Get Mystery Box with random crypto!

┈ድንቅ ታሪክ ናት┈┉┅━ {በሙሳ ዐ.ሰ} በዘመን ነው .... አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

┈ድንቅ ታሪክ ናት┈┉┅━

{በሙሳ ዐ.ሰ} በዘመን ነው ....
አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።
ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል.።

እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ
#ሚስት #ለባለቤትዋ፦"ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።

#እሱም፦"አዎን" ይላታል።
"ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው።

ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ {ሙሳ ዐ.ሰ} ቤት ጀመሩ።
{ሙሳንም ዐ.ሰ} አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።
{ሙሳም ዐ.ሰ} አላህን ለመኑላቸው።


#አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ ! አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ። #ብሎ_መለሰላቸው።

እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ  #አላህ ዱዓቸውን #ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው። ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ቢቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው።

በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ። እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ #ሚስት #ለባሏ እንዲህ አለችው፦

"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለአንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን #አንድ_መልካም_ስራ_እንስራ
#ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።

ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ #ጠዋት #ማታ ምግብ ይቀልቡ ጀመር...በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።

#ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል....

{ሙሳንም ዐ.ሰ} ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦
#ያ_ረብ_ቃል_የገበኽላቸው_ለአንድ_አመት_ሆኖ_ሳለ_እንዴት_እስካሁን_እልደኸዩም?"ብለው አላህን ጠየቁ። እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን #የአላህን_ሂክማ_ለማወቅ_ነው።


የጠየቁት/ ቸር የሆነው #አላህም፦ ሙሳ ሆይ ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው... እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ።  ሙሳ ሆይ እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው።

━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━

SHARE SHARE
http://t.me//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ