰዎች ከዚያ ከዘቀጠና ከጨለማ ህይወታቸው አውጥቶ ለሰማይና ለምድሩ የከበዱ ታላቅ ሰው እንዲሆኑ አድርጎ በአዲስ መልክ መፍጠር ችሏል፡፡ ከእነኚህ በቁርኣን ተዓምር
ከተራነት ወደ ታላቅ ሰውነት በአዲስ መልክ ከተለወጡት ግለሰቦች ውስጥ አንዱ ዑመር ኢብን አል-ኸጧብ ናቸው፡፡ እኚህን ታላቅ ሰው ታሪክ በክብር ማህደሩ የመጀመሪያ ገጽ አስፍሯቸዋል፡፡ አል-ኸጧብ በቁርኣን ተዓምር አማካኝነት ድንቅ የፖለቲካ ሰው፣ ምርጥ ሃሳቦችን አፍላቂ ጀግና ለመሆን ችለዋል። ሰይዱና ዑመር(ረ.ዐ) በቁርኣን ምስጢር አማካኝነት የኢኮኖሚ ሊቅ፣ ጥበቡ የላቀ የጦር
መሐንዲስ ለመሆን በቅተዋል፡፡

      ዑመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ከትቢያ መሬት ተነስተው የዐረብ ፔንሱላ (የጀዚረተል ዓርብ) ፣ የግብዕ፣ የሻም፣ የኢራቅና የተቀረውን የሙስሊሙ ዓለም ጠቅልለው ሊገዙና ሊያስተዳድሩ የቻሉት የቁርኣንን ተዓምር መሠረታቸው በማድረጋቸውና የቁርኣንን ተልዕኮ ሊደርሱበት በመቻላቸው ነበር፡፡

     ራስን አሳልፎ የመስጠት፣ የለጋስነት የጽኑ እውነተኝነት አብይ ተምሳሌት ለመሆን የበቁት አቡበከር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ተራ ነጋዴ ነበሩ፡፡ ተራ ነጋዴ፡፡ ከተራነት ወጥተው ለዓለም ሙስሊሞች አብይ ተምሳሌት ለመሆን የቻሉት ታዲያ ቁርኣንን ምርኩዝ በማድረጋቸው እንጂ በሌላ አልነበረም፡፡ረዲየሏሁ ዐንሁ!

    ተዓምረ-ቁርኣን ሰዎችን ለዘለዓለሙ እንዲህ እየለወጠ ይኖራል፡፡ተራና ከቁጥር የማይገቡ ሰዎችን ነጥሎ እያወጣ ፍትሃዊ፣ አዛኝ፣
ስብዓዊነትን የተላበሱ የዓለማችን ድንቅ መሪዎችና ገዢዎች ያደርጋቸዋል። የፍትህ መጓደልን የሚያስወግዱ፣ የሰብዓዊ መብት
ጥሰትን የሚያስቀሩ መሪዎች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡

   በእርግጥ ስለ አቡበክር አስ-ሲዲቅ ማንነት ሙሉ በሙሉ መግለፅ ይከብዳል፡፡ የትኛው ቃል ይሆን የርሳቸውን ታላቅነት ቁልጭ አድርጎ ሊያስቀምጥ የሚችል? በጣም ይከብዳል...
አቡበክር አስ-ሲዲቅ ተቆጥሮ የማይዘለቅ የሰናይ ምግባር፣ የጀግንነትና ታላቅነት ባለቤት ነበሩ፡፡ የትኛውም ቃል እርሳቸውን የሚገልፅ አይደለም...

           አቡበክር አስ-ሲዲቅ ማን ናቸው?

    ትክክለኛ ስማቸው ዐብደላህ ሊሆን ይበልጥ የሚታወቁት ግን አቡበክር በሚለው ቅጽል ስም ነው፡፡ ወላጅ አባታቸው ደግሞ አቡ ቁሀፋ ይባላሉ፡፡ አቡበክር(ረ.ዐ) አል ዐቲቅ የሚል የማዕረግ ስምም አላቸው በዚህ የማዕረግ ስም የሰየሟቸው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው፡፡ ነፃ የወጣ ማለት ነው ትርጉሙ፡፡ በአንድ ወቅት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸው ተነግሯል፡፡ “አላህ ከእሳት ነፃ ያወጣውን ሰው ማየት የፈለገ አቡበክርን ይመልከት፡፡"
በሌላ ዘገባ ደግሞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለአቡበክር (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋቸዋል "አንተ አቡበክር ሆይ! አንተ አላህ ከእሳት ነፃ ካወጣቸው ሰዎች ነህ"

   'አል ዓቲቅ' በሚል ይጠሩ የነበረው ከእስልምና በፊት ነው ተብሎ ተነግሯል፡፡ መልካቸውም ሆነ ምግባራቸው ውብ ስለ ነበር በዚህ የማዕረግ ስም ይጠሩ ነበር ተብሎ ይነገራል፡፡ በዓረብኛ ቋንቋ አንድ መጥፎ ምነ-ምግባር ያለው ግለሰብ "ሙዓቲቅ” ተብሎ ይጠራል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ያለው ደግሞ “ዓቲቅ” ይባላል፡፡ የአቡበክር (ረ.ዐ) ሥነ-ምግባር ግን ምን ጊዜም ቢሆን “ዓቲቅ" ነበር፡፡ ዕጹብ ድንቅ!

      ➢➢➢➢ይቀጥላል

  ኢንሻ አላህ


http://t.me//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
518 views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 10:48:18 #ሶላት_የማይሰግድ_ሰው_አንገት_እንደሌለው_ነው_የሚቆጠረው

ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.አ.ወ)
ሶላትን የመተው አደጋው
የአደምልጅ ሆይ
☞ስትወለድ ጆሮህ ላይ አዛን ይባልብሀል
☞ስትሞት ሶላት ይሰገድብሀል
☞በዱኒያ ላይ ሂወትህ ከአዛን እስከ ሶላት እንዳለው ጊዜ ነው ስለዚህ ሳይሰገድብህ ስገድ ጊዜህን በማይጠቅምና
❖ባልባሌ ቦታ አታሳልፍ
❖መቆያህን መስጅድ መረጋጊያህን ቁርአንን አድርግ።

አላህ ሱብሀነሁወተአላ ሶላትን ደንግጓል።
የኢስላምም ምሰሶና አስኳል አድርጎታል።
ነቢዩ ሙሀመድም( ) እንዲህ ብለዋል ፦ የነገሩ ሁሉ ራስ ኢስላም ነው።ሶላት ምሰሶው ነው። ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ጂሃድ ደግሞ ጣራው ( ሻኛው) ነው።
ከኢባዳዎች ሁሉ በቅድሚያ ግዴታ የተደረገው ሶላት ነው።

ነቢዩ ወደ ሰማይ ባረጉበት ሌሊት ።አዎ በዚያች በተከበረችወወ ሌሊት ያለማንም አገናኝ ( መልእክት አስተላላፊ) አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ነቢዩን የሶላትን አስፈላጊነትና ግዳጅነት በቀጥታ አሳወቃቸው ። ለዚህ ነው ሶላትን ሆን ብሎ የተወ ሰው ወደ ክህደትና ጥመት ደረጃ ደርሷል ወይም ከሃዲ ነው የሚል ብይን የሚሰጠው ።
በርግጥ ከሶላት የራቀ ሰው

☞ከኢስላም ርቋል ፤
☞ጌታውን አስቆጥቷል ፤
☞ራሱንም ለጥፋት ዳርጓል ፤
☞መልካም ስራውንም አውድሟል ።

የአላህ መልእክተኛ  እንዲህ ብለዋል ፦ በአንድ ሰውና በክህደት መካከል ( መለያ የሚሆነው) ሶላት መተው ነው።
ኢማሙ አህመድ እና ሌሎችም ቡረይዳ( ረ ዐ) የተባሉትን ሰሃባ ( ረ ዐ) ጠቅሰው እንደዘገቡት ነቢዩ  እንዲህ ብለዋል ፦ በኛና በነርሱ ( በከሃዲዎች) መካከል ያለው ልዩነት ሶላት ነው ። ሶላት የተወ ሰው በርግጥ ክዶአል ።

አብደላህ ኢብን ዑመር ( ረ ዐ) እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ ( ) ስለ ሶላት የሚከተለውን ብለዋል ፦ ሶላትን የጠበቀ ለርሱ ብርሃን ማስረጃና ነፃ መውጫ ይሆነዋል ።
ሶላትን ያልጠበቀ ለርሱ ብርሃን ፣

ማስረጃና ነፃ መውጫ አይኖረውም ። በእለተ ትንሳኤ ከቃሩን፣
ከፊርኦውን እና ከኡበይ ኢብኑ ኸለፍ ጋር ይሆናል ( ይጎዳኛል) ።

አላህ ተከሳሪወች አያድርገን ከጀሀነም ቅጣትም እሱው ይጠብቀን አንተ አዛኝ ነህና እዘንልን የአላህ
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
በኢስላምእንኖራለን...በሰለፎችፋና
598 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:48:16 አቂደቱል ዋሲጥያ
ሸይህ ዑመር አሊ
ክፍል -7-
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
681 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ