2022-10-06 11:24:24
┈ድንቅ ታሪክ ናት┈┉┅━
{በሙሳ ዐ.ሰ} በዘመን ነው ....
አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።
ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል.።
እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ
#ሚስት #ለባለቤትዋ፦"ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።
#እሱም፦"አዎን" ይላታል።
"ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው።
ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ {ሙሳ ዐ.ሰ} ቤት ጀመሩ።
{ሙሳንም ዐ.ሰ} አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።
{ሙሳም ዐ.ሰ} አላህን ለመኑላቸው።
#አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ ! አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ። #ብሎ_መለሰላቸው።
እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ #አላህ ዱዓቸውን #ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው። ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ቢቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው።
በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ። እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ #ሚስት #ለባሏ እንዲህ አለችው፦
"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለአንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን #አንድ_መልካም_ስራ_እንስራ
#ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።
ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ #ጠዋት #ማታ ምግብ ይቀልቡ ጀመር...በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።
#ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል....
{ሙሳንም ዐ.ሰ} ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦
#ያ_ረብ_ቃል_የገበኽላቸው_ለአንድ_አመት_ሆኖ_ሳለ_እንዴት_እስካሁን_እልደኸዩም?"ብለው አላህን ጠየቁ። እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን #የአላህን_ሂክማ_ለማወቅ_ነው።
የጠየቁት/ ቸር የሆነው #አላህም፦ ሙሳ ሆይ ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው... እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ። ሙሳ ሆይ እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው።
━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━
SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
135 views08:24