Get Mystery Box with random crypto!

42ኛ  ሓዲስ መሃርታን መጠየቅ እና ተውሒድ :አነስ ኢብን ማሊክ የአላህ መልእክተኛ صلى ال | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

42ኛ  ሓዲስ

መሃርታን መጠየቅ እና ተውሒድ

:አነስ ኢብን ማሊክ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ፦ አላህ እንዲህ አለ “አንተ የአደም ልጅ ሆይ!አንተኮ በጠራሃኝ እና መሃርታን በጠየቅከኝ ግዜ ካንተ ምንም ቢኖርም እምርሃለሁ ወንጀልህ ቢበዛም ምንም አይመስለኚም። አንተ የአደም ልጅ ሆይ!ወንጀልህ ሰማይ ቢደርስኳ መሃርታን ከጠየቅከኝ እምርሃለሁ። አንተ የአደም ልጅ ሆይ!አንተኮ ምድርን የሞላ ወንጀል ይዘህ በእኔ ግን ሳታጋራ ወደኔ ብትመጣ ከዚያም ብትገናኘኝ እኔም እሷን በሞላ መሃርታ ወዳንተ እመጣ ነበር።”

ሓዲሱን ቲርሚዚይ ዘግቦታል

ከአርባ ሁለተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

.የሰው ልጅ ኣላህን በለመነ እና ከኣላህ በከጀለ ቁጥር ኣላህ እንደሚምረው።
.የኣላህ እዝነትን እንረዳለን። 
.የሰው ልጅ ወንጀል ቢበዛም፣ ከኣላህ መሃርታን ከጠየቀ ኣላህ እንደሚምረው።  
ተውሒድ (ኣምልኮን ለኣላህ ብቻ ማድረግ እና ኣምልኮን ለኣላህ ብቻ ብሎ መስራት)በጣም ትልቅ ደረጃ እንዳለውና ወንጀላችንን እንድንማር እንደሚያደርግ።
 
:አርበዑነ ነወውያ(42 ሀዲሶች))
       ከ27ኛው -42 ኛው ሀዲስ ተጠናቀቁ

http://t.me//@arebgendamesjid